የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለአሥራ ሰባት ቀናት ያህል ተሰብስቦ ስህተቶቹንና ድክመቶቹን ገምግሞ፣ በችግሮቹ መንስዔ ላይ መክሮ የሃሳብ አንድነትና መተማመን ፈጥሯል የሚል መግላጫ ማውጣቱ ይታወቃል። ሊወስዳቸው ስላቀዳቸው እርማቶችና እርምጃዎችም ዘርዝሯል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የተመሰረተባቸው ክስ ተቋርጦ ዛሬ መፈታታቸው ታወቀ፡፡ አያሌ ደጋፊዎቻቸው እና የኦፌኮ አባላት በቤታቸው አካባቢ በአጀብ ተቀብለዋቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለይፋ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል፡፡
ኢራፓን ጨምሮ አሥራ ሥድስት ሀገርቀፍ ፓርቲዎች ከገዢው ኢህአዴግ ጋር እያካሄዱ ባሉት ድርድር እስካሁን የተገኘ ውጤት አለ? ወይስ በራሱ በድርድሩ ሳቢያ ቀውስ ውስጥ የገቡ ፓርቲዎች አሉ?
ኢህአዴግ እሥረኞችን ለመፍታትና ማዕከላዊን ለመዝጋት በወሰደው አቋም ወላዋይነትን አሳይቷል ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/እና ሰማያዊ ፓርቲ ነቅፈዋል።
ከነገ በስተያ ከሚለቀቁት መካከል ከአንድ ዓመት በላይ እሥር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታየው አለመረጋጋት ምክንያቱ ‘የሕገ መንግሥቷ አንቀፅ 39 ነው’ ሲሉ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አስታውቀዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ ጉርሜሳ አያኖ በምስክርነት የቆጠሯቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳይቀርቡ ወሰነ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው የሀገራት የፀጥታ ሁኔታ ደረጃ ኢትዮጵያን የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚያስፈልግባቸው ተርታ መድቧል፡፡
የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ስድስት የሙስሊም ጉዳዮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በአመክሮ ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ።
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት ሦስተኛ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የውጭ ጉዲፈቻን የሚከለክል ሕግ አፅድቋል፡፡ በዚህም መሠረት የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በጉዲፈቻ መውሰድ አይችሉም፡፡
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በደራሼ ወረዳ የአመራር አባሎቹ የድርጅቱን ልሣን ጋዜጣ በማሰራጨታቸው እና በመሸጣቸው ምክንያት መታሰራቸውን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መሪዎችንና ሌሎችን ግለሰቦች ለመፍታት የደረሰበት ውሳኔ የሚያበረታታ ነው ሲል የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፀጥታና ከጉብኝት አመቺነት አንፃር የዓለም ሀገሮችን በአራት ምድብ የሚያስቀምጥ አሠራር ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡
የአባ ሙሴ ዘርዓይ ስም የሊቢያን በረሃና የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን ለሚገቡ ስደተኞች በተለይም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስደተኞች ትልቅ ዋጋ አለው።
ወደ ኢጣልያ የሚገቡ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ይምሰል እንጂ ከፈረንሣይ ጋር በምትዋሰነው ውቢቱ ቬንቲሚግሊያ ከተማ ያለው ሁኔታ ግን የሚያሳየው እንደዚያ ዓይነቱን እውነት አይደለም።
መንግሥት ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለዲሞክራሲ መስፈን ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር እንዲያሳይ ሰመጉ ጠየቀ፡፡
ሱዳን ከኤርትራ ጋር ያላትን ድንበር ዘግታለች።
ለ18 ቀናት ስብሰባ የተቀመጠው ገዢው ፓርቲ በመጨረሻ ቅዳሜ ዕለት ያወጣውን የጹሑፍ መግለጫ በተመለከተ የተለየያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምሕርት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አበባው አያሌው ከአዲስ አበባ፣ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዋሽንግተን ዲሲና አቶ ገረሱ ቱፋ ከአምስተርዳም በመግለጫው ላይ ተወያተዋል።
የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው አቶ ያሬድ ኃይለማርያምና የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሐፊው በፍቃዱ ኃይሉ በየትኛውም ቋንቋ ቢገለፅ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው እንኳን በግልፅ የማይታወቅ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን ይናገራሉ።
እስረኛ መፍታትና ማዕከላዊን መዝጋትን የተመለከተው የኢሕአዴግ መግለጫ በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ትርፍ ሊያስገኙ የሚችሉ በፖለቲካው ዓለም ሁለት ስስ ጉዳዮች የተመረቱበት እንደሆነ የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ይናገራል። "ከማሰር ይልቅ መፍታቱ ሕግና ደንብን መከተል እንዳለበት እየተነገረን ነው" የምትለው ደግሞ የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ ናት። የውይይቱን ሙሉ ክፍል አድምጡት።
በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተወለደው ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ረቡዕ ታኅሣሥ 25 ቀን 2010 ዓ.ም በናይሮቢ ከተማ ላንጋታ በተሰኘው ቦታ ልክ በ40ኛ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ዛሬ አርብ ታኅሣሥ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ በኮልፌ እስላም መቃብር የቀብር ሥነ ስርዓቱ ተፈጽሟል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በእሥር የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት እነ አቶ ጉርሜሳ አያኖ በምክርነት በቆጠሩዋቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አቀራረብ ላይ ውሳኔ እንዳልደረሰለት አስታወቀ፡፡
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ተጨማሪ ይጫኑ