ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ከስምንት ወራት በፊት እንደተፈናቀሉ የሚናገሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከሁለቱም ክልሎች መፍትሔ ማጣታቸውን ተናገሩ።
“..አጠቃላይ የፖለቲካ መንፈሱን ለመቀየር .. ሁላችንንም በሰለጠነ መንገድ እየተነጋገርን ወደምንሄድበት የፖለቲካ ሂደት ለመክተት መጀመሪያ መቀየር ያለበት ይሄ ከእልህና ከቁጭት የወጣ መንፈስ ነው።..” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባቱ ሊቀ መንበር። "በአገራችን ያለንመሸማቀቅ ፖለቲካ እንድናራምድ፣ የአገርነት ስሜቱም እንዲኖረን አንድ እርምጃ ስለሆነ፤ እስረኞችን የመፍታቱን ሂደት እደግፈዋለው። ኢሐዴግ ሁለት ፓርቲ ነው፣ ሦሥት፣ አራት ወይም አንድ? አይገባኝም። የአረና እስረኞች እስካሁን አልተፈቱም። በዚህ አዝናለሁ።” አቶ ገብሩ አሥራት፤ የአረና ትግራይ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል።
በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ በመንግሥት በተጠራ የወጣቶች ኮንፈረንስ ላይ ለተገኙ ተሣታፊዎች ይከፈላል ከተባለ የውሎ አበል ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ አለመግባባት ወደ ፖሊስና ወጣቶች ግጭት አምርቶ በአንድ ወጣት ላይ ከባድ ድብደባ እንደፈፀመ፤ በሁለት የፖሊስ አባላት ላይም ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ድርጅት በሶማሌ ክልል ያለው ልዩ ፖሊስ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ኦሮሞዎችን እየገደለ ነው ካለ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ፖሊሱን መበተን አለበት ይላል።
ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከጥላቻ ይልቅ ለአንድነት እና ለአብሮነት አውንታዊ አመለካከት ቦታ እንዲሰጡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ሃና ማርያም ከተባለው አካባቢ ቤታችን በኃይል ፈርሶብናል ያሉ ነዋሪዎች ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አቤቱታቸውን አቀረቡ፡፡
"ለውጡ እንዳይቀለበስ በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባዋል"- አቶ ዮናታን ተስፋዬ "እስረኖች በሙሉ ሊፈቱ ይገባል"- ጦማሪ ጌታቸው ሽፈራው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከእስር እንዲለቀቁ መወሰናቸውና ከዚያም በቤተመንግሥት ለውይይት መጋበዛቸው በመብት አራማጅ ወጣቶች ዘንድ እንዴት ይታያል? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ሦስት ወጣቶችን ያነጋገረቸው ጽዮን ግርማ ተከታዩን አጠናቅራለች።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ፣ በሰሜን አሜሪካ የኢትጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው በዘንድሮው 35ኛ ዓመታዊ በዓል ላይ ለመገኘት እንደሚፈልጉ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኤምበሲ በፃፈው ደብዳቤ መጠየቁን እንደዘገብን ይታወሳል።
ከትናንት በስቲያ ከእሥር የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀኃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋራ ያደረጉት ውይይት እጅግ አውንታዊ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
“.. አሁን ያለው ነፋስ .. ከአርባ ዓመታት በኋላ ሥለ ፍቅር፣ ሥለ አንድነት፣ ሥለ ፈሪሃ እግዜብሔር፣ ሥለ ሰላም፣ ሥለ አብሮ መኖር መሆኑ በጣም ነው ደስ ያለኝ።.. ‘ጸረ’ የለም። ሲያደክሙን የቆዩት ይህን የመሳሰሉ ነገሮች መቅረታቸው ያስደስታል። ..” ልዑል በዕደማሪያም ሳህለሥላሴ ኃይለሥላሴ።
መንግሥት በፖለቲካ ምክንያት የታሠሩ ዜጎችን መፍታት ያለበት በአንድ ጊዜና በአጠቃላይ ምህረት እንጂ ተራ በተራ አይደለም ሲሉ ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።
በሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተረፉ ሰዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲሉ በውጭ የሚገኘው የሲዳማ ተወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ሰሞኑን የክስ መዝገባቸው እንዲቋረጥ ከተወሰነው 137 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ውስጥ የግንቦት ሰባት ሊቀርመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሀመድ እንደዚሁም ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥን እንደሚገኙበት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የዘገየው፣ ማረሚያ ቤቱ “ሰነድ አልደረሰኝም” በማለቱ እንደነበር ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡
በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች በዝናብ ምክኒያት በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሟች ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሐዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል። የግንቦት 20ን ክብረ-በዓል በተመለከተም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።
የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል።
የኦነግ ወይም የግንቦት ሰባት አባል ናቸው በሚል የሽብር ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ተከሳሾች ከሌሎቹ ተነጥለው ከእስር አለመፈታታቸው እንዳስከፋቸው ከእስረኛ ቤተሰቦች የተወሰኑት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
“.. በአንድ በኩል ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ከባሕር ማዶ በአካል ብኖርም በመንፈሴ በሕልሜና በመንፈሴ ግን ሁሌም አገሬ ውስጥ መሆኔን .. ብዙ ዓመት የነበርኩበት የሰሜን ተራሮች፤ የትጥቅ ትግል የሚያሳዩ ስዕሎች አሉ። .. ያደግኩብትን ሠፈሬን አራዳን፣ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና የአጼ ሚኒሊክ ሃውልትየሚያሳዩ ስዕሎች ናቸው።” የመጽሃፉ ደራሲ አቶ ያሬድ ጥበቡ።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት “ሰላም በማጣት ተቃውሳ የነበረችውን ኢትዮጵያን አረጋግቷል” ብለው ብዙዎች ይስማማሉ።
የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታን ጭምሮ፣ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ አያሌ ሰዎች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መጠየቁ ተሰማ፡፡
ዶ/ር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው 84 ከመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ደስተኞች መሆናቸውን የጠቆመ አንድ የቅኝት ሪፖርት 88 ከመቶው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ግጭት ሽሽትና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመታደገ የ280 ሚሊዮን ዶላርስ አስቸኳይ ዕርዳታ ጠየቀ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
“..በነጻነት ወደ ፊት ለመገስገስ እና ብሔራዊ አንድነትና ታሪካችንን ለማንጸባረቅ የሚያስችለንን እድል ይፈጥርናል። እናም ዘንድሮ ሙሉ ትኩረታችንን፤ ኢትዮጵያ የሀገር ነጻነትንና አንድነትን፣ እንዲሁም ሰላምን በማስጠበቅ በራስ የመተማመን ልባዊ የኩራት ሥሜት በመላው አሕጉሪቱ እንዲስፋፋ ላደረገችው አስተዋጾ አዘከሪያነት ልናውለው መርጠናል።..” ዶ/ር መና አክሊሉ ደምሴ።
ተጨማሪ ይጫኑ