የአሜሪካ ድምፅ ባለፉት ሰባ አምስት ዓመታት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ያሉ የተለያዩ አድማጮችና ተመልካቾች ከሌሎች ምንጮች ሊያገኟቸው የማይችሏቸውን መረጃዎች ለዓለም ሲያደርስ መቆየቱን ዋና ዳይሬክተሯ አማንዳ ቤኔት ገልፀዋል።
"ሳይክሎን ፋኒ" ማዕበል ምሥራቅ ህንድ ግዛት ደርሶ በከባድ ዝናብና ንፋስ አካባቢውን እየደበደበ ነው።
ዋና ከተማዋ ካራካስ ውስጥ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ ነው ሲል ዛሬ የቬንዙዌላው ሶሺሊስት መንግሥት ተናገረ።
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን መጀመርያ የማስተማመኛ ዋስትና ካገኙ የኑክሌር መሳርያን ሊያስወግዱ ይችላሉ የሚል ዕምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።
አፍጋኒስታን ውስጥ ከታሊባን ጋር በመደራደር ላይ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ ዛልሜ ኻሊሊዛድ በሀገሪቱ የሚሞቱን ሰዎች ቁጥር ለመቀነስ የሚያስፈልገው የሰላም ሥምምነት ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
የፓኪስታን ፖሊሶች በገለፁት መሰረት ማንኑቱ ያልታወቀ ታጣቂ አንዲት በፖልዮ ክትባት ሥራ የተሰማራች የጤና ጥበቃ ስራተኛን ተኩሶ ሲገድል ሌላዋን ደግሞ አቁስሏል።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲውን ወክሎ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር በሚካሄደው የምርጫ ዘመቻ እንደሚስተፉ ዛሬ አስታውቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሜክሲኮ አዲስ ፍልስተኞች ጥገኝነት ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በመከላከል ተግባር በቂ ጥረት አላደረገችም በማለት በአዲስ መልክ እየነቀፏት ነው። በተጨማሪም የሜክሲኮ ወታደሮች በቅርቡ ድንበሩ ላይ ባሉ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጠመንጃ ወድረዋል ሲሉም ነቅፈዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመጪው ዓመት የህዝብ ቆጠራ በሚካሄድበት ወቅት በሀገሪቱ የሚኖሩት ሰዎችን ሁሉ ዜግነት መጠየቅን ያካትት እንደሆነ ዛሬ በከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ተደርጎበታል።
የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂ ወይም የመሬት ምርምር ጥናት ደቡባዊ ፊሊፒኒስ በሌላ ከባድ የመሬት ነውጥ ተመቷል።
የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በያዝነው ሳምንት ቭላዲቫስቶክ ወደ ተባለችው የሩቅ ምስራቅ የሩስያ ከተማ ይጓዛሉ።
ጋዜጠኞች ማሠሯን አጠናክራ የቀጠለችው ኢራን በዓለም የፕሬስ ነፃነትን በሚያከብሩ ሠንጠረዥ ላይ ደረጃዋ ይበልጥ ማዘቅዘቁን ዓለምቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ቡድን /Reporters Without Borders/ አስታወቀ።
በኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸንፌአለሁ ሲሉ በጡረታ ላይ የሚገኙት የጦር ሠራዊት ጄኔራል ፕራቦዎ ሱቢአንቶ አወጁ።
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ አቻቸው ቭላዲሚር ፑቲን በያዝነው የአውሮፓ ወር መጨረሻ ሞስኮ ላይ ለመገናኘት አቅደዋል።
ፈረንሣይ ዋና ከተማ ፓሪስ እምብርት ላይ የሚገኘው ትናንት ከባድ ቃጠሎ የደረሰበት ድንቁ ኖትር ዳም ካቴድራል ግንቡንና በውስጡ የሚገኙትን ዋና ዋናዎቹን የጥበብ ሥራዎች ለማትረፍ መቻሉን የከተማዪቱ የእሳት አደጋ ብሪጌድ አስታወቀ።
በቀውስ ለተዋጠችው ቬኔዝዌላ የተላከ የውጭ ዕርዳታ የጫነ የዓለምቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን አውሮፕላን የመጀመሪያውን አቅርቦት ይዞ ዛሬ ካራካስ ገባ።
ፎቶ ሪፖርታዥ - በደቡብ ሱዳን ላይ ከመከረው የቫቲካን መንፈሣዊ ጉባዔ የተወሰዱ ምስሎች። ይመልከቷቸው።
ኒውዚላንድ ውስጥ በቅርቡ የዓርብ ጸሎታቸውን ለማድረስ መስጊድ ውስጥ በተሰበሰቡ አማንያን ላይ የተፈጸመውን ጨካኝ ግድያ የሚያሳዩ በወቅቱ የተቀረጹ የቪዲዮ ቅጂዎች የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላላቸው ኩባንያዎች የማንቂያ ጥሪ ሆኗል።
ከሊቢያ የጠረፍ አደጋ ፍልሰተኞችን ያተረፈው የመድህን መርክብ ማቆሚያ ወደብ ፍለጋ ሲዘዋወር፤ 64 ከአደጋ የተረፉ ፍልሰተኞች የመጠጥ ውሀና የምግብ እጥረት እንደገጠማቸው የመርከቡ ባለሥልጣኖች አስታወቁ።
የአውሮፓው ህብረት ዋና ተደራዳሪ ማይክል ባርኒየር ብሪታንያ ከህብረቱ የምትወጣበት ሥምምነት ሳይደረግ ፍቹ ሊፈፀም ወደ ሚችልበት ሁኔታ እየተጠጋች ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭጥና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ባለፈው ዓመት በዓለም ዙሪያ ከ113 ሚልዮን በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ የምግብ እጥረት ማስከታላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።
የእንግሊዝን ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትሯ እጅ ለማውጣትና እራሳቸው ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ድምፅ የሃገሪቱ እንደራሴዎች ትናንት ምሽት ላይ ሰጥተዋል።
የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔተናሁ ፣ ጋዛ ሰርጥ ላይ በደረሰው የሮኬት ጥቃት ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ዛሬ ወዳገራቸው ተመለሱ። ድንገተኛ ቢሆንም ግን፣ ኔተናሁ ወዳገራቸው ከመመለሳቸው አስቀድሞ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ተገናኘው መወያየታቸው ታውቋል።
ዩክሬይን፣ ቀደም ብላ ባወጣችው ፕሮግራም መሠረት፣ በመጪው እሑድ አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ እየተዘጋጀች መሆኗ ተገለፀ። ሁለቱ ተፎካካሪዎች ደግሞ ከ2 ሳምንታት በኋላ ድጋሚ ምርጫ ያደርጋሉ።
የኢንዶኔዥያዋን ምስራቃዊ ፓፑዋ ክፍለ ሀገር በተከታታይ ለሦስት ቀናት በመታት ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሰማኒያ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የአጣዳፊ ዕርዳታ ባለሥልጣናት ገለጹ።
ተጨማሪ ይጫኑ