የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ በተማሪዎች መሃከል ዘውግ የለየ ግጭት ለመቀስቀስ የሚውጠነጠን ሴራ እንቃወማለን፤ ሲሉ ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ።
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሰላምን ለመስበክ በራሳቸው ፈቃድ የተሰባሰቡ የሰላም እናቶች ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በመገኘት ለአዲስ አበባና ለባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ስለ ሰላም ሰብከዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሰባ በላይ ፓርቲዎች ለሚቀጥለው ምርጫ እንዲዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት 3ሺህ 231 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ።
ከሁሉም የኢትዮጵያ የተወከሉ የሰላም አምባሰደር ተብለው የተሰየሙ እናቶች መቀሌ ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር ዛሬ ከሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጣፋ ሞሐመድ ጋር በክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።
በትግራይ ክልል ደቡብ፣ ማዕከላዊና ምዕራብ ዞናች በሚገኙ ከተሞች ትናንትናው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ተጠናቅቆ በመጭው ሣምንት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አስታውቀዋል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባቱን ያሳወቀው ትጥቁን ፈትቶ መሆኑን ቃል አቀባዩ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
“ዶ/ር አብይ ‘እንዲህ ማድረግ አለበት፣ እንዲህ ማድረግ አለበት’ የሚለውን ሳይ፤ የችግሩን መጠን የተረዳን አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ። “.. የተወሰኑ በዝርዝር ሊነግረን የማችልም የማይገቡም ነገሮች መኖራቸውን እረዳለሁ። .. ወደ ፊት መሄድ አለብን እያልን ነው። ነገር ግን ወደ ፊት መሄዳችንን በምንድን ነው የምንረዳው?” መስፍን ነጋሽ። “ኢሐዴግ እንደ ፓርቲ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት የተገደደ ይመስለኛል።” ሄኖክ የማነ።
በኢትዮጵያ በአለፉት ስምንት ወራት ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ ትላንት ሐሙስ ማታ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፤ ሰዎች በጅምላ መግደላቸውን ገልፅዋል።
በሜቴክ ላይ የተካሄደው የሙስና ምርመራ በሌሎችም ተቋማት ላይ እንደሚቀጥል የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
የትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል እንዳልሆነ ተማሪዎች ተረድተው የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።
የአህጉር ዓቀፍ የብስክሌት ውድድር በአሥመራ እየተካሄደ ነው፡፡
የፊታችን ማክሰኞ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የ2012ቱን ምርጫ ነፃና ፍትኃዊ ለማድረግ በሚያስፈልጉ የማሻሻያ ዕርምጃዎች ላይ እንደሚወያዩ ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ Thanksgiving/የምስጋና ቀን/ በመባል የሚታወቀው የምስጋና ቀን በብሔራዊ ደረጃ ይከበራል።
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር Post Traumatic Stress Disorder በመባል በሚታወቀው የአእምሮ ሁከት ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ዝግጅት ነው።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በቡድን በታጠቁ ኃይሎች ሰዎች በጅምላ እየተገደሉ ነው ሲሉ ገለፁ።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እአአ እስከ ታህሳስ 8 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ጀርመንን እንደሚጎበኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ገልጿል።
ከህዳር 2 እስከ 7 በሞያሌ በደረሰው ጥቃት ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ድጋፍ አጥተው እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾማቸው፡፡
ተዓማኒ፣ ሀቀኛ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ መነሳቱን የጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግሥት አስታውቋል፡፡
ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።
ተጨማሪ ይጫኑ