“በአንድ በኩል ሙሉ በሙሉ ኢሐዲግ፤ በሌላ በኩል ወደ ሥልጣኔ የመጡበት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ድባብ ለየት ያሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል። ኢሕአዲግን ካየን እስካሁን ለመላዋጥ መፈለጉን አላየሁም።” መስፍን ነጋሽ - ዋዜማ ራዲዮ።
“ኢሕአዲግ የፓርቲውና የአገሪቷ መጻኢ ዕድል ተለያይቶ እንዳይታይ ተደርጎ ስለሆነ ፖለቲካው የተሸረበው በፓርቲው ውስጥ የሚፈጠር ኮሽታ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው። እዛ ሁነት ውስጥ ሆነን ነው የምንመልለከተው።” ጸዳለ ለማ - አዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ፍን ነጋሽ።
“ግለሰቡ አብይ አሉ። ምናልባትም የኦሮሞ ብሔርተኛው አብይ አለ። የኦሕዲድ መሪ ሆኖ ኢሕአዲግ ውስጥ ባለው ትግል ራሱን አጉልቶ ለማውጣት የሚሞክረው ኢትዮጵያዊው አብይም አለ። .. የገመድ ላይ ጉዞ ነው። በጥሩ ጀምረውታል።” ሄኖክ የማነ - ከስቴት ኦፍ ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ።