የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዲዮስ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የአምቦ ከተማ ዘጋቢያችን ናኮር መልካ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የወሎው ዘጋቢያችን መስፍን አራጌ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተሰጠው የኖቤል ሽልማቱን ለመደገፍ እሁድ ዕለት በተለያዩ ቦታዎች ከተደረጉት ሰልፎች መካከል በድሬደዋ እና በአምቦ ከተማ የተሳተፉ ሰዎች የሰጡት አስተያየት።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት።
የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የባህርዳሯ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናው በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የመቐሌው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አፅብሃ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሁለት ቀናት ልዩነት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰሜን ሶሪያ ውስጥ የሚዋጉትን ኩርዶች ሲረዱ የነበሩትን አሜሪካውያን ወታደሮች በማስወጣታቸው ሲነቀፉ ሰንብተዋል ። አሁን ደግሞ በአካባቢው ወታደራዊ ዘመቻዋን እያፋፋመች ባለችው በቱርክ ላይ ማዕቀብ ሊጣልባት ይችላል ለዚያም ዝግጅት ተደርጉዋል እያሉ ናቸው።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳይታ ዱብቲ አካባቢ የውጭ አገር መታወቂያና ተሽከርካሪ ይዘዋል የተባሉ ታጣቂዎች ከትላንት በስቲያ ሰነዘሩት በተባለው ጥቃት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የአዲስ አበባ ባለደራ ምክር ቤት መሆኑን የሚናገረው ቡድን በስድስት ነጥቦች ዙሪያ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።
የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ (አዴፓ) የህዝቡን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆም ተፎካካሪው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ (አዲሀን) አስታወቀ።
የግብርና ሙያ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ያልተሰራበት ዘርፍ ነው ትለናለች ኖላዊት ሺመልስ
ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን የአማራ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረንና የኦሮምያ አቻቸውን ኮሎኔል አበበ ገረሱን ጋብዟል።
ምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታትና አካባቢውንም ወደመረጋጋት ለመመለስ “ትርጉም ያለው ሥራ ተከናውኗል” ሲሉ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ተናግረዋል። የምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ለአንድ ቀን ያካሄዱት የፀጥታ ግምገማ ድሬ ዳዋ ላይ ተካሂዷል። ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚስተዋለው የሰላም እጦትና አለመረጋጋት ተጠያቂው የኢህአዴግ አመራር ነው ሲል የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው መቀሌ ላይ ለአራት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ “የግንባሩ አመራር ከፓርቲው እምነትና ፕሮግራም ውጭ እየሄደ ነውም” ብሏል ። “ኢህአዴግ ውሁድ ፓርቲ ሊሆን ነው” ስለሚባለውም ኮሚቴው ሲናገር “የግንባሩ አባል ድርጅቶች በተለያየ አቅጣጫ እየተጓዙ ባሉበት ጊዜ የማይታሰብ ነው” ብሏል።
የደቡብ ሱዳንን ለአምስት ዓመታት የዘለቀ የርስ በርስ ብጥብጥ ለማስቆም ያስችላል የተባለውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ጥቂት ሳምንታት ሲቀሩት የሃገሪቱ የሃይማኖትና ሲቪክ መሪዎች የሚሣተፉበት የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ሊካሄድ ታቅዷል።
ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ግጭት ያጋጥም የነበረባቸውን የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ ቦታዎች ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በጋራ ውይይት ተደረገ። የሁለቱም ክልል ርዕሰ-መስተዳደሮች በአንድ መድረክ ተገናኝተው ፤ አብሮነትን ለማሻከር ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን ኃይሎች ለመታገል እንደሚሠሩ አስታወቁ።
ከዋሺንግተን አዲስ አበባ ደርሶ መልስ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቀድሞ ኢንሳ በሚል ምህጻረ ቃል የሚጠራው የመረጃ ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት የቀድሞ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይን በቁጥጥር ስር ያላዋለው በምርመራ መዝገቡ ውስጥ ስለሌሉ እንደሆነ አስታወቀ። በተጨማሪም ከፍተኛ ምዝበራ በመፈፀምና የሰብዓዊ መብትን በመጣስ ጠርጥሮ ያሰራቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬን ያነጋግረቸው ጽዮን ግርማ ተጨማሪ አላት።
በጂግጂጋ 200 ሰዎች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር መኖሩ ለፖሊስ ጥቆማ ደርሶታል። ፖሊስ ጥቆማውን ተቀብሎ እያጣራ መሆኑን ለፍርድ ቤት አስረድቷል። በሐምሌ ወር ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ የ50 ሰዎች አስክሬን በሦስት ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሮ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።
መንግሥት በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሙስና ተጠርጣሪዎች ላይ የወሰደ እርምጃ ተገቢ መሆኑን የገለፁ ጠበቆችና የቀድሞ እስረኛ “ከዚህ የተሻለ ጠንካራ እርምጃ” እንጠብቃለን ብለዋል።
አንድን አገር የተረጋጋችና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ለማድረግ የመንግሥት ግዴታና ኃላፊነት መሆኑን አንድ የሕግ ባለሞያ ገለፁ።
የሸገር 102.1 የለዛ የሬድዮ ፕሮግራም አመታዊ ሽልማት ከሁለት ቀናት በፊት ለስምንተኛ ጊዜ ተካሄዷል ። ዘንድሮ በ9 የሽልማት ዘርፍ በሕዝብ ድምፅና በዳኞች ለታጩ የጥበብ ሰዎች ሽልማትን ሰጥቷል። አዘጋጁንና ጥቂት ተሸላሚዎችን አነጋግረናል።
ተጨማሪ ይጫኑ