የዓለም ምጣኔ ሀብት ካለፈው ዓመት በተሻለ ዕድገት ይቀጥላል ሲል፤ የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ /IMF/ የምጣኔ ዕድገት ትንበያ አስታወቀ።
በመላው ዓለም ክርስትያኖች ዕለተ ስቅለትን ዛሬ አክብረው ውለዋል፡፡
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በአሁኑ ወቅት ሞስኩ ይገኛሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሌሊት በአንድ የሶሪያ የአየር ኃይል መደብ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የአውሮፓ አጋሮቿ ሲደግፉ ሩሲያ የወረራ አድራጎት ነው ስትል አውግዛዋለች፡፡
የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች የ አሥር ሣምንቱ ወጣት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር እጅግ ደካማ መሆኑን ያሳያሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሽብር ፈጠራንና ፅንፈኛ የሁከት ቡደኖችን ለማሸነፍ ግብፅ ለምታደርገው ጥረት አስተዳደራቸው ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታውቀዋል፡፡
የቱርክ አትሌቶች ኤልቫን አብይ ለገሠ እና ጋምዜ ቡሉት የተከለከለውን አበረታች መድሃኒት በመጠቀም ከውድድሮች ታገዱ።
አል ሻባብ የኢትዮጵያ ጦር ይገኝባት የነበረችውን ኤል ቡርን ያለውጊያ ተቆጣጠረ፡፡
የምግብ ዋስትናን በዓለም ዙሪያ ማረጋገጥ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ጉዳይ መሆኑ ላለፉት ሁለት ቀናት መጋቢት 20 እና መጋቢት 21 / 2009 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡
ጆአኪም ደመር ይባላል። ስዊድናዊ የዶክሜንትሪ ወይም የዘጋቢ ፊልም ሠሪ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳማዊት እመቤት ሜለኒያ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ባዘጋጀው የ2017 ዓ.ም. ዓለምቀፍ የጀግና ሴቶች ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
የዓለም ሚቲኦሮሎጂ ቀን መጋቢት 14 “ደመናን መረዳት” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ምንም እንኳ ዓለምቀፍ ማዕቀብ ቢጣልባትና እንድትገለል ቢደረግም፣ የጦር መሣሪያ ለመግዛትና የጋራ መከላከያ ስምምነት ለመፈራረም፣ ፍላጎት ያላቸው በርካታ የአፍሪካ ሀገሮችን ሽርክና ማግኘት ችላለች ይላል፤ ምርመራውን ያካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ባለሞያዎች ቡድን።
ካሁን በሁዋላ ከስማርት ፎን የተለቁ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሁሉ ወደ አውሮፕላን የሚገቡት ተመርምረው ይሆናል ተብሏል።
ስለዚህ ጉዳይ ኋይት ሃውስ መልስ እንዲሰጥ ቪኦኤ ጠይቆ ምላሽ አላገኘም።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ይፋ ያደረጉት የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት በሃገር ውስጥም፣ በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም እያነጋገረ ነው፡፡
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባይታወጅ ኖሮ የት ነው የሚቆመው አመጹ? የት ነው ጋብ የሚለው ነገር በጣም አጠያያቂ ነው የነበረው።” አቶ አታክልት አምባዬ። “የአስቸኳይ ጊዜውን አዋጁን ያወጁትም ሰዎች መፍትሔው እንፈልጋለን መፍትሔ አልተፈለገም። መፍትሔው ምንድ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለው ነገር ላይ ውይይት አላየንም።” አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “አሜሪካ ትቅደም” በጀታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
“በተለያዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሂደቶች አልፈው ጉዳያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነገር ግን ወንጀል ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ከአገር ያልተባረሩ፤ በዓመት ወይ በስድስት ወር አንዴ ወደ ኢሚግራሽን መሥሪያ ቤት እየፈረሙ በሰላም የመሚኖሩ .. ለእነኚህና ለሌሎች አሁን አሳሳቢ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር።
በቱርክና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በአህጉሪቱ ውስጥ ባለው የስደት ጉዳይ ላይ አሳሳቢ ጥላ እንዲያርፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡
“የልብ ትርታ መረበሽ ብዙውን ጊዜ ያንን ያህል ለጤና የሚያሰጋ ነገር የለውም። ምን ሊሆን ይችላል በሚል ግለሰቡን ማሳሰቡ ነው። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተደጋግሞ ሲመጣ፥ ከእርሱ ጋር ተያይዞም የትንፋሽ ማጠር እና ደረት ላይ ጫና በሚሰማበት ጊዜ ግን ሌላ ክትትል ሊያስፈልገው ይችላል።” ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሕክምና ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ናቸው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከእርሣቸው የቀደሙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “በምርጫው ወቅት ኒው ዮርክ በሚገኘው ሕንፃዬ ላይ የስልክ መሥመሮቼን ጠልፈው ይሰልሉኝ ነበር” ሲሉ ላሰሙት ክሥ ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ማስረጃ እንዲያቀርብ ግፊቱ አሁንም እንደበረታ ነው፡፡
ጠቅላላው የሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ሥርዓት በሽብርተኛነት፣ በመጤ ጠሎችና ዝናን ናፋቂ በሆኑ ፖለቲከኞች፣ ከፍተኛ ጥቃት ሥር ወድቋል ሲሉ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን አስገንዝበዋል።
ክፍፍል የሚታይባት ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካዊ የተሃድሶ መንፈስ እንድትይዝ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ አሳስበዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ