የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ኸርበርት ዋከር ቡሽ በተወለዱ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና የሜክሲኮው ፕሬዘዳንት ኤንሪኬ ቴኛ ኒኤቶ “ናፍታ” በመባል የሚታወቀውን የሰሜን አሜሪካ ነፃ የንግድ ሥምምነት የሚተካ አዲስ ሥምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።
በሶማሌ ክልል እስር ቤቶች ውስጥ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ሰዎች በሕግ ፊት ቀርበው ሲዳኙ ማየት ትልቁ ምኞቱ እንደሆነ አንድ ቀድሞ በእነዚህ ቦታዎች ታስሮ የነበረ ወጣት ተናገረ።
በተለያዩ ባለሞያዎች ተቃውሞ ሲቀርብበት የቆየው የአልኮል መጠጦች ገደብ አልባ ማስታወቂያና የሲጋራ አጫጫስና ማስታወቂያ አለጣጠፍ ላይ ገደብ የሚጥል ረቂቅ ዐዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ፀደቀ።
በድሬደዋ ከተማ በወጣቶች መካከል የሚነሳ ተደጋጋሚ ግጭት ለሞት እና ንብረት መቃጠል ምክኒያት እንደሆነ ነዋሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የከተማው አስተዳደርና ፖሊስ ገለፁ።
ኢህአዴግ በሕገወጥነትና በአምባገነናዊነት ያዋቀራቸው የመስተዳደር አከላለሎች ዛሬ ለተፈጠረው የመለያየት ስሜት እና ግጭቶች ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ሲሉ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ከሰሰ፡፡
ሰሞኑን በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ሰብሳቢነት የተካሄደው የፓርቲዎች ውይይት በምርጫ ቦርድ መሪነት እንደሚቀጥል የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በልማድ የስኳር በሽታ በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር /Diabetes/ በመባል በሚታወቀው በሽታ ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ቅንብር ነው።
ከመንግሥት ጋር በተደረገ ሥምምነት ወደ ሀገር ገብተው በአርዳይታ የሥልጠና ማዕከል የሚገኘ የኦነግ ሠራዊት አባላት “መንግሥት ለሥልጠና ብሎ እየወሰደብን የሚገኘው ግዜ ረጅም እና ያለአግባብ ነው፤ ወደ ቤተሰቦቻችን እንዲሸኙን እንፈልጋለን” ሲሉ ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ጤና ነክ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች በተለይ የክትባትና የምርምር ሥራዎችን ለመሥራት እንቅፋት ሆኖብኛል ይላል የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ።
የጂግጂጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ማኅበረሠቦችን በማቀራረብ፣ በተጀመረው ለውጥ አውንታዊ ሚና አንዲጫወቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጥሪ አቀረቡ፡፡ በዘውግ መሥመር ሁኔትዎችን መቃኘት ኋላቀርነት ነው አሉ፡፡
በከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ባለሥልጣናት ገንዘብ እንዲታደግ ከኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ስለመኖሩ፣ አናረጋግጥም፣ አናስተባብልም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የሚጓዙ የአየር ትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን በማስተናገድ ቀዳሚነቱን ከዱባይ ተረከበች። ለዚህም - በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየተወሰደ ያለው የለውጥ እርምጃ በዓለምቀፉ ማኅበረሠብ የተሰጠው በጎ ምላሽ አስተዋፅዖ እንዳበረከተ ተመልክቷል።
ከዋሺንግተን አዲስ አበባ ደርሶ መልስ
በጣና ቂርቆስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት በእንቦጭ አረም ምክንያት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ተናገሩ።
በውሃ ሀብት አጠቃቀም ላይ የሚያተኩረውና በናይሮቢ ለአለፉት ሦስት ቀናት ሲደረግ የነበረው ብሉ ኢኮኖሚ ኮንፍረንስ ዛሬ ተጠናቋል።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) እና ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) አብረው ለመስራት የውኅደት ሥምምነት ዛሬ ተፈራረሙ።
የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችና አባላት የኢትዮጵያ ዜግነት ለማግኘት አሁን የያዙትን ፓስፖርት መተው እንዳለበቸው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ በሚገኘው ወኅኒ ቤት እጅግ አሰቃቂ በተባለ በሰው ልጆች ላይ በተፈፀመ ወንጀል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን እንደተካፈሉበት የክልሉ ፕሬዚዳንት ይፋ አደረጉ።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በተማሪዎች መሃከል ዘውግ የለየ ግጭት ለመቀስቀስ የሚውጠነጠን ሴራ እንቃወማለን፤ ሲሉ ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ።
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሰላምን ለመስበክ በራሳቸው ፈቃድ የተሰባሰቡ የሰላም እናቶች ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በመገኘት ለአዲስ አበባና ለባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ስለ ሰላም ሰብከዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሰባ በላይ ፓርቲዎች ለሚቀጥለው ምርጫ እንዲዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት 3ሺህ 231 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ።
ከሁሉም የኢትዮጵያ የተወከሉ የሰላም አምባሰደር ተብለው የተሰየሙ እናቶች መቀሌ ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ