አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ አንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ መኪና ላይ የጫነውን ቦምብ፣ የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት ወታደሮች የሚያጓጓዙ ተሽከርካሪዎች አጠገብ አፈንድቶ፣ አንዲት የሥድስት ዓመት ልጅ ሲገድል፣ ሌሎች ሃያ ሰዎች አቆሰለ። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ እስካሁን የለም።
“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር።
በዩናትድ ስቴትስ ታሪክ ከምንጊዜውም ቁጥሩ የበዛ ህይወት በጥይት የጠፋበት የፍሎሪዳው ትምህርት ቤት ከጥቃቱ የተረፉት ተማሪዎች ዛሬ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ኢራንን በየመን ሁቲ አማፁያን ላይ የተደነገገውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣስ የሚወነጅላት ውሳኔ እንዳይተላለፍ ሩስያ ማደናቀፏ ተዘግቧል።
የሳውዲ አረብያ ንጉሥ ሳልማን በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ስፋት ያለው የባለሥልጣናት ብወዛ አካሂደው አንዳንዶቹን ዋና ዋና ወታደራዊ መኮንኖችና ሚኒስትሮች ቀያይረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉተሪሽ በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ለ30 ቀናት ያህል እንዲቆም የጸጥታው ምክር ቤታ ያሳለፈውን ውሳኔ መንግስታት ባለመተግበራቸው ነቀፌታ አቅርበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የክፍላተ ሀገር አገረ ገዢዎች ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ በሚያካሂዱት ጉባዔ በቅርቡ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት የደረሰው ጥቃት ዋናው ትኩረት እንደሚሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን ሃገራቸው በሶሪያ አማፅያን ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ ሲቪሎች ዋና ከተማዋ ደማስቆ አቅራቢያ ውጊያው ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ማምለጥ እንዲችሉ በቀኑ ለአምስት ሰዓታት እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ተዘግቧል።
ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የሞተችው ዝነኛዋ የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር ሕይወቷ ያለፈው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መሆኑን የዱባይ ፖሊሶች አስታወቁ።
ኢንግላንዱዋ ሌሴስተር ከተማ አንድ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር እና የመኖሪያ ቤት ባወደመው ፍንዳታ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰዎች ቆስለዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለምቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ያወጣው ዓመታዊ ዘገባ ወደ 160 በሚጠጉ ሀገሮች ተፈፀመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ አስፍሯል።
ምሥራቃዊ ጎታ በተባለው ከደምስቆ ወጣ ብሎ በሚገኘው የተከበበ አካባቢ መንግሥት ከባድ የአየር ድብደባ ማካሄዱን ተቃዋሚዎች ገልፀዋል። በያዝነው ሳምንት በአካባቢው ተዳጋጋሚ የአየር ድብደባ ሲካሄድ ቆይቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጠመንጃዎች የከፋ ጉዳት እንዲያደርሱ የሚያደርጉ መሳርያዎች እንዲታገዱና በጠመንጃ ገዢዎች ላይ ጥብቅ የታሪክ ጀርባ ምርመራ እንዲደረግ ምክረ ሀስብ አቅርበዋል።
ዕውቁ አሜሪካዊ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ግራም ዛሬ በ99 ዓመት ዕድሜያቸው አረፉ።
በሶርያ የሚካሄደውን ጦርነት የሚከታተል ቡድን በገለፀው መሰረት የሀገሪቱ መንግሥት ከደማስቆ ወጣ ብሎ በሚገኘው በአማፅያን ቁጥጥር ሥር ባለው ምሥራቃዊ ጎታ ላይ ዛሬ ባካሄደው የአየር ድብደባ ቢያንስ 45 ሰዎች ተገድለዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ከሰሜን ኮርያ ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንዳላት እያመለከተች ነው።
ሩስያ የዩናይትድ ስቴትስን የፖለቲካ መድረክ ማተራመስ በደምብ አድርጎ ተሳክቶላታል ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ፡፡
ኢራን ውስጥ አይሮፕላን ተክሰክሶ ሥልሳ አምስቱም ተሳፋሪዎች አለቁ።
የአፍጋኒስታን የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል። ሁለተኛ የክፍለ ሀገር አስተዳዳሪ ሥልጣን እንዲለቁ ከፕሬዚዳንቱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ እምቢ ብለዋል።
እስራኤል እና ጋዛ ድንበር አጥር አቅርቢያ ትናንትና ቅዳሜ ቦምብ ፈንድቶ አራት የእስራኤል ወታደሮች ቆሰሉ። ሁለቱ በጽኑ መቁሰላቸው ተነገረ።
ቁልፍ ናቸው የተባሉ እነዚህ ስምምነቶች ሕንድ ቻባኻር የሚባለውን የኢራን ወደብ አገልግሎት ለመጭዎቹ 18 ወራት በኪራይ እንድትይዝ የሚፈቅዱን ውል እንደሚያካትቱ ተዘግቧል፡፡
በአንድ የፍሎሪዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ ከፍቶ፣ እስካሁን በታወቀው አኃዝ መሠረት፣ ለ17 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግለሰብ፣ ትናንት ሐሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ያለ ዋስ መብት በእስር እንዲቆይ ተወስኖበታል።
የእሥራኤል ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተነካክተውበታል በተባለ ሙስና ምክንያት ሥልጣን እንዲለቅቁ እየተጠየቁ ናቸው። ኔታንያሁ ክሦቹን እያጣጣሉ ናቸው።
በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገቡ ህፃናትን ከመባረር ለማዳን ያለው ዕድል እየጠበበ በመሆኑ፣ እልህ አስጨራሹ የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ህግ እንዲሻሻል የምክር ቤት አባላት መፍትሔ እንዲፈልጉ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አሳሰቡ።
የዩናይትድ ስቴትስንና የኔቶ የጦር አዛዦችን ጨምሮ፣ የአፍጋኒስታን አጎራባችና ክልላዊ ሀገሮች ወታደራዊ አዛዦች፣ አደንዛዥ እፅንና ሽብርተኛነትን መዋጋት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመወያየት፣ ዛሬ ማክሰኞ ካቡል ውስጥ ጉባዔ ተቀምጠዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ