“..አጠቃላይ የፖለቲካ መንፈሱን ለመቀየር .. ሁላችንንም በሰለጠነ መንገድ እየተነጋገርን ወደምንሄድበት የፖለቲካ ሂደት ለመክተት መጀመሪያ መቀየር ያለበት ይሄ ከእልህና ከቁጭት የወጣ መንፈስ ነው።..” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባቱ ሊቀ መንበር።
"በአገራችን ያለንመሸማቀቅ ፖለቲካ እንድናራምድ፣ የአገርነት ስሜቱም እንዲኖረን አንድ እርምጃ ስለሆነ፤ እስረኞችን የመፍታቱን ሂደት እደግፈዋለው። ኢሐዴግ ሁለት ፓርቲ ነው፣ ሦሥት፣ አራት ወይም አንድ? አይገባኝም። የአረና እስረኞች እስካሁን አልተፈቱም። በዚህ አዝናለሁ።” አቶ ገብሩ አሥራት፤ የአረና ትግራይ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል።