የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዕሁድ ዕለት አዲስ የጉዞ ሕግ ስላወጡ፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞ የጉዞ ትዕዛዝቸውን ከመጭው ወር ፋይሉ ላይ አስወግዷል፡፡
“በሰሜን ኮሪያ ላይ ጦርነት አላወጅንም” ሲሉ በትላንትናው ዕለት ለጋዜጠኞች የተናገሩት የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሃከቤ ናቸው። “እንደ እውነቱ ከሆነ ያ አነጋገር መሠረተ ቢስ ነው” ብለዋል።
አፍጋኒስታን ውስጥ ላለው ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጦር፣ ዋይት ኃውስ አዲስ ስትራተጂ ይፋ ካደረገ ወዲህ፣ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡባዊ እስያን እየጎበኙ መሆናቸው ተገለፀ።
የሮሒንግያ "አማጽያን" ያቀረቡትን የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያንማር መንግሥት እንደማይቀበል አስታወቀ።
የኢራቅ ኩርዶች፣ በሰፊው ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ የነፃነት ውሳኔ ሕዝብ እያካሄዱ ሲሆን፣ ባግዳድ ያለውን መንግሥት ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮችና ከዩናይትድ ስቴትስ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል።
አፋጣኝ ዕርምጃ ካልተወሰደ በመጪዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ 6መቶ ሺህ ሕጻናት በረሃብና በበሽታ እንደሚረግፉ /ሴቭ ዘ ችልድረን/ አስጠነቀቀ።
ሜክሲኮን በመታው ከባድ ርዕደ ምድር የሞቱት ሰዎች ቁጥር 286 ደረሰ፣ ገና ያልተገኙ ስላሉ የሟቾቹ ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችልም ተገለጸ።
በህንድና ፓኪስታን ድንበር ባለው በአወዛጋቢው የካሽሚር ክልል ሌሊቱን በህንድ ፖሊሶች በተካሄደው የድንበር ተኩስ ልውውጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን የፓኪስታን ጦር አስታወቀ።
ባለፈው ሳምንት ለንደን ውስጥ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ በደረሰውና 20 ሰዎች ባቆሰለው የቦምብ ፍንዳታ፣ የእንግሊዝ ፖሊሶች ዛሬ ዐርብ በአንድ የ18 ዓመት ወጣት ላይ ክስ መሰረቱ።
የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሌላ የሃይድሮጂን ቦምብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ እንደሚሞክሩ ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ “እብድ” ሲሉ እንደተናገሯቸው ተሰማ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ በምትደቅነው የኑክሌር መሣርያ አደጋ ምክንያት አዲስ ማዕቀቦችን እንደሚጥሉ ገልፀዋል።
ሔሪኬን ማርያ “በእንቅርት ላይ፣ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ዛሬ ፕርቶሪኮ ላይ ከባድ ዝናብ አውርዷል። ቀደም ሲል የመላ ደሴቲቱ የኤለክትሪክ መብራት በሔሪኬኑ ምክንያት ጠፍቷል። ብዙ ቦታዎችን በጎርፍ አጥለቅልቋል። ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት ጠፍቷል።
ሜክሲኮ ላይ በደረሰው ከባድ ርዕደ ምድር ምክንያት በተደረመሱ ህንፃዎች ውስጥ የተቀበሩ ስዎችን ፍለጋ የመድህን ሰራተኞች ዛሬም ደፈ ቀና እያሉ ናቸው።
የብሪታንያ ፖሊሶች ባለፈው ሳምንት ለንደን በሚገኘው ባቡር ላይ ከተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ሁለት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን አሰሩ።
እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሃገራቸውን ከማንም በፊት እንደሚያስቀድሙ ሚስተር ዶናልድ ትረምፕ በድጋሚ አረጋገጡ።
ዩናይትድ ስቴትስ 3,000 ወታደሮች ወደ አፍጋኒስታን እየላከች መሆንዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ገልፀዋል።
ዶሚኒካ የተባለችው የካሪብያን ደሴት፤ “ማሪያ” የሚል ቅጽል በተሰጠው ሄሪኬን /ብርቱ ዝናብ የቀላቀለበት ከባድ አውሎ ነፋስ/ ክፉኛ ተጎድታለች።
“በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው ጥቃት ይቁም። ግድያዎቹ በገለልተኛ ወገን ይጣሩ።” ኢትዮጵያውያኑ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ምክር ቤቶች ያስገቡት ደብዳቤ።
የሚዙሪ ክፍለ ግዛት መዲና ሴንት ሉዊስ ፖሊሶች በከተማይቱ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ መስኮቶች በመሰባበራቸው ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን እንዳሰሩ ገልጸዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ህንፃ ጋር ትይዩ በሆነው ቦታ ላይ መኖርያ ፎቅ ለመሥራት ሲወስኑ ጠቃሚነቱን በመረዳት ነው ብለዋል።
የህንድ መንግሥት ከሚያንማር ሸሽተው ህንድ የገቡትን 40ሺህ የሚሆኑ ሮሂንጋዎችን ለማስወጣት ማቀዱን በመቃወም የተሰበሰቡ ፍርማዎች ለህንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቧል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ተመልክቶታል።
ለንደን ውስጥ ዛሬ ዓርብ ማለዳ ወደስራ የሚሄዱ ተጓዦች በታጨቁበት ባቡር ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አሥራ ሥምንት ሰዎች መጎዳታቸው ተገለፀ። ብዙዎቹ በተነሳው እሳት ተቃጥለው ነው። ፖሊሶች ድርጊቱን በሽብርተኛ ተግባርነት ፈርጀው እየመረመሩ ናቸው።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በሃይለኛ ዝናብ አዘል ማዕበል አርማ ወደተመታችው ፍሎሪዳ ክፍለ ሃገር ተጉዘዋል። በዚያም ስለተያዘው የመልሶ ማቋቋምና ጥረት ገለጻ ይደረግላቸዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።
በሁከት በታመሰችው የምሥራቅ አፍጋኒስታን ክፍለ ሃገር ኩናር ውስጥ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን ያገታቸውን ሁለት ሲቪሎች መቅላቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገለጡ።
ከሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ …..እንግሊዛዊው ፎቶ አንሺ ዴቪድ ስሌተር ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ቀን ካሜራውን እንደዋዛ ቁጭ አድርጎት ዞር ይላል።
ተጨማሪ ይጫኑ