በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞች ከመስጠም ዳኑ


ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ፍልሰተኞች የሜዲትራኒያንን ባህር በማቋረጥ ወደ አውሮፖ ለመሻገር ሲሞክሩ
ፎቶ ፋይል፦ አፍሪካ ፍልሰተኞች የሜዲትራኒያንን ባህር በማቋረጥ ወደ አውሮፖ ለመሻገር ሲሞክሩ

ከትናንት በስተያ ቅዳሜ በሜዲትራኒያን ባህር አደጋ ላይ የነበሩ ቢያንስ ስድሳ አምስት የሚሆኑ ስደተኞች የኢጣሊያ ዕቃ ጫኝ መርከብ ደርሶላቸው ህይወታቸውን ማትረፉ ተዘገበ።

የአሶ ቬንቲኖቬ መርከበኞች ሲናገሩ የሚበዙት በተዳከመ የእንጨት ጀልባ ተሳፍረው የነበሩት ሴቶች እና ልጆች መሆናቸውን ገልጸው በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸዋል።

መጠን በላይ የተጨናነቀው ጀልባ ሞተሩ ተበላሽቶ ባህሩ ላይ ሲዋልል፤ ሲበርድ የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ሜዲትራኒያን ባህር መሃል ላይ አደጋ ላይ ያሉ ፍልስተኞችን እንዲቃኝ የሚያሰማራው አውሮፕላን እንዳየው ተገልጿል።

ፍልሰተኞቹ አንዳቸውም ውሃ ላይ መንሳፈፊያ ሰደሪያ ያልለበሱ እንደነበሩ መርከበኞቹ ገልጸዋል። በሌላም በኩል ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት የስፔይን ሲቪላዊ የባህር ጥበቃ አገልግሎት አርባ ስምንት ፍልሰተኞችን አውጥቶ ሞትሪል ወደተባለች የስፔን ደሴት በማድረስ ህይወታቸውን ማትረፉ ተዘግቧል።

እአአ በ2021 ብቻ ቢያንስ 44,000 አውሮፓ ገብተን የተሻለ ኑሮ እናገኛለን በሚል ጉጉት ህይወታቸውን በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ ለአደጋ በማጋለጥ ከሊቢያ እና ከቱኒዥያ ሜዲትራኒያን ባህርን እንዳቋረጡ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG