የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በሃይለኛ ዝናብ አዘል ማዕበል አርማ ወደተመታችው ፍሎሪዳ ክፍለ ሃገር ተጉዘዋል። በዚያም ስለተያዘው የመልሶ ማቋቋምና ጥረት ገለጻ ይደረግላቸዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።
በሁከት በታመሰችው የምሥራቅ አፍጋኒስታን ክፍለ ሃገር ኩናር ውስጥ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን ያገታቸውን ሁለት ሲቪሎች መቅላቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገለጡ።
ከሰባት ዓመታት በፊት እንዲህ ሆነ …..እንግሊዛዊው ፎቶ አንሺ ዴቪድ ስሌተር ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ቀን ካሜራውን እንደዋዛ ቁጭ አድርጎት ዞር ይላል።
ኃይለኛ ዝናብ ቀላቅሎ በሚነፍሰው ሀሪኬን ኧርማ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የፍሎሪዳ ነዋሪዎች፣ ዛሬ ማክሰኞ ወደየቤቶቻቸው መመለስ መጀመራቸው ተሰማ።
በቅርቡ ሰሜን ኮሪያ ላይ የተጣለውን ዓለማቀፍ ማዕቀብ፣ የእስያ ሀገሮች በአዎንታዊ መልኩ ዕያዩት ሲሆን፣ ብዙዎቹ ግን፣ ተጨባጭ ውጤት ስለማስገኘቱ፣ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተገለፀ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሆፕ ሃይኪስን፣ የዋይት ኃውስ ቋሚ የኮሚኒኬሽንስ ዳይሬክተር አድርገው እንደሾሟቸው፣ ከቤተ መንግሥታቸው የወጣው መግለጫ አመለከተ።
መስከረም አንድ በአሜሪካዊያን ዘንድ በከበደ ኀዘን ታስቦ የሚውል ቀን ነው። ልክ የዛሬ 16 ዓመት መስከረም 1994 ዓ.ም. በበረራ ቁጥር 77 የተመዘገበ የአሜሪካን ኤይርላይንስ አይሮፕላን ተሣፍረውበት ከነበሩ 59 መንገደኞች ጋር ተጠልፎ የዩናይትድ ስቴትስ የመከለከያ ሚኒስቴርን መታ። ያኔ ፔንታገን ውስጥ የነበሩ 125 ሰዎች ተገደሉ።
ሰሜን ኮሪያ እያካሄደች ባለው የሚሳይል ሙከራና የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ፕሮግራሟ ምክንያት ማዕቀብ እንዲጣልባት፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ድምፅ የሚያሰጥ ውይይት እንደሚያካሂድ ተገለፀ።
አፍጋኒስታን ውስጥ፣ አንድ አጥፍቶ ጠፊ፣ ቦምብ የያዘች መኪናውን፣ ከአንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ ወታደራዊ ተሸርካሪ ጋር ዛሬ በማላተም፤ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የውጪ አገር ወታደሮችና የአፍጋኒስታን ሲቪሎች ማቁሰሉን፣ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፣ እአአ በ2001 ዓ.ም የዛሬ 16 ዓመት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተለይም ኒው ዮርክና ዋሽንግተን ላይ በደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት የሞቱትን የሚያስታወስ የጸሎት መርሐ ግብር መምራታቸው ተነገረ።
አሸባሪው ቡድን አልሻባብ ጥቃት ለማድረስ በመዛቱ፣ አሜሪካውያን ወደ ኬንያና ሶማልያ ድንበር አካባቢ እንዳይጓዙ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
ኢርማ በመባል የተሰየመው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎነፋስ ዛሬ ሰኞ ወደ ቀላል ማዕበል ተለውጦ ሰሜን ፍሎሪዳና ደቡባዊ ጆርጂያን ማዳረሱ ተሰማ።
በከፍተኛው አምስት ደረጃ የሚለካ ሃሪኬን ኢርማ የተሰኛ ብርቱ ዝናብ የተቀላቀለበት ከባድ አውሎነፋስ ወደ ፍሎሪዳ እያመራ ነው።
የእሥራኤል የጦር አሮፕላኖች ዛሬ ሐሙስ በአንድ የሦርያ ወታደራዊ ይዞታ ላይ ጥቃት ማካሄዳቸውን የሦርያ ጦር ኃይል አስታወቀ።
ህንድ፣ ሙምባይ ውስጥ እአአ በ1993 ለደረሰውና ከ250 በላይ ሰዎች ላለቁበት ፍንዳታ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሁለት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ፣ አንድ የህንድ ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ በየነባቸው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የየመን ሕዝብ የሚሰቃየው ሰው ሰራሽ በሆነው ከሁለት ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ነው አለ፡፡
በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ መጣል ወይም የተጣለውን ማጥበቅ፣ ባሕረ ሰላጤው አካባቢ ያለውን ውጥረት እምብዛም አይቀንሰውም ሲሉ ሩስያና ቻይና አስታወቁ።
ቁጥራቸው ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በየዓመቱ ከፍተኛ ሥፍራ በሚሰጠው የሃጂ ኡምራ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ መካ ይጓዛሉ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪክስ ቴሌርሰን ሰሞኑን እርሳቸውና አንድ ሌላ ረዳት ለጋዜጠኞች የሰጧቸውን አስተያየት ተከትሎ በቅርቡ ከትራምፕ አስተዳደር ሊሰናበቱ እንደሚችሉ እዚህ በዋሺንግተን አካባቢ በስፋት እየተገረ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የምትደቀነውን አደጋ በሚመለከት “መልሱ መናገር አይደለም” ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ሰሜን ኮርያ ተጨማሪ ቦሊስቲክ ሚሳይል ለፍተሻ ከተኮሰች በኋላ ነው።
“የይሁዳ ከንፈር” ትሰኛለች፤ የሳምንቷ ምርጥ ግጥም በወጣቷ ገጣሚ ትዕግስት ዓለምነህ ናት።
ዛሬ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ታጣቂ ጥቃት አድርሶ በትንሹ አምስት ሰዎችን ሲገድል ሌሎች ዘጠኝ አቁስሏል።
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ማለዳ በጃፓን አናት ላይ ያለፈ የሚሳይል ሙከራ አካሂዳለች።
ሃሪኬይን ሃርቪ በተባለው በከባድ ንፋስ ታዝሎ የሚወርድ ከባድ ዝናብ የዩናይትድ ስቴትስዋን የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ሂዩስተን ከተማ አካባቢ እና በሉዊዚያና ክፍለ ግዛትም አንዳንድ አካባቢዎች በከባድ ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ