የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የካቢኔ ሹም ሽር አካሂደዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አዲስ ካቢኔ በመሰረቱ፣ ከወትሮው የተለየ እንዳልሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው በቅርብ ላሉ አጣዳፊ ጉዳዮች ነው ይላሉ - የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፡፡
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በነገው ዕለት የካቢኔ ሹም ሽር እንደሚያካሂዱ ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የጆርጅ ቡሽ ባለቤት ባርብራ ቡሽ ዛሬ አረፉ። ዕድሜያቸው 92 ሲሆን ባርብራ ቡሽ የፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ እናትም እንደሆኑ ይታወቃል።
“በእኔ ዓይን .. የወደፊቷ ኢትዮጵያችን የፖለቲካ እስረኞች የሌሉባት እንድትሆን ማሰብ ብዙዎች ይስማሙበታል ባይ ነኝ።” ጌብ ሃምዳ (ዶ/ር) “ይሄ መንግስት አዋላጅ መንግስት ከመሆኑ በፊት .. አዋላጅ ባለ ሥልጣናት አንዲመጡ ያስፈልጉታል። ዶ/ር አብይ የመጡበትም ይሄው የአዋላጅ ባለ ሥልጣን አካሄድ ነው።” ዘላለም እሸቴ (ዶ/ር)
ዛሬ ጠዋት ተፈጥሮ የነበረው የበርካታ በረራዎች መስተጓጎል ችግር እልባት ማግኘቱንና የተለመደው ሥራ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ዛሬ ረፋድ በሞያሌ ተከስቶ በነበረዉ አለመረጋጋት 3 ሰዎች ሞተዉ ከ 50 በላይ የሚሆኑት ከባድ ና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረባቸዉ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል። ግጭቱ የተከሰተዉ በሞያሌ 02 ቀበሌ መናኸርያ በሚባል ቦታ ሲሆን አንድ የእጅ ቦምብ መወርወሩንና ሽጉጥ መተኮሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
አንድ የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ መግባባትና የሽግግር መንግሥት አስተባበሪ ኮሚቴ የተሰኘ አካል ሀገር ውስጥ ሊካሂድ ላቀደው ጉባዔ የርዕሰ ብሄሩን ድጋፍ እንዳገኘ አስታወቀ፡፡
ኤችአር 128 ተብሎ የሚጠራውን የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያሳለፈው ውሣኔ እንዳይፀድቅ ለማስተጓጎል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰባት መቶ ሚሊየን ብር በላይ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ማውጣቱን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለፁ።
ጥያቄያቸው የማንነት እንጂ የልማት እንዳልሆነ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት ኮሚቴ አመራር አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በኢትዮጵያ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በኮንሶ የታሰሩ እስረኞችን በተመለከተ የተጠናቀረ ዘገባ።
የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየጊዜው ደረሱብን በሚሉ የፌደራልና የመከላከያ ጥቃቶች ሳቢያ ትምህርታቸውን ካቋረጡ ከአንድ ወር በላይ እንደሆናቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
"ትግራይ የሀገራችን ኩራት ነች” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ተናግረዋል።
ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 114 ሰዎች መካከል ዛሬ ሁለቱ የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ከእስር መፈታታቸው ታወቀ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የኢትዮጵያን ሰብዓዊ መብትና የተጠያቂነት ሕግ ኤችአር 128 ማፅደቁን እንደሚደግፉ፣ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ፡፡
“ዶ/ር አብይ እንዲያውም H. Res. 128 ያነበቡ እኮ ነው የሚመስሉት እዛ ላይ። ስለዚህ H. Res. 128 ምንድን ነው? ብሎ አንድ ሰው ድንገት መንገድ ላይ አስቁሞ ቢጠይቀኝ፤ የመልካም አስተዳደር የጀርባ አጥንት ነው፤ ብዬ ነው የምመልሰው።” የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ከትላንት በስቲያ ያፀደቀው።”ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የኮሎራዶው የኢትዮ-አሜሪካውያን ሲቪክ ምክር ቤት (ካውንስል) ሊቀ መንበር።
የፊደል ገበታ ተዘርግቶ ሀ-ሁ መቁጠር ከተጀመረ መቶ ዓመት ሞላው፡፡
የኤርትራ መንግሥት ሰሞኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ኮሚሽን የሰጠው ውሳኔ ተግባር ላይ እንዲውል የሚጠይቅ መግለጫ አውጥቷል፡፡
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የገቡትን ቃል በተግባር እንዲፈፅሙ እንጠብቃለን ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ፡፡
“በመጀመሪያ ደረጃ የምክር ቤቱን ተቆርቋሪነት ያሳያል። እና ይሄ ሕገ-ውሳኔ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን፣ የሕዝብን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው በግዴታ መባረርን፣ እናም የሕግ አልባነትን በመቃወም የወጣ ውሳኔ ነው።” ፍጹም አቻምየለህ ሂደቱን የተከታተሉ እና በዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው በጥብቅና ሥራ የተሰማሩ የሕግ ባለ ሞያ
በዛሬው ዕለት ወደ አምቦ ከተማ ተጉዘው በስተዲየም ለተሰባሰው የከተማው ነዋሪ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትናንቱን ቁርሾና ጠባሳን በመተው ጠንካራ የአንድነት ማዕቀፍ እንዲገነባ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድር ከዩናይትድ ስቴይትስ ፖሊሲ ጋር ለመቃነት ያለመው ውሳኔ 128 በዩናይትድ ስቴይትስ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት ፊት ትናንት ምሽት ቀርቦ ያለምንም ተቃውሞ ጸድቋል።
የአሜሪካ ኮንግረስ ያሳለፈው ኤችአር 128 መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃውሞውን ገልጿል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ114 ተከሳሾችን ክስ ማቋረጡ ታወቀ፡፡ ከእነዚህም መካከል ሁለቱ የዋልድባ ገዳመ መነኮሳት እንደሚገኙባቸውም ተረጋግጧል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ