በከፍተኛው አምስት ደረጃ የሚለካ ሃሪኬን ኢርማ የተሰኛ ብርቱ ዝናብ የተቀላቀለበት ከባድ አውሎነፋስ ወደ ፍሎሪዳ እያመራ ነው።
የእሥራኤል የጦር አሮፕላኖች ዛሬ ሐሙስ በአንድ የሦርያ ወታደራዊ ይዞታ ላይ ጥቃት ማካሄዳቸውን የሦርያ ጦር ኃይል አስታወቀ።
ህንድ፣ ሙምባይ ውስጥ እአአ በ1993 ለደረሰውና ከ250 በላይ ሰዎች ላለቁበት ፍንዳታ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ፣ አንድ የህንድ ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ በየነባቸው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የየመን ሕዝብ የሚሰቃየው ሰው ሰራሽ በሆነው ከሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ነው አለ፡፡
በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ መጣል ወይም የተጣለውን ማጥበቅ፣ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ ያለውን ውጥረት እምብዛም አይቀንሰውም ሲሉ ሩስያና ቻይና አስታወቁ።
ቁጥራቸው ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በየዓመቱ ከፍተኛ ሥፍራ በሚሰጠው የሃጂ ኡምራ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ ይጓዛሉ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቴሌርሰን ሰሞኑን እርሳቸውና አንድ ሌላ ረዳት ለጋዜጠኞች የሰጧቸውን አስተያየት ተከትሎ በቅርቡ ከትራምፕ አስተዳደር ሊሰናበቱ እንደሚችሉ እዚህ በዋሺንግተን አካባቢ በስፋት እየተገረ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የምትደቀነውን አደጋ በሚመለከት “መልሱ መናገር አይደለም” ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ሰሜን ኮርያ ተጨማሪ ቦሊስቲክ ሚሳይል ለፍተሻ ከተኮሰች በኋላ ነው።
“የይሁዳ ከንፈር” ትሰኛለች፤ የሳምንቷ ምርጥ ግጥም በወጣቷ ገጣሚ ትዕግስት ዓለምነህ ናት።
ዛሬ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ታጣቂ ጥቃት አድርሶ በትንሹ አምስት ሰዎችን ሲገድል ሌሎች ዘጠኝ አቁስሏል።
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማለዳ በጃፓን አናት ላይ ያለፈ የሚሳይል ሙከራ አካሂዳለች።
ሃሪኬይን ሃርቪ በተባለው በከባድ ንፋስ ታዝሎ የሚወርድ ከባድ ዝናብ የዩናይትድ ስቴትስዋን የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ሂዩስተን ከተማ አካባቢ እና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛትም አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
“እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የምንኖር ሰዎች እንደ ብዛታችን እንደ ቁጥራችን ሃሳብ የምንለዋወጥባቸው መድረኮች ለምንድነው የሌሉን በሚል በማዘጋጀው የቴሌቭዥን ከምጋብዛቸው እንግዶች ጋር ዘወትር የምናነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው መነሻ የሆኑን” ሄለን መስፍን የፕሮግራሙ አዘጋጅ።
ሰሜናዊ ህንድ ውስጥ ሁለት ተከታዮቻቸውን ደፍረዋል ተብለው የተከሰሱ አንድ አወዛጋቢ የሆኑ መንፈሳዊ መሪ ላይ ፍርድ ቤት ወንጀሉን ፈፅመዋል ብሎ ብይን መስጠቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ብጥብጥ፣ ቢያንስ ሃይ ስምንት ሰው ተገደለ፣ ሌሎች ሁለት መቶ ሰዎች ቆስለዋል።
ከወደ ሜክሲኮ ባህረ ሰላጤ ከባድ ንፋስ ይዞት የሚነጉደው ከባድ ዝናብ ሀሪኬይን ሃርቪ ወደ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ጠረፍ አካባቢ እያመራ ነው።
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኛ የሺያዎች መስጊድ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ ሃያ ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለፁ። በዓርብ የፀሎት ሰዓት ላይ በደረሰው ጥቃት የተገደሉት ሁለቱ ፖሊሶች ሲሆኑ ከአርባ በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።
አንድ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣን በሶሪያ ራካ ከተማ ውስጥ “እሥላማዊ መንግሥት” በተባለው ነውጠኛ ቡድን የታገቱ 20 ሺህ ዜጎች ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አስጠነቀቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከግራና ቀኝ በመጣ ከፍተኛ ውርጅብኝ ውስጥ ናቸው። ይህም፣ በነጭ ብሔርተኞች ተዘጋጅቶ ባለፈው ቅዳሜ በሻርለትስቪል ቨርጂንያ ለተፈፀመው አመፅ ተጠያቂው ማን እንደሆን የሰጡትን አስተያየት በመለዋወጣቸው ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ቅዳሜ ቻርለትስቪል ቨርጂኒያ ከተማ ውስጥ የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑ ቡድኖች የጠሩት ሠልፍ፣ ተቃውሞ ገጥሞት በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ቅዳሜ በቨርጂንያ ክፍለ ግዛት በምትገኘው ሻርለትስቪል ከተማ ላይ ግጭት ከተከሰተ በኋላ አንድ ምስል ትዊተር ላይ አውጥተዋል። በማኅበራዊ ሚድያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ተወዳጅነት አትርፏል።
ዩናይትድ ስቴትስ የቨርጂንያዪቱ ሻርለትስቪል ከተማ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ የተነሣውን የሕይወት መጥፋት ያስከተለ ሁከት የጫሩትን ኔኦ ናዚዎችና የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑትን ኩ ክለክስ ክላን የሚባል ቡድን አባላት “ወንጀለኞችና ወንበዴዎች” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አውግዘዋቸዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮሪያ ላይ የጀመሩትን የብርቱ ቃላት ድብደባ ዛሬ ይበልጥ አጠንክረው ቀጥለዋል።
ኦገስት 21 / 2017 ዓ.ም. [ከአሥር ቀን በኋላ የፊታችን ነኀሴ 15፤ በወዲያኛው ሰኞ] ዩናይትድ ስቴትስን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያቋርጥ የፀሐይ ግርዶሽ ይኖራል።
ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ