በሀዋሳ እና በዙሪያዋ ለተፈጠረ ግጭት መንስዔው በትክክል እንደማይታወቅ ተነገረ፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ እየወሰዷቸው ባሉ አውንታዊ እርምጃዎች በእጅጉ ተበረታተናል ሲሉ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ሬነር አስታወቁ፣ አሳሳቢ ለሆኑ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ጥረት ለመደገፍ፣ ሀገራቸው የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ችግሮቻቸውን ፈትተው ግንኙነታቸውን ለማሻሻል አዎንታዊ ዕርምጃዎች መውሰዳቸውን ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ በደስታ መቀበላቸውን አስታወቀ፡፡
የዓለም የስደተኞች ቀን የጎረቤት ሃገሮች ስደተኞችን እያስተናገደች ባለችው ኢትዮጵያም በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየታሰበ ነው።
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአልጀርሱን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ በቅርቡ ስለገቡት ቃል የሚነጋገሩ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ አስታወቁ።
መ/ቤታቸው ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ እንደሚሰራ አዲሱ የኢትዮጵያ የደሕንነት ኃላፊ ተናገሩ፡፡
ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ ታስረው የተፈቱ አባላት በበዙበት ኮሚቴ እየተዘጋጀ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማው ሰልፍ ፍቃድ ማግኘቱን አዘጋጆቹ ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት ግጭት በተቀሰቀሰባቸውና በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት በደረሰባቸው ሦስት የደቡብ ክልል ከተሞች የሚገኙ የወረዳና የዞን አመራሮች ኃላፊነት ወስደው ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ሊለቁ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናገሩ።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማፅያኑ መሪ ሪያክ ማቻር የፈረሰውን የሰላም ሥምምነት ያንሰራራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን ስብሰባ ለማካሄድ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መፍትሔ ታጥቶለት ሳይገኝለት ዓመታት ለዘለቀው የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ውዝግብ ሁነኛ መፍትኄ ተስፋ ባንሰራራ በተባለ ውሳኔያቸው አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ላለፉት 18 ዓመታት የዘለቀችበት “ጦርነትም ሰላምም የሌለበት ሁኔታ እንዲያበቃ” በሚል የአልጀርሱን ስምምነትና የሄጉን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደምትቀበል መንግሥቷ አስታውቋል። ከኤርትራ በኩል ግን የተሰጠ ምላሽ የለም።
አሸናፊ አካሉ በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ውስጥ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽሕፈት ቤት የግዢ ኃላፊ በነበረበት ወቅት በሽብር ወንጀል ተከሶ መታሰሩን ይናገራል። በእስር ላይ በነበረበት ወቅትም አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈፀመበት ይናገልፃል።
የመልካም አሰተዳደር ችግር ከአድራጎቶቻቸው ሊጠበቁ የሚገባቸው የፖለቲካ ነጋዴዎች የሚፈጥሩት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀብት “በብዙ ሀገሮች ተከማችቷል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተጠያቂዎቹን ለህግ ለማቅረብ አስተዳደራቸው ከየሀገሩ መንግሥት ጋር እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
"የሦስተኛ ዓመት ትምሕርቴን ጨርሼ ወለጋ ቤተሰቦቼንለመጠየቅ መንገድ ጀመርኩ። መስከረም 3/1999ዓ.ም ካደርኩበት አዲስ አበባ ካራ ቆሬ የምትገኝው እህቴ ቤት ወጥቼ ከጓደኞቼ ጋራ ወደ አውቶብስ ተራ መንገድ ጀመርን። አንድ ፌርማታ እንደሄድን ተኩስ ተከፈተብን። ሦስቱ ወዲያው ሞቱ። እኔ አንድ እግሬ ተጎዳ። ፖሊስ ሆስፒታል ገባሁና ጤነኛው እግሬ ተቆረጠ። ሁለቱም ተቆርጦ ከእነ ቁስሎቼ ወደ ማዕከላዊ ተወሰድኩ"- አርብ ዕለት ከእስር የተፈታው ከፍያለው ተፈራ የተናገረው ነው።
ትልቅ ሀገራዊ አማራጭ የፖለቲካ ሃይል የሚያደራጅ የጋራ ኮሚቴ መዋቀሩን ሰማያዊ ፓርቲና የኮሚቴው አባላት አስታወቁ።
የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርስን ስምምነትና የሄግን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደሚቀበል ማስታወቁን በመቃወም አረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መቀሌ ላይ ተካሂዷል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙ ሦስት ከተሞች ውስጥ ባለፉት አምስት ቀናት በተካሄዱ ግጭቶች 15 ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ በሁለቱ ሃገሮቻቸው መካከል ያሉትን ወንድማዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር ዛሬ ተስማምተዋል።
"ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አራቱ ድርጅቶች የራሳቸውን ድርሻ በመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ አስቀምጠው ተግባብተው ወጥተዋል።.. ለኢህአዴግ ተገዥ እንሁን ነው በአጭሩ።" አቶ አሉላ ሰለሞን በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር ዳይሬክተር። ይሄ መግለጫ ወዲያ ወዲህ መያዝ አያስፈልገውም። በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የተደረገ ተግሳጽ፤ ከፍ ካለ ደግሞ እንደ ዛቻ ነው መታየት ያለበት።” አቶ ጀዋርን ማሃመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር።
ግጭትና መፈናቀልን ለመቅረፍ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ቀዳሚ መፍትሔው እንደሆነ ምሑራን ገልፁ።
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምሕንድስና ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ጋራ በተያያዘ ተማሪዎች ባደረጉት ተቃውሞ በዩኒቨርስቲው ተጀምሮ የነበረው ፈተና መቋረጡን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገለጹ።
በሀዋሳ፣ በወላይታና በወልቂጤ በተፈጠሩ ግጭቶች በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። አካባቢዎቹም ውጥረት እንደነገሰባቸው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። ለግጭቶቹ መባባስ ደግሞ የተጋነኑ መረጃዎች አስተዋጾ አላቸው ብለዋል። ከዚህ በላይ ሁኔታዎቹ እንዳይባባሱ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበትም አሳስበዋል።
ዛሬ የኢድ አል ፈጥር በዓል በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ