የእግርኳስ ኮከብ ተጫዋቾች የኢቦላን ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የሚካሄደውን አለምአቀፍ ዘመቻ ተቀላቀሉ።
G20 በመባል የሚታወቁት የአለም ከበርቴ ሀገሮች መሪዎች በሳምንቱ ማብቂያ ከህዳር 6 እስከ 7 በ Brisbane ተገናኝተው በምጣኔ ሃብትና ልማት እድገት ላይ ለመነጋገር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፥ አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ ተጠቃሚ ትሆናለች ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
ፊሌ ተብላ የተሰየመች ንብረትነቷ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ የሆነ መንኩራኩር ሕዋ ውስጥ ከምትገኝ አንዲት ቀደም ብላ ከተላከች የአውሮፓ ኅብረት ማምጠቂያ መደብ ተወንጭፋ በልማድ “ጅራታም ኮከብ” እየተባሉ ከሚጠሩ የተፈጥሮ የሰማይ አካላት ወይም ኮሜቶች በአንዷ ላይ አረፈች፡፡
ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ወደ ከባቢ አየር የሚለቅቋቸውን በካይና ሙቀት አማቂ ጋዞችን መጠን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ አዲስ ዕቅድ ይፋ አደረጉ፡፡
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ አለምአቀፍ የማራቶን ሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል። ፍቃዱ ግርማና ሙሉሀብት ጸጋ በቤይሩት፥ ሹሜ ሀይሉ በፈረንሳይ አሸንፈዋል። ጊዜአቸውም የፍቃዱ 2 - 12 - 26 እና 2- 29 - 15 ተመዝግቧል። በፈረንሳዩ የአልፕስ ማራቶን ደግሞ የወንዶቹን ሹሜ ሃይሉ በአንደኝነት አጠናቋል።
“በዚህ ኃላፊነት ላይ ከተቀመጥኩ ጊዜ ጀምሮ በየወሩ ማለት በሚቻል ፍጥነት ወደ አዲስ አበባ እመላለሳለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ሁለታችንም ከፕሬዚዳንት አብዱል-ፈታህ ኤል-ሲሲና ከወንድማቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በየጊዜው መገናኘታችንን ጠንክረን እንድንቀጥል፣ የግንኙነታችንን መንፈስም ይዘን እንድንጓዝ በተቀበልነው መመሪያ መሠረት ነው፡፡” - ሳምሃ ሹክሪ - የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረው በተመስገን ደሣለኝ ላይ የተላለፈው የእሥራት ፍርድ እንደሚያሳስበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አስታወቀ፡፡
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ሳምንቱን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ኤርትራ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ድምጽ ተሰማና ኢቦላን በሚመለከት ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ ሊኖር እንሚችል ተገለጸ የሚሉ ዘገቦች ይገኙባቸዋል።፣
“አንድ ሰው በፖሊስም ሆነ በሌላ የሕግ አስፈጻሚ አካል ለሚቀርብለት ጥያቄ፤ ካልፈቀደ በስተቀር መልስ ያለመስጠት መብት አለው።” አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶ፤ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያ።
ከተከሳሹ የኅግ ጠበቃ አቶ ደረጀ ሰምሴ ቡልቶ ጋር የተካሄደውን ከዚህ ያድምጡ።
ማስተካከያ፡ ቀደም ሲል "ኢትዮጵያ ወደ ምዕራብ አፍሪካ በጎ ፍቃደኞችን ልካለች" ተብሎ የወጣው የዜና ርዕስ እና መልዕክት "ኢትዮጵያ በጎ ፍቃደኞችን ወደ ምዕራብ አፍሪካ ልትልክ ነው" በሚል እንዲስተካከል ከይቅርታ ጋር እንጠይቃለን፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ