መንግሥት በፖለቲካ ምክንያት የታሠሩ ዜጎችን መፍታት ያለበት በአንድ ጊዜና በአጠቃላይ ምህረት እንጂ ተራ በተራ አይደለም ሲሉ ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።
በሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት የተረፉ ሰዎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው እርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል ሲሉ በውጭ የሚገኘው የሲዳማ ተወላጆች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ሰሞኑን የክስ መዝገባቸው እንዲቋረጥ ከተወሰነው 137 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ውስጥ የግንቦት ሰባት ሊቀርመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሀመድ እንደዚሁም ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥን እንደሚገኙበት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የዘገየው፣ ማረሚያ ቤቱ “ሰነድ አልደረሰኝም” በማለቱ እንደነበር ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡
በሲዳማ ዞን ጭሬ ወረዳ ሐሊላ መሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች በዝናብ ምክኒያት በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ23 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የሟች ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሐዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል። የግንቦት 20ን ክብረ-በዓል በተመለከተም፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል፣ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።
የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል።
የኦነግ ወይም የግንቦት ሰባት አባል ናቸው በሚል የሽብር ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ተከሳሾች ከሌሎቹ ተነጥለው ከእስር አለመፈታታቸው እንዳስከፋቸው ከእስረኛ ቤተሰቦች የተወሰኑት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
“.. በአንድ በኩል ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ከባሕር ማዶ በአካል ብኖርም በመንፈሴ በሕልሜና በመንፈሴ ግን ሁሌም አገሬ ውስጥ መሆኔን .. ብዙ ዓመት የነበርኩበት የሰሜን ተራሮች፤ የትጥቅ ትግል የሚያሳዩ ስዕሎች አሉ። .. ያደግኩብትን ሠፈሬን አራዳን፣ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና የአጼ ሚኒሊክ ሃውልትየሚያሳዩ ስዕሎች ናቸው።” የመጽሃፉ ደራሲ አቶ ያሬድ ጥበቡ።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት “ሰላም በማጣት ተቃውሳ የነበረችውን ኢትዮጵያን አረጋግቷል” ብለው ብዙዎች ይስማማሉ።
የቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታን ጭምሮ፣ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ አያሌ ሰዎች ክስ እንዲቋረጥ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ መጠየቁ ተሰማ፡፡
ዶ/ር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው 84 ከመቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ደስተኞች መሆናቸውን የጠቆመ አንድ የቅኝት ሪፖርት 88 ከመቶው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ግጭት ሽሽትና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመታደገ የ280 ሚሊዮን ዶላርስ አስቸኳይ ዕርዳታ ጠየቀ።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
“..በነጻነት ወደ ፊት ለመገስገስ እና ብሔራዊ አንድነትና ታሪካችንን ለማንጸባረቅ የሚያስችለንን እድል ይፈጥርናል። እናም ዘንድሮ ሙሉ ትኩረታችንን፤ ኢትዮጵያ የሀገር ነጻነትንና አንድነትን፣ እንዲሁም ሰላምን በማስጠበቅ በራስ የመተማመን ልባዊ የኩራት ሥሜት በመላው አሕጉሪቱ እንዲስፋፋ ላደረገችው አስተዋጾ አዘከሪያነት ልናውለው መርጠናል።..” ዶ/ር መና አክሊሉ ደምሴ።
በሽብር ወንጀል ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምሕር ጌታ አስራደ ከእስር እንዲፈታ ቤተሰቦቹ ተማፀኑ።
የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ዛሬ 7ሺህ 6መቶ አሥራ አንድ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ ፋቷል። 7ሺህ 183 ወንዶች፣ 428 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሳዑዲ ያደረጉትን ጉብኝት በማስመልከት በሃገሪቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ መሪዎች የተሰጡት አስተያየት።
ሰሞኑን በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "ማንጎ ጨፌ" በሚባል አካባቢ ከ2 ሺህ በላይ ቤቶች በኃይል መፍረሳቸውን መላው የኢትዮጵያ የአንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አስታወቀ፡፡
ለሥድስት ወራት የቤት ክራይ ለመክፈል ቃል የገባልን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአካባቢው አስተዳደር ከሁለት ወራት በኋላ ሜዳ ላይ በትኖናል ሲሉ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች አማረሩ፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በጂቡቲ ጀምረው ሱዳንና ኬንያን በጎበኙበት ወቅት የኢኮኖሚና ሌሎች ሥምምነቶች ማድረጋቸው የሚታወቅ ነው። በተለይም ከጂቡቲ ጋር ቀደም ብሎ የታቀድው የኢኮኖሚ ውሕደት ሊፋጠን የሚችልበት ሁኔታ ፈጥሯል ተብሏል።
ከኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ የተፈናቀለ አንድም የአማራ ክልል ተወላጅ አርሶ አደር የለም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ትላንት ምሽት ፍንዳታ መድረሱን የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን ያደረጉት ጉብኝት ካሳካቸው ጉዳዮች አንዱ ሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲን ለማስፈታት ጫፍ ላይ መደረሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታወቁ።
ተጨማሪ ይጫኑ