“ለሃገሩ ራሱን የሰጠ ወታደር እንጂ ለቡድን የሚሰጥ መሆን የለበትም። ፖለቲካ ሌላ ነው ወታደር ሌላ ነው። በግልጽ መለየት አለባቸው። ይሄ ሁኔታ ነው ለሃገርም የሚጠቅመው። ነገር ግን ከፖለቲካ ጋር ወታደሩ ወዲህ ወዲያ የሚሄድ ከሆነ የሃገር ጥበቃ ትክክል አይመጣም።የጃንሆይም የደርግም ወታደር አልነበርኩም አሁንም ከዚህኛውም ጋርም ግንኙነት የለኝም።” ብርጋዲየር ጀነራል አሸናፊ ገብረ-ጻድቅ ከዘንድሮው “የጀግኖች ቀን” ተሸላሚዎች አንዱ።