“ተጠያቂነትን አልተማርንም። ለሞቱት ሰዎች የተጠየቀ ሰው የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲህ ያሉት የጭፍን አሰራሮች ተቁዋሞቻችንን ይገድሏቸዋል።” አቶ የሺዋስ አሰፋ።
“ሰው እኮ አንዴት ነው ያለመቀበሉን ሃሳቡን የሚገልጽበት መስመር መኖር አለበት። ሰው በተናገረ ቁጥር እንደ ጠላት ማየት የመንግስትነት አያያዝ ነው ብዬ አላምንም ።” ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ።
“የመንግስት ተቀባይነት በምን ላይ ነው የሚመሰረተው? እነኝህን ችግሮች ፖለቲካዊ ገፅታ በዚህ መንገድ እፈታቸዋለሁ’ ማለት አልቻለም።” አቶ ሙልጌታ አረጋዊ።