“የአገሪቱን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ውሉን መጨበጥ ያስፈልጋል። ለዚህም የሕዝብን አመኔታ ማግኘት ነው። ዶ/ር አብይ ዛሬ ባደረጉት ንግግር .. ተስፋ ሰጪ ነገሮችን ተናግረዋል። በተስፋ ብቻ ሳይሆን ታዲያ በተግባር መጀመር አለባቸው።” ዶ/ር ታዬ ዘገየ የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ሸንጎ ፕሬዝዳንት።
“አንድ ሃሳብ የበላይነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃሳብ የሚንሸራሸርበት፤ ታቃዋሚ ሳይሆን ተፎካካሪ የምንሆንበት የሚል ዓይነት መሳጭ ንግግሮችን ስለሰማሁ ይህንን ኃላፊነት .. ጊዜው የሚጠይቀውን ፖለቲካ የተረዱት ይመስለኛል።” አቶ ጃዋር መሃመድ የኦሮሞ ሚድያ ኔት-ወርክ ሥራ አስኪያጅ።