ኬንያ ደዳብ ስደተኞች መጠለያ የሚኖሩ ስደተኞች በኬንያ በተለያዩ ቦታዎች የሽብር ጥቃት ሲፈፀም ስደተኛውም ላይ እንግልት እንደሚደርስበት ተናገሩ፡፡
ኬንያ ውስጥ ከአራት ዓመታት በፊት በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ የሚበዙት ተማሪዎች የሆኑ አንድ መቶ አርባ ስምንት ሰዎች የገደሉ አክራሪ እስላማዊ ታጣቂዎችን በመርዳት የተከሰሱ ሦስት ወንዶች በኬንያ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል።
የሱዳኑን ተቃውሞ የሚያስተባብሩት ቡድኖች፣ ሌሊት ሌሊት የተቃውሞ ሰልፎቹ እያካሄድ የጦር ሰራዊቱ ሥልጣኑን ለሲቪላዊ አስተዳደር እንዲያዛውር መታገላቸውን ሊቀጥሉ አቅደዋል።
ትናንት ያረፉት የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሞርሲ ቀብር ተፈፀመ።
በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቃዊ ቦርኖ ክፍለ ግዛት በደረሱ ሦስት አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቶች ቢያንስ ሰላሳ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሊሎች አርባ ሰዎች እንደቆሰሉ ተገለፀ።
የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙርሲ በዛሬው ዕለት ማረፋቸውን የመንግሥቱ ቴሌቭዢን አስታወቀ።
ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ከሃያ ስምንት ዓመታት በፊት የዘጋችውን የዓለምቀፍ ልማት ዕርዳታ ቋሚ ሚሽን ልትከፍት ነው።
ዓለምቀፍ ዕውቅና ያላቸው የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋዬዝ አል ሴራጅ ከተቃናቃኛቸው ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ እንዳልሆኑ አስታውቀዋል።
ለሱዳን የወቅቱ ሁኔታ እየተፈለገ ላለው መላ የዩናይትድ ስቴትስን አጋዥ ተሣትፎ ለማሳየት ያስችላል የተባለ ጉብኝት የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትሯ ቲቦር ናዥ እያደረጉ ናቸው።
በኤርትራ መንግሥት ላይ የሚካሄደው ዓለምአቀፍ ክትትልና ፍተሻ እንዳይቆም ሰላሣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል።
ባለፈው ዕሁድ በማዕካላዊ ማሊ በሚገኝ መንደር ላይ በተፈፀመ ቢያንስ 35 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት በዘር ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። ነገር ግን እስላማዊ አማፅያን የሀገሪቱ ክፍሎችንና የድንበሩን አከባቢ የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው የዘር ግጭትንና የጂሐድ አሸባሪነትን ለመለያት አስቸጋሪ መሆኑ ተገልጿል።
ኡጋንድ ውስጥ አንድ ልጅ በኢቦላ በሽታ መሞቱ ታውቋል። በኡጋንዳ ጎረቤት ሀገር ኮንጎ ከአንድ ዓመት በፊት ኢቦላ የገባ ሲሆን የድንበር ዘለል ጉዳይ እንደሆነ ተመልክቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛው ዲፕሎማት ቲቦር ናዥ በዚህ ሳምንት ብጥብጥ ላይ ወደምትገኘው ወደ ሱዳን እንደሚጓዙ ተገልጿል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በገለፀው መሰረት የሱዳን መንግሥት ኃይሎች በዳርፉር ክልል አዲስ ተከታታይ የጦርነት ወንጀል በመፈፀም ተግባር ተጠያቂ ናቸው።
ቦትስዋና የተመሳሳይ ፆታ ፍቅረኝነት ወንጀል እንዳይሆን ወስናለች። ከሰሀራ በመለስ ያሉት በርካታ ሃገሮች የተመሳሳይ ፆታዎች ወሲብ ወንጀል እንዲሆን የሚያደርጉ ህጎች አሏቸው።
ዛሬ በማዕከላዊ ማሊ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 95 ሰዎች እንደተገደሉ ታውቋል። የታጠቁ ሰዎች ሌሊት በህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው መኖርያ ቤቶችን በእሳት አጋይተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሱዳንን በሲቪል የሚመራ መንግሥት እስክታቋቁም ከማናቸውም እንቅስቃሴዎቼ አግጃታለሁ ሲል አስታወቀ።
ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ውስጥ በኢቦላ ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሺህ መብለጡን የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ትሪፖሊ ውስጥ ግጭት በመበባሱና የፀጥታ ሁኔታው እየከፋ በመሄዱ 149 የሚሆኑ ለአደጋ የተጋለጡ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ሮም ተወስደዋል።
ሱዳን ውስጥ ከአምስት ዓመታት በፊት በሌለበት የሞት ቅጣት የተፈርደበት የሱዳን አማፅያን መሪ ወደ ሀገሩ ተመልሷል። የሱደን ወታደራዊ ጁንታ ከሀገሪቱ እንዲወጣ ቢጠይቀውም አልወጣም ማለቱ ተዘግቧል።
የሞዛምቢኩን የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር እንዲላኩላት ለጠየቀችው ለዩናይትድ ስቴትስ ሳይሆን ለሀገራቸው ለሞዛምቢክ አሳልፈን እንሰጣለን ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የፍትህ ሚኒስትር አስታወቁ።
ከበርካታ ዓመታት በፊት በሶማሊያ ብሄራዊ የጦር ሰራዊት ውስጥ በኮሎኔልነት ያገለገሉ አንድ ሰው እኤአ በ1987 በአንድ ታዳጊ ወጣት ላይ የማሰቃየት ተግባር በመፈፀም በዩናይድት ስቴትስ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ተሰጥቷቸዋል።
የማላዊ ህዝብ ዛሬ ፕሬዚዳንቱንና የፓርላማ ተወካዮቹን ምርጫ ሲያካሂድ ውሉዋል። ፕሬዚዳንቱ ፒተር ሙታሪካ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን በዕጩነት ቀርበዋል።
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በብዙ መቶዎች ለሚቆጠሩ እስረኞች ምህረት አድርገዋል። ከእነሱም አንዱ በሀገሪቱ ፅኑ መሰረት ያለውን ክፍል በመንቀፉ የታሰረ ዕውቅ ጋዜጠኛ ይገኝባቸዋል።
ካርቱም ውስጥ ትላንት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተካሄደ ግጭት ቢያንስ ሥምንት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ የሱዳን ገዢ ወታደራዊ ካውንስል ከሲቪል የተቃውሞ መሪዎች ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ንግግር አቋርጧል።
ተጨማሪ ይጫኑ