የኃይማኖት መሪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግን/ና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ኦዴፓ/ን ለመሸምገል ድርድር መጀመራቸው ተዘገበ፡፡
በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሰመረ ርእሶም የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ለፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ አቅርበዋል።
ቪዥን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰበተኛ የጥናትና ምርምር ጉባዔውን አዲስ አበባ ላይ ከፈተ፡፡
በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አምስት የቡርጂ ወረዳ አርሶ አደሮች በታጠቁ የኦነግ አባላት ሲገደሉ፤ ሊሎች ሰባት ሲቪሎች ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደረሰባቸው የቡርጂ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ለሰላማዊ ትግል የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ እንዳይቀለበስ ከለውጡ ኃይሎችና ለሰላም ከቆሙ የተለያዩ ተፎካካሪ ድርጅቶች ጋር በፅናት እንቆማለን ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት አስታወቀ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት የአዳዲስ አምባሳደሮችን ሾመ።
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ጊዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ትናንት ማንነታቸው ባልታወቀ አጥቂዎች ተተኩሶባቸው መገደላቸውና ሌላ ወጣት መቁሰሉ ተገለፀ፡፡
"በትግራይ ክልል በሚገኙ ድርጅቶች ኤርትራውያን በንግድ እየተሳሰሩ ናቸው" ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ የዛላንበሳ ድንበር ዛሬ መዘጋቱን የትግራይ ክልል የጉሎ መኸዳ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከዛሬ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
በጊንቢ ከተማ ሁለት ወጣቶች በታጠቀ ኃይል መገደላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ትናንት አንድ በጉልበት ሥራ የሚተዳደር ወጣት ሲገደል፣ ዛሬ ደግሞ የአእምሮ ጤና እክል ያለበት ወጣት ተገድሏል፤ ይላሉ የዓይን እማኞች፡፡
በኢትዮጵያ ከየትኛውም ጉዳይ በላይ መቅደም ያለበት አገርን ማረጋጋትና ሰላምን ማስፈን ነው ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት አስታወቀ።
የትግራይና አማራ ክልሎች የእግር ኳስ ክለቦች በትግራይ ስታድዮሞች የሚያካሂዱት ጨዋታ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የትግራይ ህዝብና መንግስት ሓላፊነት ይወስዳል አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
'አባ ቶርቤ' በሚባል መጠሪያ ምዕራብ ኦሮምያ ውስጥ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስና በክልሉ ባለሥልጣናት እና በፖሊስ ባልደረቦች ላይ ግድያ የሚፈፅምን ቡድን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ አዋሳኝ ላይ ዳግም በተቆሰቆሰ ግጭት ትላንት የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን የአማሮ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡
በምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ፓርላማ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አፅድቋል፡፡
የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ቤታቸው ሲያመሩ በደረሰባቸው ጥቃት በፀና ቆስለው በኦሮታ ሆስፒታል ሲታካሙ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ወደ ውጭ ሃገር እንደተላኩ ተገልጿል።
"መንግሥት ጦርነት እያወጀ ነው" ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከሰሰ፡፡ አስመራ ላይ የተደረገው ውል ገቢራዊ እንዳይሆንም መንግሥት እንቅፋት እየሆነ ነው ብሏል።
"ውቭን" ይሰኛል - የሁለት ዓለም ባሕል፣ የኑሮ መስተጋብር ዘይቤና ፈተናዎቹን ከግዙፉ የፊልም ሰሌዳ የከሰተው፤ ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን ተዋናዮች የተሳተፉበት የሶሎሜ ሙልጌታና የናግዋ ኢብራሂም ፊልም።
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሰባዊ መብት ጥሰት ተዳርገን ቆይተናል” ሲሉ ከአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ አዲስ ራይ ማሰልጠኛ ተቋም ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የመጡ ወጣቶች ገለፁ።
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአማራና ኦሮሞ ተወላጆች መካከል የተካሄደውን የእርቅ ሥነ-ስርዓት ይመለከታል፡፡ በሥነ-ስርዓቱ የታደሙት የሁለቱም ክልል ተወላጆች ዳግመኛ ላለመጣላት ቃል ገብተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የታወጀው የምህረት ዓዋጅ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት እንደቀሩት የገለፀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ የሚመለከታቸው ሁሉ በፍጥነት እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቀረበ፡፡
"ከሆስፒታሉ ካርድ ከማውጣት ውጭ ምንም ዓይነት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም። ምርመራ ከግል ሆስፒታል አድርጉ፣ መድሃኒት ከውጭ ግዙ ነው የምንባለው" ሲሉ በባህር ዳር ከተማ የፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተገልጋዮች ገለፁ።
አራተኛው የኢህአደግ ሴቶች ሊግ ጉባዔ መቀሌ ተካሂዷል።
ተጨማሪ ይጫኑ