ከቤኒሻንጉል ጉምዝ በሎ ጃገንፎይና ሶጌ ወረዳዎች ተፈናቅለው በነቀምቴ ከተማ ሠፍረው የሚገኙ ቪኦኤ ያነጋገራቸው አንዳንድ ተፈናቃዮች - መንግሥት ዘላቂ መፍትሄ ይስጠን እያሉ ነው።
"ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ያላትን የተፈጥሮ ሃብት አስተባብሮ መምራት የሚችል መንግሥት ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
የተባበሩት መንግሥታት የወንጀልና የሱስ አምጭ ዕፆች መከላከያ ጽ/ቤት በኤርትራ ጉባዔ እካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ፓርላማ ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ ላይ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ግምገማቸውን ለቪኦኤ አካፍለዋል።
ወንጀለኛ በይፋ ሲንቀሳቀስ እያየ ለሕግ ያላቀረበ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ እንደሚጠየቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ከጂግጂጋ ወደሃረርና አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ባቢሌ ላይ ተዘጋ፡፡
በቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በሌላ በኩል አምስት ሰዎች መገደላቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሲቪሎች መቁሰላቸውን የከተማው ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር አመልክቷል፡፡
ስለ ለውጥ መናገር ለውጥን መጀመር መለወጥ አይደለም ሲሉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር አስገነዘቡ፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ስር የሚገኙት የካቤና ለጎጎራ አካባቢ ኗሪዎች የካቤ የቀድሞ ወረዳነት ተመልሶልን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄውን ተከትሎ የወረኢሉ ወረዳነት ሊታጠፍ ይችላል የሚል ጭምጭምታ በመሰራጨቱ በወረዳው ውጥረት ነግሶ ቆይቷል፡፡
የኢትዮጵያ አቃብያነ ህግ በቀድሞው በሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትና በ46 ሌሎች ሰዎች ላይ ባለፈው ዓመት በክልሉ ዘር ተኮር ግጭት ቀስቅሰዋል የሚል ክስ ትናንት መስርትዋል ሲል ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል።
የአገር ሸማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡
በኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ።
በትላንትናው ዕለት ከጭናክሰን ከተማ አካባቢ ቤተክርስትያን አንግሰው ወደ ጂግጂጋ ከተማ ሲመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ጥቃት መፈፀሙንና ይሄንን ተከትሎ በተነሳው ረብሻ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናገሩ፡፡
ዛሬ በደቡባዊ ፊሊፒንስ በሚገኝ መስጊድ ላይ በተፈፀመ የፈንጂ ጥቃት ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
የፌደፌሽን ም/ቤት በክልሎች መካከል የሚፈጠረውን የወሰንና የማንነት ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ሲገባው በአማራ ክልል በህጋዊ መንገድ የቀረበ የማንነት ጥያቄ የለም ብሎ መደምደሙ በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል አላስፈላጊ ውዝግብ እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲሉ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዚዳንቱ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ አቶ መርሃፅድቅ መኮነን ተናገሩ።
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮና በምሥራቅ ወለጋ ሊሙ ገሊላ ወረዳዎች ቁጥራቸው ከሃያ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ፡፡
የአካባቢው ነዋሪ ማኅበረሰብ ያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአፋጣኝ ለመፍታት ልዩ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ሊገባ መዘጋጀቱን የድሬዳዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የኦነግ ታጣቂዎች ዛሬ አራት ሰዎችን አንደገደሉ የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የተገደሉት ሰዎች ከአርባ ምንጭ በኮንሶ ዞን አድረገው ቡርጂ ወረዳ አቋርጠው ወደ አማሮ ኬሌ ይጉዋዙ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የፌዴራል መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
“... አብይ አሕመድ ጥረቶቻቸው እንደሚሳኩላቸው የብዙዎች ተስፋ ነው ...” ሲል ፎረን ፖሊሲ ፅፏል።
ሼኽ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱት መቼ እንደሆነ ለጊዜው አይታወቅም።
ራዕይ ለኢትዮጵያ ወይም ቪዥን ኢትዮጵያ የሚባለው የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ምሁራን ስብስብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲያካሂድ የመጀመሪያ የሆነውን ስብሰባውን ባለፈው ወር አዲስ አበባ ላይ አካሂዷል።
ተጨማሪ ይጫኑ