በባህር ዳር ከተማ አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ምንነት ግራ እንዳጋባቸው ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።
ዴሞክራሲ በተግባር
በሐረሪ ክልል የሚገኝ የማኅበረሰብ የትምህርት ተቋም በይዞታው ውስጥ በሚፈፀም ህገወጥ የመሬት ወረራ የተነሳ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመር አልቻልኩም አለ።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዛሬ በተጀመረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ንግግር አድርገዋል።
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡ ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገርም ትክክል አይደለም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡ የተወሰ ጊዜም እንደሚወስድ ይታወቅ እንደነበርም አብራርተዋል፡
የአዲስ አበባ መስተዳደር በዘንድሮ የትምህርት ዓመት ከመዋዕለ-ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ በ415 ት/ቤቶች ለሚገኙ 300,000 ተማሪዎች የምገባ መርሃ-ግብር አዘጋጀቷል፡፡
የሚነሱ ቅሬታዎች ሚዛናዊነትን፥ የጋራ እሴቶቻችንንና መርኆችን በጠበቀ መንገድ መቅረብ አለባቸው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ መክረዋል።
ላለፍት 7 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረውን ፀሎተ ምህላ ያጠናቀቁት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምዕመናን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ይፈፀማሉ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ዙሪያ ከቤተክርስቲያንቷ ጋር በሃዋሳ ከተማ መከሩ።
ላለፉት ሦስት ወራት በነቀምቴ ኩምሳ ሞረዳ ቤተ መንግሥት ታስረው የሚገኙ ግለሰቦች እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እንዳሳሰባቸው ከቤተሰቦቻቸው መካከል አንዳንዶቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል::
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊና ለፍትኅ ፓርቲ/ኢዜማ/ በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የድጋፍ ማኅበር መቋቋም መጀርመሩን አስታወቀ፡፡
በድሬዳዋ በሦስት ቀበሌዎች የሚኖሩና በጣም ዝቅተኛ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ከ15ሺ በላይ ነዋሪዎች ከያዝነው ወር ጀምሮ የምግብ ዋስትና ተጠቃሚ መሆን ይጀምራሉ።
አፍሪካውያን ልጆች በባሰ መልኩ ወደ ኋላ እየቀሩ በመሆናቸው እአአ እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ወይም በ 11 ዓመታት ውስጥ በዓለም በድኅነት ከሚኖሩት ሰዎች ከግማሽ በላይ ይሆናሉ ሲል አንድ አዲስ ዘገባ ጠቁሟል።
በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በተደረገ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በግድቡ ውኃ አሞላል ሂደት ላይ ከሦስቱም ሀገሮች በሚቀርቡ ሃሳቦች ላይ በተከታይ ዙር ለመነጋገር ተስማምተው ተለያይተዋል።
በምሥራቅ ሃረርጌ ዞን ጎሮጉቱ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ 10 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የምሥራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።
ከከፋ ህዝብ የምንማረው ብዙ ነገር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አካባቢውን መጠበቁን እና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ማኖሩን አድንቀዋል፡፡
ካለፉት 19 ዓመታት ወዲህ በድሃ ሀገሮች ሳይቀር የኑሮ ሁኔታ የተሻለ ቢሆንም በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዕኩልነት በጎደለው ኑሮ እንደሚገኙ አንድ አዲስ ዘገባ ገልጿል።
“ኢትዮጵያን የማሳነስ ልምምድ ለልጆቻችን አናወርስም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደዚሁም የተለያዩ ሃይማኖቶች አገር መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው ሁሉም ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቅ ሃገር ለመገንባት እንደሚሠራም አብራርተዋል።
በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ማታ መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በየክልላችሁ ተዋልደውና ተጋምደው የሚኖረውን የአማራ ህዝብ፣ በቆየው ኢትዮጵያዊው የመፈቃቀር መንፈስ አቅፋችሁ ኑሩ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ ክልል የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ በአካባቢው የነገሰው የፖለቲካ ውጥረት ለክልሉ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ መሆኑ ይታመናል።
ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሁለት የረድዔት ሠራተኞች የተገደሉበትን ከአንድ ሣምንት በፊት የተፈፀመውን ጥቃት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አውግዟል።
ተጨማሪ ይጫኑ