በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ “ሸዋበር” በተባለ የመኖሪያ መንደር በትናንትናው ዕለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፈፀሙት ጥቃት ዐሥር ሰዎች ተገድለው ሌሎች ዐሥራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች፣ የከተማው አስተዳደርና ኮማንድ ፖስቱ አረጋግጠዋል።
“የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ ቆስለው ወደ ሆስፒታላችን የመጡና እየታከሙ ያሉ አሥር ሰዎች አይተናል። ሌሎች ቁጥራቸው ዘጠኝ የሚደርስ ሰዎች የሞቱ አይተናል።” የሞያሌ ሆስፒታል ሥራ አሥኪያጅ አቶ አሬሮ ቢቂቻ
ሩሲያ ግጭቶች ያለምንም ጣልቃ ገብነትና ሁሉን ዓቀፍ በሆነ ውይይት እንዲፈቱ እንደምታበረታታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን ያደረጉት ጉብኝት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ያላትን አቋም ይበልጥ ያረጋገጠችበትና ግልፅ ያደረገችበት መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙት አምባሳደር አስታውቀዋል፡፡
ከኮንሶ የአስተዳደር እርከን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የተያዙ ሰዎች አብዛኞቹ ዛሬም በእሥር እንደሚንገላቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ለሴቶች መብት ለአካል ጉዳተኞች መብትና ዕኩልነት ተሟጋች ጠበቃዋ፣ የትነበርሽ በዛሬው ዓለምቀፍ የሴቶች ቀን አንድ ከፍተኛ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
በኢትዮጵያ የቅርብ ሴት ጓደኛማቾች በጋራ የመሰረቱት “safe house” በአማርኛ "ከለላ ቤት" የተሰኘው የግብረሰናይ ድርጅት የተጎዱ ሴቶች የሚያገግሙበት መጠለያ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሄርመን ኮኸን በአሁኑ ወቅት አምስት የአፍሪካ ሃገሮችን በመጉብኝት ላይ ስላሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን ጉዞ በተለይም ኢትዮጵያን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት መነሻ በማድረግ አነጋግረናቸዋል።
ከኢሕአዴግ አዲስ ለውጥ እንደማይጠብቁ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልፀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች መኖራቸውን የኮማንድ ፖስት ማለትም የማዘዣ ዕፅ ጽ/ቤት ኃላፊ የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሳ አስታወቁ፡፡
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አዲስ ሊቀመንበሩን ወደመምረጥ የሚወስደውን ስብሰባ ለማድረግ ለፊታችን ዕሁድ፤ መጋቢት 2/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ያዘ።
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የነበሩና ትምህርታቸውን በሀንጋሪ በመከታተል ላይ የሚገኙ ሰላሳ የሚሆኑ ተማሪዎች በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለችግር እንደተጋለጡ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገለፁ።
አብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞችና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ንግድ ቤቶች አስቸኳይ ጊዜ አዐዋጁን በመቃወም ዝግ ናቸው።
የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ከእሥር መፈታቱ ተሰማ፡፡
“ለኢትዮጵያ አምላክ ሰላም እንዲያወርድ እፀልያለሁ” - ባለቤታቸው የተገደለባቸው ልጃቸው የቆሰለባቸው እናት።
የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው - በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፀዳደቅ በሕገ መንግስቱ መሰረት ግድፈት አለበት ሲሉ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና የሕግ ባለሞያ ገለፁ። በሀገሪቱ ሕገ መንግስት ላይ ዐዋጁ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ መፅደቅ እንዳለበት በግልፅ እንደሚያስቀምጥና ይህ ድምፅ ደግሞ አለመገኘቱን ይናገራሉ።
በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ፣በምዕራብ ወለጋ፣በምስራቅ ወለጋና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ውስጥ በዛሬው ዕለት በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲያነጋግር የሰነበተውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአነስተኛ ድምጽ ብልጫ በዛሬው ዕለት አጽድቋል።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውና ለኢትዮጵያ ፓርላማ የቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ዛሬ “ያልተለመደ” ከሚባል ሰፊ ተቃውሞ ጋር ፀድቋል፡፡
ዛሬ የኢትዮጵያ ፓርላማ ያፀደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ዓለምቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወዲያውኑ ባወጣው መግለጫ ውሣኔውን “አሳዛኝ እና ኃላፊነት የጎደለው” ብሎታል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከፊታችን ማክሰኞ የካቲት ሃያ ሰባት አንስቶ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ ሃገሮችን እንደሚጎበኙ መሥሪያ ቤታቸው አስታውቋል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ዝግጅታችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ተጨማሪ ይጫኑ