የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ በሁለቱ ሃገሮቻቸው መካከል ያሉትን ወንድማዊ ግንኙነቶች ለማጠናከር ዛሬ ተስማምተዋል።
"ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አራቱ ድርጅቶች የራሳቸውን ድርሻ በመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ አስቀምጠው ተግባብተው ወጥተዋል።.. ለኢህአዴግ ተገዥ እንሁን ነው በአጭሩ።" አቶ አሉላ ሰለሞን በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር ዳይሬክተር። ይሄ መግለጫ ወዲያ ወዲህ መያዝ አያስፈልገውም። በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የተደረገ ተግሳጽ፤ ከፍ ካለ ደግሞ እንደ ዛቻ ነው መታየት ያለበት።” አቶ ጀዋርን ማሃመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር።
ግጭትና መፈናቀልን ለመቅረፍ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ቀዳሚ መፍትሔው እንደሆነ ምሑራን ገልፁ።
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምሕንድስና ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ጋራ በተያያዘ ተማሪዎች ባደረጉት ተቃውሞ በዩኒቨርስቲው ተጀምሮ የነበረው ፈተና መቋረጡን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገለጹ።
በሀዋሳ፣ በወላይታና በወልቂጤ በተፈጠሩ ግጭቶች በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ታወቀ። አካባቢዎቹም ውጥረት እንደነገሰባቸው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። ለግጭቶቹ መባባስ ደግሞ የተጋነኑ መረጃዎች አስተዋጾ አላቸው ብለዋል። ከዚህ በላይ ሁኔታዎቹ እንዳይባባሱ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበትም አሳስበዋል።
ዛሬ የኢድ አል ፈጥር በዓል በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው።
ኦሮምያ ውስጥ አልፎ አልፎ ይታያል ያሉትን የሥርዓተ-አልበኝነት ችግር ለማስወገድ ከሕዝብ ጋር ሆነው እንደሚሠሩ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮምያና ሶማሌ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች ላይ ሲነሱ በቆዩ ግጭቶች ምክንያት ኦሮምያ ውስጥ 159 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማስወገድ፣ የተባበረው አረብ ኤሚሬትስ መንግሥት $1 ቢሊዬን ዶላር ማዕከላዊ ባንክ ውስጥ እንደሚያስገባላት አስታወቀ።
በሀዋሳ ከተማ የተከበረውን የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የፊቼ ጨምበላላ ባህል ዋዜማ ተከትሎ የተፈጠረው ግጭት በዛሬው ዕለት ተባብሶ መዋሉን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ። ግጭቱ ወደ ብሔር እንዲያድግ የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ የሚናገሩም አሉ።
የአልጀርስን ስምምነት የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽንን ውሣኔ እንደሚቀበል የኢህአዴግን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የደረሰበትን አቋም በመቃወም በድንበሩ አካባቢ ያለው የኢሮብ ተወላጆችና የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብና የመንግሥት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታ ማዞርን በተመለከተ በመገናኛ ብዙኃን ይፋ መግለጫ ከመሰጠቱ በፊት የኢሕአዴግ ምክር ቤት መወያየት ነበረበት ሲል የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ካናዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ በጋራ እንዲያዘጋጁ ፊፋ፣ ዓለምቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ወሰነ።
በትናንትናው ዕለት በሐዋሳ ከተማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል ዋዜማ ላይ በተፈጠረ ግጭት፤ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ከ30 የበለጡ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን በሐዋሳ ከተማ ያነጋግረናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።
በአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ምክንያት ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ባላቸው አነስተኛ መሬት ራሳቸውንና ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል የተባለ አንድ የንግድ ሥራ ድርጅት መቋቋሙ ታውቋል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አሳሪ ነው ያለውን የአልጀርሱን ሥምምነት የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ መቀበሉ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው አለ፡፡
የምሕረት አሰጣጥና አፈፃፀም ሥነስርዓት ረቂቅ ዐዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል። ይህ ረቂቅ ዐዋጅ ምን ያካትታል? ጽዮን ግርማ በምክር ቤቱ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ዴታ አቶ አማኑኤል አብርሃም ጠይቃቸዋለች።
በተለያየ ደረጃ በሚገኙ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ የአመራር አባላት ላይ ዕርምጃ መውሰዱን የኦሮምያ ገዢ ፓርቲ /ኦህዴድ/ አስታወቀ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በራስ ገዟ ታይዋን ውስጥ እጅግ ያማረ የይስሙላ ኤምባሲ ከፈተች፣ “ታይዋን የእኔ ግዛት ነው” የምትለዋ ቻይና፣ በነገሩ ተቆጥታለች።
ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ምላሽ እንዲሰጣቸው አስፈላጊው ጥበቃም እንዲደረግላቸው አሳስቧል።
ከቀድሞው የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ብሪጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ጋራ የተደረገ ቃለ ምልልስ።
ከኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን የተፈናቀሉት ነዋሪዎች የመፈናቀላቸው ምክኒያት “ፍርሃት እንጂ የፀጥታ ችግር አይደለም” ሲሉ የዞኑ የሰዲ ጨንቃ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ።ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ “የተደራጁ ኃይሎች ንብረት አቃጥለው፣ መሰረታዊ አገልግሎት እንዳናገኝ ከልክለው፣ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ ብለው ሲያባርሩን ነው የኖርንበትንና ንብረት ያፈራንበትን መንደር ጥለን የተሰደድነው።” ይላሉ።
በዩናይትድ ስቴይትስ ብዙ ሰዎችን ከሚያስተናግዱ የአውሮፕላን ማረፊያዎች አንዱ በሆነው ኦ-ሄይር አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያደርገው በረራ በዩናይትድ ስቴይትስና ኢትዮጵያ መካከል የንግድና የምጣኔ ሀብት ትስስርን የሚያጠናክር እንደሚሆን ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ምሥራቅና ምዕራብ ጉጂ ዞኖችንና ጌዴኦ ዞንን በሚያዋስኑ ወረዳዎች ውስጥ ግጭት አገርሽቶ የብዙ ዜጎች ሕይወት መጥፋቱ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ሰለሕዝብ ከመኖሪያው መፈናቀልና መፍትኄው መልስ የሚሠጡን ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም መሆናቸውን ስናሳውቅ ሰሞነኛ በሆነው የኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ላይም መልስ ይስጡን የሚሉ ጥያቄዎች ከ አድማጮቻችን ቀረቡ በተለይም አሰብ ወደብ ታሪካዊ ባለቤትነት ላይ ዶ/ር ያዕቆብ "አሰብ የማናት" የሚል መጽሐፍ አስነብበውናል።
ኢትዮጵያ የአባይን ውኃ ለልማት ስትጠቀም የግብፅንም ሆነ የሱዳን ፍላጎት እንደምትረዳና ድርሻቸውንም እንደምታከብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ