መሰብሰብና ሃሣብን መግለፅን መከልከልን ጨምሮ በመሠረታዊ መብቶች ላይ ክልከላ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰደው ውሣኔ በብርቱ እንደማይስማማ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ።
“ሁከትና የሰው ሕይወት የጠፋባቸውን አጋጣሚዎች የምንረዳና የኢትዮጵያ መንግሥትም ያሉትን ሥጋቶች የምንጋራ ብንሆንም መልሱ ግን ነፃነትን ማሳነስ ሳይሆን ማብዛት እንደሆነ በብርቱ እናምናለን” ብሏል የኤምባሲው መግለጫ።