ቱርክ ሩስያ የሸጠችላትን የመጀመሪያዋን ኤስ 4መቶ የሚሳይል መከላከያ መሳሪያ ዛሬ መረከቧን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ወግ አጥባቂ ቡድኖች ታዋቂ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ ስለሚሰራጩ ዘገባዎች ለመወያየት ዛሬ ዋይት ኃውስ ውስጥ ይታደማሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በኢራን ላይ የተጣለውን የምጣኔ ኃብት ማዕቀብ በቅርቡ በጣም ከፍ እናደርገዋለን ሲሉ ተናገሩ።
በኢራን ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ከፍ ባለ መጠን ይጨመርባታል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።
በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ የድንበር ክፍለ ግዛት ቴክሳስ የፍልሰተኛ ማቆያ ማዕከሎች ከባድ የሆነ ለተራዘመ ጊዜ የማቆየት እና በሰው ብዛት የመጨናነቅ ችግር መኖሩን ባለፈው ሳምንት የአገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዋና ተቆጣጣሪ (ኢንስፔክተር ጀነራል) አጉልተው አስገንዝበዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የእንግሊዝ አምባሳደር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “እርባና ቢስ”፣ “በራስ መተማመን የጎደላቸው” እና “ብቃት የሌላቸው”፤ አስተዳደራቸውም “በተለየ ሁኔታ የተመሣቀለ” እንደሆነ በመግለፅ ማዋደቃቸው ይፋ ከወጣ በኋላ ከአምባሳደሩ ጋር “ከእንግዲህ እንደማይሠሩ” ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
ኢራን የየኒውክሊየር መርሃ ግብሩዋን የሚገድበውን ስምምነት የማክበሩዋን ጉዳይ በተመለከተ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ተሰብስበው ኣንዲነጋገሩበት አውሮፓውያኑ የውሉ ፈራሚዎች እየጠየቁ ናቸው።
በቴክሳስ ክፍለ ግዛት በሚገኙ ሁለት ማቆያ ቦታዎች ላይ የተያዙት ፍልሰተኞች በዘግናኝ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሚያሳዩ ምስሎች ይፋ ሆነዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ብዙዎቹ ፍልሰተኞች ከመጡበት ቦታ ይልቅ ባሉባቸው ሰፈሮች እጅግ በተሻለ የደኅንነትና በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።
የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለመገደብ ሲባል እአአ በ2015 ሥምምነት ከፈረሙት ሀገሮች የተጣለባትን ማዕቀብ ለማንሳት የሚያስችል ዕርዳታ ካላገኘች በስተቀር ኢራን ዩራንየሙን ከፍ ባለ ደረጃ ማዳበር ትጀምራለች ሲሉ የኢራን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ዛሬ ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን ጋር ያደረጉት ስብሰባ “እጅግ ውጤታማ ነበር” ካሉ በኋላ ሁለቱም ሀገሮች እንዲገፋበት ይፈልጋሉ ብለዋል።
የዓለም ኃያላን ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ኢራን፣ ቪዬና ውስጥ በዛሬው ቀን ተገናኘው፣ በ2015ቱ የኢራን የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ሥምምነት ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ።
ሩስያና የብሪታንያ ግንኙነት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል ከተፈለገ፣ ሩስያ ኃላፊነት የጎደለው የማፈራረስ ተግባሯን ማቆም አለባት ሲሉ፣ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ለሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አስጠነቀቁ።
ከህንድ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንደሚፈጠር የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ፣ ሁለቱ ሀገሮች፣ በወዳጅነት መንፈስ፣ ልዩነቶቻቸውን በንግድና በሌሎች ጉዳዮች እንደሚፈቱ ተስፋችውን ገልፀዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ እአአ ከ1992 ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ በከፍተኛ ደረጃ የተሰራጨ 33 አዳዲስ የኩፍኝ ወረርሽኝ ባለፈው ሳምንት ብቻ መገኘቱ ተገለፀ።
ሳዑዲ ዓረብያ እና ኪዩባ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን የመዋጋት ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ሀገሮችን በሚዘረዝረው የዩናይትድ ስቴትስ መዝገብ ገብተዋል። ጉዳዩ ሃገሮቹን ይበልጡን ለማዕቀብ ያጋልጣቸዋል።
በኢራን የሚታገዙት የየመኖቹ ታጣቂ ሁቲዎች ወደ ደቡባዊ ሳዑዲ ዓረብያ የተኮሱት ተወንጫፊ ሚሳይል አንድ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ አጠገብ ወድቋል። በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ግን የለም።
ኢራን በዓለምቀፍ የአየር ክልል የዩናይትድ ስቴትስን ካለአብራሪ ተጓዥ አውሮፕላን/ድሮን/ መትታ መጣሏን የመከላከያ ባለሥልጣኖቻቸው ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለኢራን በማኅበራዊ መገናኛ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡
እኤአ በ2014 ዩክሬን ላይ ተመትቶ የወደቀውን የማሌዥያ አየር መንገድ ጄት ጉዳይ እየመረመረ ያለው በኔዘርላንድስ የሚመራ መርማሪ ቡድን ሦስት ሩስያውያንና አንድ ዩክሬይናዊ በነፍስ መግደል ተጠርጣሪነት ይፋ አደረገ።
በዓለም ዙሪያ ጦርነት መሳደድ እና ግጭት አስገድዱዋቸው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ከሰባ አንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ አስታወቀ።
የቤጂንግ ወገንተኛዋ የሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ ካሪ ላም ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ የአፍቃሪ ዲሞክራሲ ትግል አቀንቃኙ ጃሹዋ ዎንግ እየጠየቁ ናቸው።
ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።
በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።
የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች ዛሬ የሀማስን ሠፈር መተዋል። ከጋዛ በተትኮሰ ሮኬት አንድ የሀይማኖት ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ነው ጄቶቹ የምላሽ ዕርምጃ የወሰዱት ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የማዕከላዊ አሜሪካ ፍልሰተኞች በአሜሪካ ጥገኝነት እንዳይጠይቁ ለማገድ በቀናት ውስጥ ከጓቲማላ ጋር ሥምምነት የማድረግ ተስፍ እንዳለው ገልጿል።
ተጨማሪ ይጫኑ