አራቱን የፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላትን ጨምሮ ዘጠኝ እስረኞች በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታወቀ።
“እንደምን ዋላችሁ ልዑካን! አንዳች ታሪክ እውን ልናደርግ ተዘጋጅተናል?” የኦሃዮ ክፍለ ግዛቷ ዲሞክራት ማርሻ ፈጅ፤ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ልዑካን ሂላሪ ክሊንተንን የፓርቲው እጩው ያደረጉበትን ድምጽ ለመስጠት በተሰናዱበት ያቀረቡት ሃሳብ አዘል ጥያቄያቸው።
የዘንድሮዋ ወ/ት ኢትዮጵያ በዩናይትድ ስቴትስ በትውልድ ስሟ ሔለን ወርቁ አሁን ደግሞ ሔለን ኬነርድ ትባላለች። የ29 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ የተወለደችው ሆለታ ከተማ ነበር።
የአምባሰልን ቅኝት በድምጿ ስትጫወተው የተደመሙ የሙዚቃ ባለሞያዎች "አምባሰልን ከተራራው በላይ ያገነነች"ይሏታል። የወሎ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ለዚች እንቁ ድምፃዊ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷታል። እንሷም “አንባሰልንማ ከእኔ በላይ የተጫወተው….” ትላለች- ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ።
የወባ ትንኝ በከፍተኛ ሁኔታ የሚራባበት ቦታ ይኖሩ ከሆነ ዶሮዎችን ከመኝታዎ አጠገብ አድርጎ መተኛቱ ያዋጣል የሚል ጥናት በቅርቡ ተሰምቷል። የዶሮ የተፈጥሮ ጠረን የወባ ትንኝን አርቆ የሚያበር ሆኗል። ይህ ጠረን በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ህመምም ለመከላከል ታላቅ አስተዋፆ እንዳለው በጥናቱ ተደርሶበታል።
ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚረዳ መድሃኒት ለማግኘት አበረታች ሳይንሳዊ ጥናቶች መኖራቸው፤ የፈውስ መድሃኒትን ለማግኘት የተያዙ ምርምሮችና፤ የቫይረሱን መቋቋሚያ እንክብሎች ቫይረሱን ለመከላከል ማስቻላቸው፤ በዚህ ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ በሚገኘው አለም አቀፉ የኤድስ ጉባዔ አትኩሮት የተደረገባቸው ጉዳዮች ሆነዋል።
ከትላንት በስትያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በተጀመረው አለም አቀፉ የኤድስ ጉባዔ ላይ ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የመድሃኒት ግኝት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባዔው ቫይረሱን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ምን እንደተሰራ ይገመግማል፤ ለመጪዎቹ አምስት አመታት ሊተገበሩ የሚገባቸውን አዳዲስ እቅዶችንም ያወጣል።
ህፃናትን ከቫይረሱ በመከላከል ዙሪያ በሰፊው በመሰራቱ እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም ከተመዘገበው የሕፃናት የመያዝ ቁጥር 70 በመቶ ቀንሶ ታይቷል። በኤች አይ ቪ የተያዙ አዳዳዲስ አዋቂዎች ላይ በተደረገው ጥናት ግን በ2010 ዓ.ም ከተመዘገበው ቁጥር ጋር ሲተያይ ምንም አይነት ለውጥ አላሳየም። ለአምስት አመታት ቁጥሩ 1.9 ሚልየን ላይ ቆይቷል።
አለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በኤልኒኖ ምክንያት ከ600 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን መፈናቀላቸውን አስታወቀ።
የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ የነበረው አቶ ሃብታሙ አያሌው የህክምና እርዳታ ሲያገኝበት ከቆየበት ሆስፒታል ዛሬ ወደ ሌላ ስፍራ ለመዛወር መገደዱ ታወቀ።
በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በመንግስት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ያለፈ አቶ ሲሳይ ታከለ የተባሉ አንድ አዛውንት የቀብር ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ መፈጸሙን ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግሥት በግጭቱ አምስት ሰዎች በተባራሪ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
ናዝራዊ ኢያሱ አባቱ ኢትዮጵያዊ እናቱ ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው። ወላጆቹ እኤአ ከ2001 ዓ. ም. ጀመሮ በኬንያ በስደት ነው የኖሩት። ኬንያ እንደመጡ ከናይሮቢ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘዉ ናሮክ ከተማ ኑሯቸውን መሰረቱ።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ዜጎች ለረዥም ዓመታት የኖሩበት ቤት ፈርሶ ለጎዳና ተዳዳሪነት መጋለጣቸውን አጥብቆ ያወግዛል ሲል መግለጫ አወጣ።
በጎንደር ከተማ ከትላንት ጀምሮ በተፈጠረው ውጥረት ሳቢያ ሕይወት እየጠፋና ንብረት እየወደመ መሆኑ ተነገረ።
ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ በመንግሥት ከተዘጋ አምስት ቀናት ስላስቆጠረው ማኅበራዊ ሚዲያ ጽዮን ግርማ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ተጨማሪ ይጫኑ