ባለፈው ህዳር 27 ቀን 2007 አም. በየመን ዐልማካ ወደብ አጠገብ በደረሰ የጀልባ መስመጥ አደጋ 70 ኢትዮጵያውን መሞታቸውን የጠቀሱ የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች የተሳሳቱ መሆነቸውን አረጋግጫለሁ ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ኢህደግ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን ምርጫ ነጻና ሰላማዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የአስልጣኞች ስልጠና ለከፍተኛ አመራሮቹ እየሰጠ ነው።
ኒዮሊበራል ሀይሎች በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ምርጫ ከ 10 አመታት በፊት እንደሞከሩት ሁሉ የቀለም አብዮት ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ነው ሲሉ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሰሱ።
ወደ ምዕራብ አፍሪካ የዘመቱት የጤና ባለሙያዎች ሲመለሱ የሃያ አንድ ቀናት ኳራንታይን ላይ እንደሚቀመጡ (ተነጥለው እንደሚቆዩ) ተገልጿል፡፡ እስከ ዛሬ በኢቦላ የተጠረጠረ ሰው ከውጭ ከገባ መንገደኛም ሆነ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
Ethipia - ebola update - 12-22-14
አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። 187 ኢትዮጵያውያን የህክምና ሰራተኞች ምዕራብ አፍሪቃ ገቡና የዴንማርክ ኢሚግረሽን ስለ ኤርትራ ያወጣው ዘገባ ተነቀፈ የሚሉት ይገኙባቸዋል።
IOM በሚል አህጽሮት የሚታወቀው አለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት በያዝነው ወር የሚያበቃው 2014 አም ግጭትን፣ የፖለቶካ ወከባንና የኢኮኖሚ ችግርን በመሸሽ ለሚሰደዱት ሰዎች አደገኛ አመት ሆኖ እንደቆየ አስታውቋል።
በጁባ ጭፍጨፋ የተፈጸመበት አንደኛ ዓመት ያሉትን በጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች ፕሬዚደንት ሳልቫኪር ማያርዲት የኑዌር ተወላዶችን ለይተዉ አጥቅተዋል ሲሉ ወንጅለዋል።
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ባለው ዘመቻ የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት አደርጋለሁ አለ። ፓርቲው በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሩን መዘርጋቱናን በየትኛውም ደረጃ የምክር ቤት እጩዎችን ለማቅረብ እንደሚችል ገልጿል።
Ethiopia - Ebola - medics - farewell
ተጨማሪ ይጫኑ