ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ ሃይ ሥድስት ሰው ገድሎ ሌሎች ከሃያ በላይ ያቆሰለው የሃይ ስድስት ዓመት ዕድሜው ዴቪን ኪሊ ጥቃቱን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው የቴክሳስ ባልሥልጣናት ክትትል ይዘዋል።
“በደርግ አባልነቴ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች፥ በእነርሱም አማካኝነት ለመላው ኢትዮጵያውያን ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “አቶ እሸቱ፥ ዛሬም ‘ይህን በደል ፈጽሜያለሁ’ ሲሉ ወንጀሉን አላመኑም። በጸጸትም የተዋጡ ሰው አይደሉም።” አቶ ዓለሙ ጥሩነህ በጊዜው በእስር ቤት እንግልት ከደረሰባቸውና ከሞት የተረፉ ከዛሬው ሰባት ምሥክሮች አንዱ።
“የያዛችሁት የተሳሳተ ሰው ነው። “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “ወንድሜና ሌሎች በጊዜው ታስረው የነበሩት ወጣቶች እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጡት አቶ እሸቱ ስለመሆናቸው በፊርማቸው ያዘዙበትን ጨምሮ ብዙ ማስረጃ ተገኝቷል።” አቶ አብረሃም ብዙነህ ከከሳሽ አቃቤ ሕግ ምሥክሮች አንዱ።
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ በተከራየው የዕቃ መጫኛ መኪና ሥምንት ሰዎችን ሆን ብሎ ገጭቶ በመግደል የተወነጀለው የኡዝቤክሳታኑ ተወላጅ በሞት መቀጣት አለበት በሚለው አቋማቸው ፀንተዋል።
የሚያንማር መሪ ኡን ሳን ሱ ቺ ወደ ታወከው የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍለ ሃገር ራኺኔ ተጉዘዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ጧት በትዊተር መልዕክታቸው፣ ትናንት ማክሰኞ በኒው ዮርኩ ማንሃተን ሥምንት ሰዎችን በመኪና ገጭቶ የገደለው የኡዝቤክ አጥቂ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የገባው በዲቪ/በግሪን ካርድ/ ነው ሲሉ አስታወቁ።
አውስትራልያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የስደተኞች ማቆያ እስር ቤት ውስጥ የሰፈሩ ከ600 በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የአካባቢው ኗሪዎች ያስነሱብናል የሚሉትን አመፅ በመፍራት ከካምፑ ውስጥ አንወጣም ማለታቸው ተገለፀ።
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኙ የዲፕሎማቲክ መኖሪያ አካባቢዎች የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ስምንት ሰዎች ገድሎ ሌሎች አያሌ ማቁሰሉን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ሰሜናዊ ኩርዲስታን ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይደር አል አባዲ ተማፀኑ።
ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ የሳህል አካባቢ ሀገሮች ለሚያካሂዱዋቸው ፀረ ሽብርተኛ ጥረቶች መርጃ 60ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ቃል ገባች።
በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ያለውን የካርቦን ልቀት መጠንና የኃይል አጠቃቀም የተመለከተ አውደ ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡
የኢራቅ ኃይል የኢራቅ ወታደራዊ ኃይል “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” በሚለው ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን ቁጥጥር ሥር ያሉትን የመጨረሻ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ጥቃት ከፍቷል።
በሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመት እውነት ይሄ ይሆናል? ሊያሰኝ ይችላል። በዓለም ዙሪያ በሚያስገርም ቁጥር ሰው እንደጉድ ይሸጣል፣ ይገዛል፡፡
የካታላን ክልል ፕሬዚዳንት ካርለስ ፒዩጅሞንት የምክር ቤት አባላት የካታሎኒይ የራስ አስተዳደር ቦታን ለመቀልበስ በሰነዘሩት ዛቻ የሚገፉ ከሆነ የስፔን መንግሥት የካታሎኒያ ክልል ለነፃነት ከሚያካሄደው ዘመቻ ጋር የተያያዘውን የፖለቲካ ቀውስ ያባብሳል ብለዋል።
የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ለቋሚ የፖሊት ቢሮ ኮሚቴ የአዲስ አመራር ዝርዝር ይፍ አድርጓል። ፖሊት ቢሮ በዓለም ሁለተኛዋ ትልቅ ኢኮኖሚ በሆነችው ሀገር የበላይ አመራር ነው።
የፊሊፒንስ መከላከያ ሚኒስትር ደለፊን ሎረንዛና ማራዊ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ በአማፅያን ላይ ሲካሄድ የቆየው የአምስት ወራት ውጊያ አብቅቷል ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል።
በያዝነው ወር ለኒጀር ውስጥ የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት የሟቹን ባለቤትዋን ስም “ላ ዴቪድ ጆንሰንን ለማስታወስ ሲንተባተቡ በመስማቴ የባሰ እንዳልቀስ አድርጎኛል” ስትል ዛሬ ተናግራለች።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በአፍጋኒስታን በአካሄዱት አስቀድሞ ያልተገለፀ ጉብኝት ከሀገሪቱ መሪዎች ጋር ስለ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ የደቡብ እስያ ስትራቴጂ ተነጋግረዋል።
ዝምታቸውን በመስበር አደባባይ የወጡት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ፣ በሀገሪቱ የሚታየውን ፖለቲካዊ ወገንተኛነትና አድልዎ አጋለጡ።
ከጊዜ ወደጊዜ ሥልጣናቸው እየፈረጠመ የሄደው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ኮሙኒስት ፓርቲው ሕዝብ ለሚያቀርባቸው ጥያቂዎች ዲሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ለሚደረጉ ጥሪዎች በተሻለ ምላሽ እንዲሰጥ አደርጋለሁ ሲሉ ቃል ገቡ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ አርብ ወደመካከለኛው ምሥራቅ ይጓዛሉ። ሚኒስትሩ የሳውዲ አረብያና የኢራቅ መንግሥታት በሚያካሂዱት ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ይገኛሉ። የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ መንገዶችን ይፈትሻሉ።
የሰሜን ኮሪያ መንግሥት ላለፉት አሥርት ዓመታት ካዝናውን ለመሙላት ሲተማመን የቆየው፣ በሕገወጥ ንግድ በሚያገኘው ገንዘብ ላይ ነበር።
ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚከለክለው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ እገዳ፣ በሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መሻሩ ይታወቃል።
የስፔን መንግሥት ካታሎኒያን ራስ ገዝ አስተዳደርዋን የሚገፍፍ ዕቅድ ማውጣቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
እአአ ጥቅምት 16 የዓለም የምግብ ቀን ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ