በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በተደረገ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በግድቡ ውኃ አሞላል ሂደት ላይ ከሦስቱም ሀገሮች በሚቀርቡ ሃሳቦች ላይ በተከታይ ዙር ለመነጋገር ተስማምተው ተለያይተዋል።
በምሥራቅ ሃረርጌ ዞን ጎሮጉቱ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ 10 ሰዎች ሲሞቱ 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የምሥራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።
ከከፋ ህዝብ የምንማረው ብዙ ነገር አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አካባቢውን መጠበቁን እና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ ማኖሩን አድንቀዋል፡፡
ካለፉት 19 ዓመታት ወዲህ በድሃ ሀገሮች ሳይቀር የኑሮ ሁኔታ የተሻለ ቢሆንም በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ዕኩልነት በጎደለው ኑሮ እንደሚገኙ አንድ አዲስ ዘገባ ገልጿል።
“ኢትዮጵያን የማሳነስ ልምምድ ለልጆቻችን አናወርስም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ። ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንደዚሁም የተለያዩ ሃይማኖቶች አገር መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው ሁሉም ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቅ ሃገር ለመገንባት እንደሚሠራም አብራርተዋል።
በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች ትናንት ማታ መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በየክልላችሁ ተዋልደውና ተጋምደው የሚኖረውን የአማራ ህዝብ፣ በቆየው ኢትዮጵያዊው የመፈቃቀር መንፈስ አቅፋችሁ ኑሩ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል።
በደቡብ ክልል የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ በአካባቢው የነገሰው የፖለቲካ ውጥረት ለክልሉ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ መሆኑ ይታመናል።
ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሁለት የረድዔት ሠራተኞች የተገደሉበትን ከአንድ ሣምንት በፊት የተፈፀመውን ጥቃት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አውግዟል።
የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተለያዩ አካላት መስከረም 4/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ የጠሩትን ሰላማዊ ሰልፍ ለሌላ ጊዜ ማስተላለፋቸውን አስተባባሪው ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
የተሻለ እንጂ የከፋ ዘማን ተመልሶ እንዳይመጣ እውነተኛ ሽግግር ለልጆቻችን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡
“ሀገርቀፍ መድረክ ህገ መንግሥቱንና ህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስረዓቱን ለማዳን” በሚል ስያሜ በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ለሁለት ቀናት ያህል ሰፊ ስብሰብ ተደርጎ ውይይት መካሄዱ የሚታወስ ነው።
1441ኛው የዓሹራ በዓል በአል-ነጃሺ መስጂድ ትናንት ተከብሯል።
አዲሱን ዓመት ምክንያት በአማራ ክልል ከ4ሺ በላይ ታራሚዎች እንዲለቀቁ ተወስኗል።
የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ከመስከረም 9 - 22/2012 ዓ.ም የሚቆይ የዕርቅ ሳምንት አወጁ።
ዜጎቿ የሚፈልጓትን ሀገር ለመገንባት ቁልፉ ያለው እየተወሰዱ ባሉ የማሻሽያ ዕርምጃዎች ላይ መሆኑን ከመቼውም ጊዜ በላይ አምናለሁ ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬነር አስታወቁ፡፡
65 እንሆናለን የሚሉ ፓርቲዎች በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አፋኝ ነው በማለት በሥራ ላይ እንዳይውል ጠየቁ፡፡
በጅማ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ሰሞኑን በተከሰተ በሽታ ሕይወት ማለፉን አንዳንድ የመጠለያው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በመጭው 2012 ዓ.ም. "ከመንግሥት የፀጥታ አካላት ውጭ የታጠቀ አካል በኦሮምያ ክልል አይኖርም" ሲሉ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአዲስ አመት በዓልን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሃረር አከበረ።
"ችግሮችን ስናስብ ወደ መቆም ነው የምንሄደው። .. መቆም መልስ አይደለም። ሁልግዜ ችግሮች አሉ። ችግሮችን ለመፍታት መሞከር ነው። አንዴ ተፈጥረናል በዚህ ምድር ላይ ባየነው ነገር ላይ በሁለት እግር ቆመን .. እንፈታዋለን ብለን መሞከር" አቶ ክብረት አበበ የኢትዮጵያ ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት።
የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ተዘዋውረው የቺኩንጉንያ ታማሚዎችን አይተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በደቡብ አፍሪካ ከሚኖሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ተወያዩ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ