በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውና ለኢትዮጵያ ፓርላማ የቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ዛሬ “ያልተለመደ” ከሚባል ሰፊ ተቃውሞ ጋር ፀድቋል፡፡
ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያፀደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ዓለምቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወዲያውኑ ባወጣው መግለጫ ውሣኔውን “አሳዛኝ እና ኃላፊነት የጎደለው” ብሎታል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት ሃያ ሰባት አንስቶ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሃገሮችን እንደሚጎበኙ መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ዝግጅታችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ጉዳዩን የሚከታተሉ ምሑራን ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት አባላት ፓርቲያቸውን በየትኛውም መድረክ እንዲደግፉ የሚያስገድድ መታነፅ ወይም ዲስፕሊን እንዳላቸው ይናገራሉ።
“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር።
"ዓለማቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረኃይል" የተባለው ቡድን ለኢትዮጵያውያን ባቀረበው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ ወደ ህወሓት አካውንት በሬሚታንስ ወይም በሀዋላ መልክ የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ ለማቆም እንደሆነ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከ2007ቱ ምርጫ አንስቶ በሀገሪቱ የተካሄዱ ሂደቶች ድምር ውጤት ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞችና ተቃዋሚዎች።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሶሪያ የታወጀው ለአንድ ወር የሚዘልቅ ተኩስ አቁም ተግባራዊ እንዲሆን መወትወቱን አላቆመም፣ አያቆምምም ሲሉ የድርጅቱ የሶሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስቴፋን ደ ሚስቱራ ተናገሩ፡፡
የአፍሪካ ማኅበረሰቦች በህብረት የሚገኙበት፣ የማኅበረሰብ አባሎቻቸውን መብትና ነፃነት ለማስከበር፣ በሥራ ገበታቸውም ላይ የሚገጥማቸውን የመብት ጥሰት ለመከላከል የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ስብስብ ባለፈው ቅዳሜ ዋሽንግተን አካባቢ ባሉ አውሮፕላን ጣቢያዎች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ላነሷቸው ጥያቄዎች ስለተገኙት ድሎች ለኢትዮጵያውያን ማኀበረሰብ መሪዎች አስረድቷል።
ሦስቱ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስታውቀዋል። የኢሕአዴግ ምክር ቤትና የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመወሰን በምክር ቤቱ በሚደረገው ምርጫ ላይ ለመወሰን ዕጩ ያላቀረብው ፓርቲ የተሻለ ዕድል እንዳለው ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ይናገራሉ።
የኦሮሚያ ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ እና ተቃዋሚው ኦፌኮ ለመደራደር መወሰናቸውና በቅርቡ እየታዩ ያሉ ሌሎች ለውጦች ከሁለቱ ፓርቲዎች ግንኙነት የዘለለ ትርጉም እየተሰጣቸው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ መገንባት ከጀመረች አምስት ዓመታት አልፈዋል።
የጉራጌ ዞን ማዕከል የሆነችው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ያነሱት የልማት ጥያቄ ፖለቲካዊ ትርጉም እየተሰጠው ነው ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናገሩ።
የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሕገወጥ ያላቸው አካላት የሕዝብን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሞክረዋል ሲል አስታውቋል።
“የአሁኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከቀደመው የሚለየው፤ አሁን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር በዋናነት ለመጨፍለቅ ጭምር የታሰበ አርጌ ስለማየው፤ መጭውን በዚህ ሁኔታ ነው የምገነዘበው።” ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና “በስልጣን ላይ (ሳለ) ሰው ሲታሰር የማውቀው እርሳቸውን ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መልቀቃቸውን የማየው ሌሎች ከእስር እንደተፈቱት ነው .. የችግሩ ሰበብም አይመስሉኝም። በመልቀቃቸውም ደግሞ ችግሮቹ ይቃለላሉ ብዬ ለማሰብ እቸገራለሁ።” ቴዎድሮስ ጸጋዬ
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ እስር ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ታዟል።
“የኮማንድ ፖስት ያዘዘው ነው፣ አስተዳደሩ ሥራ ላይ ያዋለው። ከዓዋጁ ጋር አይሄድም። በመሆኑም ለሌላ ጊዜ ሁኔታዎችን አመቻችተን እንቀበላቸዋለን፤ ለአሁኑ ይመለሱ ነው የተባለው።” - አቶ ሞገስ ኤዴኤ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን በብርቱ በመቃወሙም ሆነ ያንን ይፋ በማድረጉ አቋሙ እንደሚፀና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ኢህአዴግ ሀገራችንን ካስገባት ቀውስ ውስጥ የማውጣት ብቃት የለውም ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ መግለጫ አወጣ፡፡
በሦሪያ በተከበበችው ምሥራቅ ጎታ ላይ የሚዘንበው እጅግ ሰቅጣጭ የቦንብ ድብደባና በደማስቆ ከተማ ላይ የሚወነጨፈው የከባድ መሣሪያ ውርጅብኝ በአስችኳይ እንዲቆም፣ የዓለሙ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ስታፋን ዲ ሚስቱራ ዛሬ ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ሊቀመንበር፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያለፈውን የአውሮፓውያኑን 2017 ዓ.ም የሃገሮች ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሪፖርቱን አውጥቷል።
በኬንያ ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ።
ጀርመን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በዋና ከተማዋ ውስጥ ከጧቱ 4ሰዓት አንስቶ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን ከአስተባባሪዎቹ አንዱ ለአሜሪካ ጣቢያ ገለፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ