አዲሱ የማሌዥያ ንጉሥ ዛሬ በተደረገው የንግሥና ስነ ሥርዓት በትረ ሥልጣኑን በኦፊሴል ተረክበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚዋሰነው ድንብር ላይ ግንብ ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት ዛሬ በአዲስ መልክ አጠናክረውታል። የሀገሪቱ ምክር ቤት ለግንቡ የሚሆን ባጀት ባይመድብላቸውም እንኳን “በሆነው መንገድም ቢሆን” ይገነባል ብለዋል።
የብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን አስማልክቶ የሀገሪቱና የአውሮፓ ህብረት ተደራዳሪዎች ዛሬ የተለያየ አመለካከት አንፀባርቀዋል።
ኢራን የሳይበር ሥለላ ሥራዋን በማስፋት ዋና ዋና የፖለቲካና የቢዝነስ ባለሥልጣኖችን እንቅስቅሳሴ ለመከታተል የሚያስችላት መረጃ እየሰረቀች ይመስላል ይላሉ የዜና ዘገባዎች።
በዓለም ደረጃ ሙስናን የሚታገለው ቡድን እንደሚለው በፀረ ሙስና ጥረት ውስጥ ከፈረጃቸው ሀገሮች መካከል ዩናይትድ ስቴትስ በአራት ነጥብ ወደ ኋላ ቀርታለች ይላል። ዩናይትድ ስቴትስ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍተኛ ቦታ ከተሰጣቸው ሀገሮች ዝርዝር ወጥታለች።
የፓኪስታን ከፍተኛ ፍርድ ቤት “የእስልምናን እምነት ስም አጉድፋለች” በሚል በሀሰት የተከሰሰችውን ክርስትያን ሴት በነፃ መለቀቅን አፅድቋል፤ ለአስርት ዓመት በዘለቀ የፍርድ ሂደት፡፡
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሳዑዲ ተወልጅ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ አገዳደልን አስመልክቶ ከሚመረምረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍርድ ጠቢብ ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተነጋገረዋል። ቱርክ ዓለምቀፍ ምርመራ እንዲካሄድበት እየጠየቀች ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የምክር ቤት ተደራዳሪዎች በደቡባዊው የሀገሪቱ ድንበር ግንብ ለመገንባት የሚያስችል ሥምምነት ያቀርባሉ የሚለው ግምታቸው ከአምሳ ከመቶ ያነሰ መሆኑ ገልፀዋል።
“... አብይ አሕመድ ጥረቶቻቸው እንደሚሳኩላቸው የብዙዎች ተስፋ ነው ...” ሲል ፎረን ፖሊሲ ፅፏል።
ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱት መቼ እንደሆነ ለጊዜው አይታወቅም።
በቬነዝዌላ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ወጥተው ብዙ ደም ከመፋሰሱ በፊት ሰላማዊ ንግግር እንዲጀመር የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሚሼል ባሽሌ ጥሪ አቀረቡ።
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ ፖለቲካ አማካሪ ሮጀር ስቶን - ዛሬ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፣ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል።
በአፍጋኒስታን ለ17 ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት በፖለቲካ ድርድር ለማብቃት በዩናይትድ ስቴትስና በታሊባን መካከል ኳታር ውስጥ የሚካሄደው የሰላም ንግግር መቀጠል ትልቅ ተስፋ አሳድሯል።
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር ከለር ብላይንድነስ በመባል በሚታወቀውና ቀለምን የመለየት የተፈጥሮ ችሎታ ማጣት በሚያስከትል የዓይን ጤና ችግር ምንነት ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጂብ ታይፕ ኤርዶዋን - ከሩሲያው አቻቸው ከቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለመነጋገር በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።
የቀጣይ አራት ዓመታት እቅዳቸውን ለመንደፍ እየሞከሩ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ዓለም አሁን ከገጠማት ይበልጥ ውስብስብ ትርምስ ጋር ይጋፈጣሉ።
ታሊባን ትላንት ካቡል አቅራቢያ በሚገኝ ቁልፍ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 36 ሰዎች ተገድለው ሌሎች 58 መጎዳታቸውን የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት አረጋገጡ።
አንድ የሩሲያ ፍ/ቤት በሥለላ ወንጀል ለተከሰሰው አሜሪካዊ የዋስ መብት እንዳይሰጠው ከለከለ።
".. ሕልም አለኝ! አራቱ ትንንሽ ልጆቼ አንድ ቀን በቆዳቸው ቀለም ሳይሆን፤ በምግባራቸው የሚለኩባት አገር ውስጥ እንደሚኖሩ .. ዛሬ ሕልም አለኝ! .." ማርቲን ሉተር ኪንግ - እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ነሃሴ 28, 1963 ዋሽንግተን ዲሲ።
እሥራኤል፣ ሦርያ ውስጥ በሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ማካሄዷን ዛሬ በሰጠችው ቃል አመነች።
የታሊባን ተዋጊዎች ማዕከላዊ አፍጋኒስታን ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ የጦር ካምፕ ውስጥ ከባድ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታና የጠመንጃ ጥቃቶችን አካሂደው 18 የደኅንት አባሎች መቁሰላቸው ተገለፀ።
የፕሬዚደንት ትረምፕ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከነበረው ዕቅድ በብዙ ሺህዎች የሚበልጡ ፍልሰተኛ ህፃናትን ከወላጆቻቸው ሳይነጥል እንዳልቀረ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መርማሪዎች ይናገራሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮቿን ከሦርያ የማስወጣት ውሳኔዋ፣ ከፍተኛ የስትራቴጂክና ወታደራዊ ጠቀሜታን ያሳጣል ሲሉ ተንታኞች ተናገሩ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ሞስኮ ውስጥ የትረምፕ ህንፃ ለማቆም ስለነበራቸው ዕቅድ ጠበቃቸው ለምክር ቤት የሀሰት ቃል እንዲሰጡ አድርገዋቸዋል መባሉ ተዘገበ።
የቻይና የኢኮኖሚ ኃላፊ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሉሂ ለሁለተኛ የድርድር ዙር በያዝነው ወር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይጓዛሉ።
ተጨማሪ ይጫኑ