ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ አገሮች የተመዘገበዉ የኢኮኖሚ እድገት ድህነትን በሚፈለገዉ መጠን አልቀነሰም ሲሉ አንድ የዓለም ባንክ ባለሙያ ተናገሩ።
የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በስብሰባዎቻቸዉን ከቀን ይልቅ በምሽቱ እንዲያደርጉ ዉሳኔ መተላለፉ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች የሚሳተፉበትን የሰርከስ ትርዒት እያስተናገደች ነው። በትርዒቱ ላይ ሚዛን መጠበቅ፥ ጂምናስቲክ፥ ኳስና ዱላ የመሳሰሉትን ወደ ሰማይ እያፈራረቁ በመወርወር መቅለብና ሌሎች ጨዋታዎች ቀርበዋል።
ገንዘቤ ዲባባ የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ተባለች
በኦሮሚያ - ጊንጪ ከተማ ህዳር ዘጠኝ ቀን የጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም በምዕራብ ወለጋ ሁለት ከተሞች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ሁለተኛ ጉባዔ ዛሬ ተፈፅሟል።
በአንዳንድ የምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ሰላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡
የመረጃ ነፃነት የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረጋገጥና ሌሎች መብቶች መከበር መሣሪያ እንደሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ አሳስበዋል።
በድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን እየተደረገ ያለው ድጋፍ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተለው ብሔራዊ ኮሚቴ ፀሐፊ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ሁለተኛ ጉባዔ በአገሪቱ እየተስፋፋ ካለው ከፍተኛ ትምህር የሚገኘው ጠቀሜታ ስለሚያድግበት ብልሃት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ተገልጧል።
ከሰላሳ በላይ ዓመታት፤ ከስድስት በላይ ቤተሰቦችና ልጆቻቸው የምሥጋና ቀን አከባበር ልማድና ወግ፤
በኢትዮጵያ እንደሚጨምር ከሚጠበቀዉ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር አንጻር ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች፣ ሌሎች አጋሮች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸዉን አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ አስታወቁ።
የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን ድርጅት(CPJ) ትናንትና ማታ በዓለም አቀፍ ዙሪያ መረጃ የብዙኅን ነፃነት እንዲከበር ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ሽልማት በኒው ዮርክ አበረከተ።
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
በኢትዮጵያና በኬንያ ወሰን አቅራቢያ ሰሞኑን በተገደሉት የኬንያ ፖሊሶች ላይ ደፈጣ አለማካሄዱን፤ ኬንያ ውስጥም እንደማይንቀሣቀስ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለቪኦኤ ገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት መንግሥታቸው በስምምነቱ በተጥቀሰው መሰረት ሃይሎቹን ከመዲናዋ ከጁባ ማስወጣት መጀመሩን ይፋ ባደረገበት በትናናንትናው ዕለት ነው።
በኢትዮጵያ በኤልኚኞ ምክንያት ሊከስት ለሚችል የጎርፍ አደጋ የጥንቃቄ እቅድ መነደፉ ተገለጸ።
ዝርዝሩን ለሁለት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የምጣኔ ሀብት አማካሪ ንዋይ ገብረዓብ በዚህ ቃለ ምልልስ ያስረዳሉ።
ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ታውቋል።
የዓለም አቀፍ እርዳታና ልማት መድረክ ዳይረክተር ሶንያ ሩትዘል (Sonja Ruetzel) የመድረኩን ዓላማና እአአ በየካቲት ሁለትና ሦስት በአዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማእከል የስብስባ ፕሮግራሙን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።
“የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያን ድንበር ዘልቀው ሦስት የኬንያ ፖሊሶችን ገደሉ” ሲሉ የኬንያ ጋዜጦች ፅፈዋል፤ የሃገሪቱ ፖሊስ ግን ሰዎቹን የገደሉት የኢትዮጵያ ታጣቂ አማፂያን እንጂ የመንግሥቱ ወታደሮች አይደሉም ይላል፡፡
ዓለም በመጭዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ ቲቢን ለመፈፀም የሚያስችል ዕቅድ ይዟል፡፡
አሜሪካ ወደሶሪያ ወታደሮች ባስችኩዋይ ልትልክ የጸረ ኣይሲስ ህብረት ልዩ ልዑኩ ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ