የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከምዕራባውያኑ የሙዚቃ ስልት ጋር በአንድ ላይ በማቀናበር በተለያዩ የአውሮፓ የሙዚቃ መድረኮች ላይ ከአውሮፓ እውቅ ሙዚቀኞች ጋር በመሆን ስራውን የማሳየት ተደጋጋሚ እድሉን አግኝቷል። “የኢትዮጵያ ሙዚቃ በእንደኔ አይነት ቅንብርና የአጨዋወት ስልት ፤የተለየ አይነት የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሆኖ እንዴት ለሌላ አለም መቀረብ ይችላል የሚል ህልም እና ምኞት ስለነበረኝ፤ ያሬድ ውስጥ ቁጭ ብዬ የኢትዮጵያ ቅኝቶች ላይ እመራመር ነበር።” ሳሙኤል ይርጋ።
“በ1900 ዓ/ም ጥቅምት25 ቀን ምኒልክ በአዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶችንና የውጭ አገር ሰዎችን ጋብዘው ሆቴሉን አስመረቁ። በኋላ ግን እንደ አገር አባባል ጣይቱ እጅ የሚያስቆረጥም ወጥ እያሠሩ ገበያ ቢጠብቁ ጠፋ። እንኳን ምግብ መብላት ከግሪኮቹ ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ መጠጣት ነውር ነበረና: ጣይቱ ጠዋት የሚያሠሩት ወጥ ለሠራተኞቹ የማታ ራት ይሆን ጀመር።”
የአዲስ አበባ ገፅታ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1960ዎቹ ምን ይመስል ነበር?
“የቅኔ ቤት ባህልና የሕይወቴ ገጠመኝ” የተሰኘው የይትባረክ ግደይ መፅሃፍ በዘመኑ የነበሩትን የኢትዮጵያ ከተሞችን በምናብ ለማስቃኘት ይሞክራል። “አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ የሚጠጣው ጠጅና ቢራ ነበር።ከጠዋት እስከማታ መጠጣት ስለማይከለከል አዲስ አበባ በዚህ በኩል ጥሩ አልነበረችም።” በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን የአዲስ አበባ ገፅታ ከተሰኘው ርዕስ ስር የተፃፈ ነው።
በጋቢና ሙዚቃ ሊጋብዟችሁ ዳኒ አይሬና ሳሚ ዳን ተዘጋጅተዋል። http://m.amharic.voanews.com/a/3126939.html
ጋቢና ቪኦኤን ፕሮግራም ለመከታተል ዌብ ሳይቱን ይጎብኙ። http://m.amharic.voanews.com/p/5520.html
ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡
ቆይታ ከሙላቱ አስታጥቄ እና ሄኖክ ተመስገን ጋር።
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ የመደረግን እቅድ ተከትሎ፤ በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ያገረሸው ተቃውሞ የዛሬው ውሎ ምን መልክ እንደነበረው ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስና በርዕሱ ዙሪያ የተጠናከረ ዘገባ።
“ከአራት በላይ የፖሊስ ባልደረቦች ተገድለዋል” የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ
የድረገጽ ገበያ በኢትዮጵያዊያን፡- ሽሮና በርበሬ ብራውዝ ሊደረጉ ነው!