በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር በሞያሌና ቱርካና ተደጋግመው የሚከሰቱ ግጭቶች "የአካባቢው ምጣኔ ኃብት እንዲቀጭጭና በቀጣናው ውጥረት እንዲሰፍን አድርጓል" ሲል የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት(ኢጋድ) አስታውቋል።
በሞያሌ ዛሬም በሶማሌ ክልል ታጣቂዎች የሚፈፀመዉ ጥቃት መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።
በዕርዳታ በተገኘ ገንዘብ ባጃጅ ገዝቶ በመስጠት ሥራ ያልነበራቸው ያላቸውን ሃያ አምስት ወጣቶች ሥራ ማስጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ የጥቃቅንና የአነስተኛ ንግዶች ልማት መምሪያ ገልጿል።
በትግራይና አማራ ህዝቦች መካከል ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ፎረም በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል።
በምዕራብ ሐረርጌ በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረደ “ጭናክሰን” ውስጥ አዲስ ጥቃት እንደተከፈተባቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
“ቪዥን ኢትዮጵያ” ወይም “ራዕይ ለኢትዮጵያ” የሚባለው ሲቪክ የምሁራን ስብስብ ሰባተኛ ጉባዔውን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያካሂድ ነው።
የአማራና የቅማንት ሕዝብ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማናትና በሥነ ልቦና አንድ ሕዝብ ነን፣ ሊለያዩን የሚሹ ወገኖችን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ስለ ሰላም እንሰራለን ሲሉ በጎንደር በተደረገው የሰላም ውይይት ላይ የተገኙ የሁለቱም ወገን ተሳታፊዎች ተናገሩ።
በአለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተገለፀ ካለውም የከፉ መሆናቸውን፣ በቀዳሚነት በጉዳዩ ላይ ሲሰራ የቆዮ ሀገር በቀል ድርጅት ይናገራል፡፡
በአለፉት 16 ዓመታት በኢትዮጵያ ከድኅነት ወለል በታች የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም በድሃውና በባለፀጋው መካከል የነበረው ልዩነት ግን መስፋቱን አንድ ጥናት አስታወቀ፡፡
ድሬዳዋ በተጠራች ቁጥር ስለ ነዋሪዎቿ ስብጥርና ሰላም “የፍቅር ከተማ” የሚል ሃረግም እንደ ዓርማ ሁሉ አብሮ ይነሳላታል። ከጥቂት ወራት ወዲህ ግን የግጭት ሁኔታዎች ብልጭ ድርግም ሲሉ ይስተዋላል።
የአማራ ሕዝብ በአለፉት ጊዜያት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኮስሶ እንዲታይ በውሽት ትርክት ክብሩ ዝቅ እንዲል ሲደረግ፣ መኖሩ ቁጭትን ፈጥሮብናል ይላሉ የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግሥት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የአመራር ቡድን ባለፈው ሳምንት እሁድ ዩናይትድ ስቴትስ መግባቱ የሚታወስ ነው።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ ያሶ ወረዳ ከሚገኘው ቀያቸው ተፈናቅለው ባህርዳር ከተማ የገቡ አምስት መቶ ተፈናቃዮች ከክልሉ መንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልፀው ቅሬታ አቀረቡ።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ያለፈውን ችግር በሕግና በሥርዓት እንዲሁም በእርቅ መሻገር አማራጭ የለውም ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አሳሰበ።
የሁለት ዜጋቿን እጆች አሳልፋ እንድትሰጣት ቱርክ ያቀረበችውን ጥያቄ ሳዑዲ አረቢያ ውድቅ አደረገች።
ሞሮኮዪቱ ከተማ ማራኬሽ ውስጥ ዛሬ በተከፈተ የሁለት ቀናት ጉባዔ ላይ የተናገሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ “የፍልሰት ጉዳይ መመራት በአግባቡና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንጂ በዘፈቀደና አደገኛ በሆነ መንገድ አይደለም” ብለዋል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የክልሉን ሰላም በመጠበቅ እና በሌሎች የጋራ ጉዳይ ላይ አብረው ለመሥራት በአዲስ አበባ ባደረጉት ወይይት ተስማሙ።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በደንቢያና ጭልጋ በቅማንትና አማራ ብሄር ተወላጆች መካከል ከአራት ቀናት በፊት በተቀሰቀሰ ግጭት ከሥድስት በላይ ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፀ።
ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ አልወረደም አለ፡፡
“ኢትዮጵያ በውጭው እንዲሁም ‘አንዳንድ’ - ባሏቸው - የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ስለከፈተችው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እያራመዱት ስላሉት መንገድ ምሥጋና ይግባውና...” ሲሉ ነው አምባሳደሩ የመክፈቻ መግለጫቸውን የጀመሩት።
ኢትዮጵያን ወደ ኋላ የሚመልስ ኃይል የለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ከሥድስት ዓመታት በፊት ኤርትራ ከሱዳን ጋር የምትዋሰንበትን ድንበር ለማቋረጥ ከሞከረች በኋላ የተሰወረችው የሲያም አሊ አብዱ ቤተሰብ የት እንዳለች እየጠየቀ ነው።
ኢትዮጵያ ሳተላይት የፊታችን መስከረም ውስጥ ልታመጥቅ ነው።
በድሬደዋ ከተማ ከሰባት ዓመት በፊት የተጀመረ የውኃ ፕሮጀክት ሳይጠናቀቅ በመዘግየቱ የሚጠጣ ውኃ አገልግሎት ችግር መኖሩን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። የከተማዪቱ የውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክቱ በመጭዎቹ ሦስት ሣምንት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመልክቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ