ኢራን በዓለምቀፍ የአየር ክልል የዩናይትድ ስቴትስን ካለአብራሪ ተጓዥ አውሮፕላን/ድሮን/ መትታ መጣሏን የመከላከያ ባለሥልጣኖቻቸው ማረጋገጣቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለኢራን በማኅበራዊ መገናኛ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፡፡
እኤአ በ2014 ዩክሬን ላይ ተመትቶ የወደቀውን የማሌዥያ አየር መንገድ ጄት ጉዳይ እየመረመረ ያለው በኔዘርላንድስ የሚመራ መርማሪ ቡድን ሦስት ሩስያውያንና አንድ ዩክሬይናዊ በነፍስ መግደል ተጠርጣሪነት ይፋ አደረገ።
በዓለም ዙሪያ ጦርነት መሳደድ እና ግጭት አስገድዱዋቸው ከቀያቸው የተፈናቀሉ ቁጥራቸው ከሰባ አንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ አስታወቀ።
የቤጂንግ ወገንተኛዋ የሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ ካሪ ላም ሥልጣናቸውን እንዲለቅቁ የአፍቃሪ ዲሞክራሲ ትግል አቀንቃኙ ጃሹዋ ዎንግ እየጠየቁ ናቸው።
ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።
በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።
የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች ዛሬ የሀማስን ሠፈር መተዋል። ከጋዛ በተትኮሰ ሮኬት አንድ የሀይማኖት ትምህርት ቤት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ነው ጄቶቹ የምላሽ ዕርምጃ የወሰዱት ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የማዕከላዊ አሜሪካ ፍልሰተኞች በአሜሪካ ጥገኝነት እንዳይጠይቁ ለማገድ በቀናት ውስጥ ከጓቲማላ ጋር ሥምምነት የማድረግ ተስፍ እንዳለው ገልጿል።
አንድ የኢራን የጥበቃ ጀልባ ጥቃት ከደረሰባቸው ሁለት ነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከቦች ከአንደኛው ያልፈነዳ ፈንጂን ሲያነሳ ያሳያል ያለውን ቪድዮ የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ይፋ አድርጓል።
ህንድ የራስዋን የጠፈር ጣብያ የመመስረት ዕቅድ እንዳላት አስታውቃለች። የህንድ የጠፈር አገልግሎት ሊቀ መንበር ኬ ሴቫን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ህንድ እአአ በ2030 ከ11 ዓመታት በኋላ፣ 20 ቶን የሚሆን የጠፈር ጣብያ የመመስረት ዕቅድ አላት ብለዋል።
ሜክሲኮ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት ሲሉ በግዛትዋ በኩል የሚያልፉትን ፍልሰተኞች ለመገደብ ከዩናይተድ ስቴትስ ጋር ባደረገችው ሥምምነት መሰረት ዛሬ ከጓቲማላ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የብሄራዊ ዘብ ወታደሮችን ታሰፍራለች ተብሎ ይጠበቃል።
የዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ መርማሪ ካውንስል ሮበርት ሞለር ባለፈው ዓመት በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካ እጃቸውን ዶለዋል በሚል የጠቅሷቸው የሩስያ ወታደርዊ ተቋራጭ የክረምሌን ተፅዕኖን በአፍሪካ ላይ ለማስፈን በሚያደርጉት ጥረት ቁልፍ ሰው ሆነው እየወጡ መሆናቸው ተዘግቧል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጭ የሚካሄደው እአአ በ2020 ሲሆን የቀረው 17 ወራት ቢሆንም ሪፖብሊካዊው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና እሳቸውን ለመተካት ከሚወዳደሩት ዲሞክራቶች መካከል ዋናው የሆኑት ጆ ባይደን አዮዋ ላይ የሚያካሄዱት የምርጫ ዘመቻ እንደሚጧጧፍ እሙን ነው።
የምርመራ ጋዜጠኛው ኢቫን ጋሉኖቭ ከቁም እስርነት ነፃ ሆኗል። ባለሥልጣኖች የታሰረበትን ምክንያት እየመረመሩ ነው ሲሉ የሩስያ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ቭላዲሚር ኮሎኮልሰቭ ተናግረዋል።
አንድ የህንድ ፍርድ ቤት በህንድ ካሽሚር የስምንት ዓመት ዕድሜ ህፃንን በአስከፊ ሁኔታ ደፍረው የገደሉ ሦስት ወንዶች ላይ የዕድሜ ልክ እስራት በይኗል።
ለብዙ ዓመታት ሕዝብን ያዝናናው ዶ/ር ጆን አረፈ፡፡
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሬሳ ሜይ ከወግ አጥባቂ ፓርቲው መሪነታቸው በዛሬው ዕለት ይለቃሉ። ተተኪያቸው የሚመረጡበት የመጀመሪያ ዙር ምርጫ በመጪው ሳምንት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላርስ ሎከ ራስሙሰን በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ ሶሺያል ዲሞክራቶች አብዛኛ የምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንደሚለቁ ዛሬ አስታወቁ ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ብሪታንያን እየጎበኙ ነው።
"ከሜላንያ ጋር ሆነን የሞቀ የኢድ አልፈጥር ሰላምታ እናስተላልፋለን" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረማፕ የበዓሉን መልዕክት አስተላልፈዋል።
እስራኤል በሶርያ የአየር ሠፈር ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ አንድ ወታደር ሲገደል ሁለት እንደቆሰሉ አንድ የመሳርያ መጋዘን ደግሞ እንደወደመ የሶርያ የመንግሥት ሚድያ ዘግቧል።
ቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ በሚያካሂዱት መራራ የንግድ ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስ ዐይን ያወጣ የኢኮኖሚ አሸባሪነት እየፈፀመች ነው ስትል ቻይና ከሳለች።
ልዮ መርምሪ ሮበርት ሞለር ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ዛሬ በሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ ከሀገሪቱ የፍርድ ሚኒስቴር በተሰጣቸው መመርያ መሰረት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን በወንጀል መክሰስ መሥርያ ቤታቸው ሊያስበው የማይችል ነገር ነበር ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በጃፓን ያካሄዱትን የአራት ቀናት ጉብኝት ሲያጠናቅቁ ቻይና እየመጠቀች በሄደችበት በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስና በጃፓን መካከል ወታደራዊ ትብብር የማጠናከሩ ጉዳይ ትኩረት ተደርጎበታል።
የየመን ሁቲ አማፅያን በደቡብ ሳውዲ ዓረብያ ናጅራን ከተማ የጦር መሳሪያ መጋዘን ላይ ጥቃት አድርሰናል ሲሉ ዛሬ አስታወቁ።
ተጨማሪ ይጫኑ