በኢትዮጵያ በአለፉት ስምንት ወራት ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ሁነቶች እየተስተዋሉ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚያገናኙ የሑመራ - ኡምሓጀርና የራማ -ዓዲዃላ የመንገድ መስመሮች በቅርብ ግዜ ተከፍተው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ለማጠናከር ውይይት አመራሮች እያካሄድን ነው አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
ለውጡን ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚደክሙ እኩያን አሉ ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባ ጉለሌ የነበረውን የቀድሞ ጽ/ቤቱን ከ26 ዓመት በኋላ ዛሬ በይፋ ከፈተ።
በኢትዮጵያ የሕግ ልዕልና ለማክበር የተጀመረው ሂደት ፖለቲካዊ መልክ ይዟል አሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የወልቃይት ህዝብ ማንነት እኛ የወልቃይት ተወላጆች እንጂ ሌላ አካል እንዲገልፅልን አንፈልግም ሲሉ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ይጀመራል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ የተካሄደውና በትናንትናው ዕለት የተጠናቀቀው የውጭ ጉዳዮቹ ስብሰባ በአለፉት ዓመታት ሲጠና የቆየው የሕብረቱ ማሻሻያ ሀሳብ ላይ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል፡፡
በትጥቅ ትግል መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንግሥት በሰላም አሳምኖ ለመመለስ ጥረት ማድረግ አለበት፤ ካለበለዚያ “መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ግዴታ ስላለበት በወሰነበት መንገድ ሁኔታውን መቆጣጠር ይችላል” ብለዋል የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት መንግሥት ለጄኔራል ክንፈ ዳኛው ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የስጠውን ትዛዝ አነሳ፡፡
"ወንጀለኞች ገና ከየጎሪያቸው ይወጣሉ" ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
“ማዕቀቡ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም” የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ። “ቀድሞውንም መሆን ያልነበረበት” የኤርትራ መንግሥት መግለጫ።
የፌዴሬሽን ም/ቤት በማንነት ዙርያ እያወጣው ያለው መግለጫ እንደ ተቋም ገለልተኛ ያልሆነና ወገንተኝነት የሚታይበት ነው ሲሉ የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀን ጨምሮ አንዳንድ የወልቃይት ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥርያቸዋለሁ ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል ይህ ጉዳይም መነጋገርያ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ አስመልክቶ የአቋም መግለጫ ያወጣ የትግራይ ክልል መንግሥት የክልሉ ህዝብና መንግሥት የህግ ልዕልና እንዲሰፍን አበርትተው ይሰራሉ ብሏል። እንዲሁም በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየታየ ያለ ሁኔታ አንድ ብሄር መሰረት እንዳያደርግ እንታገላለን ሲል ገልፅዋል፡፡
ዛሬ ከቀትር በኋላ ፍርድ ቤት የቀረቡት የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዳይሬክተር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ጠየቁ።
የቤንሻንጉል ክልል መንግሥት ከቤንሻንጉል ክልል በመጡ ታጣቂዎች የሚፈጸመውን ጥቃት እንዲያስቆም ከተለያዩ አካባቢዎች ለአቤቱታ የመጡ ሰዎች ጠየቁ።
“የቡና መገኛነታችን ይከበርልን” በሚል የሚነሱ ጥያቄዎች ለውዝግብ ምክንያት ሊሆኑ እንደማይገባ አንድ የቀደሞ የፓርላማ አባል አሳሰቡ፡፡
በኤርትራ መንግሥትና ባለሥልጣናት ላይ የተነጣጠረው ማዕቀብ እንዲነሳ በብሪታንያ ተረቆ የቀረበውን ሃሳብ የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው ውሳኔው በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል።
አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኤምባሲውን “ኤምባሲያችን” እያሉ ሲጠሩ መስማት የብርቅ ያህል እየሆነ ነው።
የአሜሪካ ድምፁ ተወልደ ወልደገብርዔል ወደ ኤርትራ ተጉዞ የተለያዩ ሥፍራዎችን ተመልክቷል።
የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ-ብሄር መሆን ብዙዎችን ያስደሰተ ዜና ሆኖ መሰንበቱ ይታወሳል።
የብሄራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄነራል ክንፈ ዳኘው የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) አንድ ፓርቲ ሆነው በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
ሰመጉ መብቶችን በሚጥሱ ኃይሎች ላይ መንግሥት እየወሰደ ነው ያለውን እርምጃ፣ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማልያ መሪዎች ስለአካባቢያቸው ሰላምና ምጣኔ ኃብት መምከር በአፍሪካ ቀንድ ለሚታየው የስደትና የድኅነት ማዕበል መረጋጋት ይፈጥራል ሲሉ አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ