“ዶ/ር አብይ ‘እንዲህ ማድረግ አለበት፣ እንዲህ ማድረግ አለበት’ የሚለውን ሳይ፤ የችግሩን መጠን የተረዳን አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ። “.. የተወሰኑ በዝርዝር ሊነግረን የማችልም የማይገቡም ነገሮች መኖራቸውን እረዳለሁ። .. ወደ ፊት መሄድ አለብን እያልን ነው። ነገር ግን ወደ ፊት መሄዳችንን በምንድን ነው የምንረዳው?” መስፍን ነጋሽ። “ኢሐዴግ እንደ ፓርቲ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት የተገደደ ይመስለኛል።” ሄኖክ የማነ።
በኢትዮጵያ በአለፉት ስምንት ወራት ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ ትላንት ሐሙስ ማታ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች፤ ሰዎች በጅምላ መግደላቸውን ገልፅዋል።
በሜቴክ ላይ የተካሄደው የሙስና ምርመራ በሌሎችም ተቋማት ላይ እንደሚቀጥል የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
የትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል እንዳልሆነ ተማሪዎች ተረድተው የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።
የአህጉር ዓቀፍ የብስክሌት ውድድር በአሥመራ እየተካሄደ ነው፡፡
የፊታችን ማክሰኞ ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፣ የ2012ቱን ምርጫ ነፃና ፍትኃዊ ለማድረግ በሚያስፈልጉ የማሻሻያ ዕርምጃዎች ላይ እንደሚወያዩ ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ Thanksgiving/የምስጋና ቀን/ በመባል የሚታወቀው የምስጋና ቀን በብሔራዊ ደረጃ ይከበራል።
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር Post Traumatic Stress Disorder በመባል በሚታወቀው የአእምሮ ሁከት ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ዝግጅት ነው።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የያሶ ወረዳ ነዋሪዎች፣ በቡድን በታጠቁ ኃይሎች ሰዎች በጅምላ እየተገደሉ ነው ሲሉ ገለፁ።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ እአአ እስከ ታህሳስ 8 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ኬንያንና ጀርመንን እንደሚጎበኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ገልጿል።
ከህዳር 2 እስከ 7 በሞያሌ በደረሰው ጥቃት ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ድጋፍ አጥተው እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾማቸው፡፡
ተዓማኒ፣ ሀቀኛ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ መነሳቱን የጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግሥት አስታውቋል፡፡
ወደ ሰላም የተቀላቀሉትን የኦብነግ ታጣቂዎች ሰዉ ጂግጂጋ ላይ የተቀበላቸው ከአይሮፕላን ማረፊያው አንስቶ በመንገዶች ግራና ቀኝ ተሰልፎ እንደነበረ የገለፁት ቃል አቀባዩ ሄርሞጌ በእውኑ “የሞቀና የደመቀ ነበር” ብለውታል አቀባበሉን።
"ወሰንና የማንነት ጥያቄን በህገ መንግሥቱ አስመልሳለሁ" ይላል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ በቅርቡ አካሂዶት በነበረው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ትላንት ከባህርዳር ከንቲባ ጋር በተለያዮ ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ተገለፀ።
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያገናኙ የሑመራ - ኡምሓጀርና የራማ -ዓዲዃላ የመንገድ መስመሮች በቅርብ ግዜ ተከፍተው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ለማጠናከር ውይይት አመራሮች እያካሄድን ነው አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
ለውጡን ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚደክሙ እኩያን አሉ ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባ ጉለሌ የነበረውን የቀድሞ ጽ/ቤቱን ከ26 ዓመት በኋላ ዛሬ በይፋ ከፈተ።
በኢትዮጵያ የሕግ ልዕልና ለማክበር የተጀመረው ሂደት ፖለቲካዊ መልክ ይዟል አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የወልቃይት ህዝብ ማንነት እኛ የወልቃይት ተወላጆች እንጂ ሌላ አካል እንዲገልፅልን አንፈልግም ሲሉ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ይጀመራል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ የተካሄደውና በትናንትናው ዕለት የተጠናቀቀው የውጭ ጉዳዮቹ ስብሰባ በአለፉት ዓመታት ሲጠና የቆየው የሕብረቱ ማሻሻያ ሀሳብ ላይ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ