በፔንሲልቬንያ ክፍለ ግዛት ከፒትስበርግ ወጣ ብሎ የሚገኘውን ወረዳ ወክሎ ለህግ መመሪያ ምክር ቤት አባልነት በተደረገው ልዩ ምርጫ ዲሞክራት ተወዳዳሪ ኮኖር ላምብ ማሸነፍቸውን ዛሬ ማለዳ ተናግረዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የሀገሪቱ ምክር ቤት መሳርያ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ አለመውሰዱን በመቃወምና በአንድ የፍሎሪዳ ትምህርት ቤት ላይ የተገደሉትን ተማሪዎች ለማሰብ ከትምህርት ቤቶቻቸው ወጥተዋል።
ብሪታንያ በሩስያ ላይ 23 ሩስያውያን ዲፕሎማቶች ማባረርን ያቀፈ የምላሽ እርምጃ መውሰድዋን አስታውቃለች። በሶቭየት ህብረት ዘመን የነበረ ለምት የሚዳርግ የነቭ ኤጀንት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ሰርገይ ስክሪፓልንና ልጃቸው ዩልያን ለመመረዝ እንዴት በብሪታንያዋ ሳልስበሪ ከተማ ሊደርስ ቻለ? ለሚለው ጥያቄ ሩስያ ምላሽ ባለመስጠትዋ ነው እርምጃው የተወሰደው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የህግ መምርያው ምክር ቤት ውሳኔ ንፁህነቴን አረጋጧል እያሉ ነው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከሥራ አስወግደው በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ የስለላ አገልግሎት /ሲአይኤ/ ሥራ አስኪያጅ ማይክ ፖምፕዮ እንደሚተኳቸው ታውቋል።
ከባንግላደሽ የተንሳ የመንገደኞች አይሮፕላን በኔፓል አይሮፕላን ማረፍያ ላይ ሊያርፍ ሲል ተከስክሶ ወድቆ በመፈንዳቱ ቢያንስ 40 የሚሆኑ ተሳፋሪዎች እንዳለቁ የኔፓል ባለስልጣኖች ገልጸዋል።
ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የተመድ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ወደ ምሥራቃዊቷ የሦርያ ከተማ ጉታ የሚሄደውን እርዳታ የጫኑ ካሜዎኖች ዛሬ ዐርብ መንቀሳቀሳቸው ተሰማ፤ ዳሩ ግን በአካባቢው የሚካሄደው የአየር ጥቃት በአስቸኳይ የተፈለገውን እርዳታ ማራገፍ እንዳላስቻለ ታውቋል።
በኢትዮጵያ የቅርብ ሴት ጓደኛማቾች በጋራ የመሰረቱት “safe house” በአማርኛ "ከለላ ቤት" የተሰኘው የግብረሰናይ ድርጅት የተጎዱ ሴቶች የሚያገግሙበት መጠለያ ነው።
ምሥራቃዊ አፍጋኒስታን ውስጥ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከሞቱት ሦስት ሰዎች አንዱ፣ ከፍተኛ የክፍለ ሀገር ባለሥልጣን መሆናቸው ተገለፀ።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የነበሩና ትምህርታቸውን በሀንጋሪ በመከታተል ላይ የሚገኙ ሰላሳ የሚሆኑ ተማሪዎች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለችግር እንደተጋለጡ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገለፁ።
ዊንድ አፕ ራድዮን ያፈለቁት እንግሊዛዊ ተመራማሪ ትሬቨር ባይሊስ በ80 ዓመት እድሜያቸው ትላንት አረፉ።
አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን እንደሚሉት የሚያንማር የጸጥት ሃይሎች በሰሜን ምዕራብ ራኺን ክፍለ-ግዛት የቀሩትን ሮሂንጋ ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት መርገጡን ቀጥለዋል።
ሩስያ እስካሁን ባለው ጊዜ ያነጋገረኝ ክፍል ባይኖርም በጸና ስለታመሙት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ ጉዳይ ከሚመረምሩት የብሪታንያ ባለልስጣኖች ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነኝ ብላለች። ሰውየው በጠና ታመው ሆስቲፓል የገቡት ምንነቱ ላልታወቀ ንጥረ ነግር ከተጋለጡ በኋላ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሀገራቸው ከውጭ በሚገቡት የብረት ምርቶች 25 ከመቶ በአሉሚኒየም ምርቶች ደግሞ 10 ከመቶ ቀረጥ ለመጣል በወሰደችው ውሳኔ እንደምትጸና ትላንት ተናግረዋል። የፖለቲካና የዲፕሎማሲ አጋሮች እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች አሜሪካ የንግድ ጦርነት ሊያስከትል የሚችል ፖሊሲን እንዳትከተል ጫና እያደረጉ ናቸው።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢራንን ወታደራዊ ለማጨንገፍ ስለሚቻልበት መንገድ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ለመነጋገር ዋሽንግተን ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲያነጋግር የሰነበተውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአነስተኛ ድምጽ ብልጫ በዛሬው ዕለት አጽድቋል።
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ አንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ መኪና ላይ የጫነውን ቦምብ፣ የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት ወታደሮች የሚያጓጓዙ ተሽከርካሪዎች አጠገብ አፈንድቶ፣ አንዲት የሥድስት ዓመት ልጅ ሲገድል፣ ሌሎች ሃያ ሰዎች አቆሰለ። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ እስካሁን የለም።
“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር።
በዩናትድ ስቴትስ ታሪክ ከምንጊዜውም ቁጥሩ የበዛ ህይወት በጥይት የጠፋበት የፍሎሪዳው ትምህርት ቤት ከጥቃቱ የተረፉት ተማሪዎች ዛሬ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ኢራንን በየመን ሁቲ አማፁያን ላይ የተደነገገውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በመጣስ የሚወነጅላት ውሳኔ እንዳይተላለፍ ሩስያ ማደናቀፏ ተዘግቧል።
የሳውዲ አረብያ ንጉሥ ሳልማን በመከላከያ ተቋሙ ውስጥ ስፋት ያለው የባለሥልጣናት ብወዛ አካሂደው አንዳንዶቹን ዋና ዋና ወታደራዊ መኮንኖችና ሚኒስትሮች ቀያይረዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉተሪሽ በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ለ30 ቀናት ያህል እንዲቆም የጸጥታው ምክር ቤታ ያሳለፈውን ውሳኔ መንግስታት ባለመተግበራቸው ነቀፌታ አቅርበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የክፍላተ ሀገር አገረ ገዢዎች ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ በሚያካሂዱት ጉባዔ በቅርቡ ፍሎሪዳ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት የደረሰው ጥቃት ዋናው ትኩረት እንደሚሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ።
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን ሃገራቸው በሶሪያ አማፅያን ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ ሲቪሎች ዋና ከተማዋ ደማስቆ አቅራቢያ ውጊያው ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ማምለጥ እንዲችሉ በቀኑ ለአምስት ሰዓታት እንዲቋረጥ ማዘዛቸው ተዘግቧል።
ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የሞተችው ዝነኛዋ የህንድ ቦሊውድ ተዋናይት ስሪዴቪ ካፑር ሕይወቷ ያለፈው ውሃ ውስጥ ሰጥማ መሆኑን የዱባይ ፖሊሶች አስታወቁ።
ተጨማሪ ይጫኑ