በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አደራዳሪነት በየመን ተፋላሚ ወገኖች መካከል ለሰኞ ተይዞ የነበረው የሰላም ድርድር ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተዘገበ። በኩዌት በዛሬው እለት ሊጀመር ታቅዶ የነበረው የመናዊ-ከየመናዊ የተባለው የሰላም ድርድር በየመን የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ኢስማኢል ኦላድ ቼክ አህመድ ማብራሪያ፤ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በተከሰቱ ሁኔታዎች ሳቢያ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። የምክኒያቶቹን ተጨባጭ ምንነት ግን ልዩ መልዕክተኛው አልዘረዘሩም።