ሳይክሎን ኢዳይ በመባል በሚጠራው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በተመታችው ሞዛምቢክ በገባው የኮሌራ በሽታ፣ እስከ ትናንት ሐሙስ ባለው አኃዝ፣ የሟቾች ቁጥር ከ5 ወደ 139 ማደጉ ተገለፀ።
የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ዛሬ ወደ ሞዛምቢክ ማምራታቸው ተሰማ። የዳይሬክተሩ ጉዞ ዓላማ፣ በቅርቡ ሳይክሎን ወይም ከባድ አውሎ ነፋስ በደቡባዊ ምሥራቅ የአፍሪካ ክፍል በሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌና ማላዊ ውስጥ ያደረሰውን ውድመትና አደጋ ለመመልከት መሆኑም ታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ደቡባዊ አፍሪካዊቱን ሃገር ሞዛምቢክን በመታት ዝናብ አዘል ማዕበል ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ።
ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በየዕለቱ ለሚያደርገው መደበኛ በረራ ዛሬ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ተነስቶ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሕይወት የተረፈ ማንም እንደሌለ ተረጋግጧል።
ሞቃዲሾ ውስጥ ከሶማልያው ፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ከሚገኝ ምግብ ቤት ውጭ ዛሬ የደረሰ የመኪና ቦምብ ፍንዳታ በትንሹ ለ5 ሰዎች ሕይወት መጥፋትና ሌሎች ዘጠኝ መቁሰል ምክንያት መሆኑ ተገለፀ።
ለበርካታ ዓመታት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኸን ዛሬ እንደገና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተመልሰው ለደኅንነት ኮሚቴው የምስክርነት ቃል ይሰጣሉ። ኮሚቴው በዚህ ሳምንት በትረምፕ አስተዳደር ላይ አዲስ ምርመራ በከፈተውና ዲሞክራቶች በተቆጣጠሩት የተወካዮች ምክር ቤት ከሚገኙ በርካታ ኮሚቴዎች አንዱ ነው።
በየካቲት 17ቱ የሴኔጋል ምርጫ ፕሬዚዳንት ማኪ ሣሊ ማሸነፋቸውን የሃገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት አስታወቀ።
ኬንያና ሶማልያ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ።
የሶማሊላንዷን የወደብ ከተማ በርበራን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ አውራ ጎዳና ሊሠራ ነው።
ሰሜን ምዕራባዊ ኬንያ ውስጥ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት አሜሪካውያን እና ኬንያዊው አብራሪ ሞቱ።
ሶማልያ ውስጥ በተካሄደ ጥቃት የሃያ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተገለጸ።
በሴኔጋሉ ምርጫ ዛሬ ሐሙስ ይፋ በሆነው ጊዜያዊ ውጤት መሠረት፣ ማኪ ሳል እንደገና አሸናፊ ሆነዋል።
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ዛሬ በተናገሩት ቃል፣ ምንም እንኳ ተቀናቃኛቸው ቅሬታ ቢኖራቸውም፣ ለሌላ አራት ዓመት ለሥልጣን ያበቃቸው የአሁኑ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግን ምንም ውዝግብ እንደሌለበት አስታወቁ።
በግብፅ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች መሠረት ካይሮ በሚገኘው ዋናው የመንገደኞች ማመላለሻ ባቡር ማዕከል በደረሰ ግጭት፣ 20 ሰዎች ሞቱ፡፡
ናይጄሪያውያን ባለፈው ቅዳሜ ባካሄዱት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየገባ ያለው የድምፅ ውጤት እንደሚያሳየው ሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ እየመሩ ናቸው። ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ግን የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው በማለት ውድቅ አድርጓል።
የአል-ሻባብ ነውጠኞች ዛሬ ሰኞ ሞቅዲሾ አካባቢ ባካሄዱት ጥቃት ዘጠኝ ሲቪሎችን እንደገደሉ፣ የሶማልያ ባለሥልጣናት ገለፁ።
ባለፈው ቅዳሜ የተካሄደው የናይጀርያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምፅ ቆጠራ እንደቀጠለ ሆኖ፣ ውጤቱ ተቀራራቢ በመሆኑ ትናንት ዕሑድም የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ክፍት ሆነው መዋላቸው ተገለፀ።
ስለ አፍሪካ
ናይጄሪያ ለአንድ ሳምንት እንዲዘገይ የተደረገውን ሀገርቀፍ ምርጫ በምትካሂድበት በነገው ዕለት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ፀጥታ የተጠበቀ እንደሚሆን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ።
የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት እንዳመለከተው የሶማሌ ላንድ ድርቅ ሊቀጥል እንደሚችል፣ ሰባት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ሰው በረሃብ ሊመታ እንደሚችል ስጋቱን አሰምቷል።
እንዲቀር ለማድረግ የሚያስችሉ ተጨማሪ ዕርምጃዎች ካልተወሰዱ አንድ የልጃገረዶች ትውልድ ትምህርት ሳያገኝ ሊቀር እንደሚችል፤ ሴቶች በወሊድ ወቅት እጅግ ለበረቱ የጤና ሁከቶች፣ ለፆታና ለቤት ውስጥ ጥቃቶች ሊጋለጡ እንደሚችሉ ኦክስፋም የሚባለው የእንግሊዝ ግብረሰናይ ድርጅት አስጠነቀቀ።
የዩጋንዳ ገዢ ፓርቲ የፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒን እኤአ በ2021 በሚካሄደው ምርጫ የፓርቲው ዕጩ እንዲሆኑ ወሰነ።
በናይጀርያ ነገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል።
ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማሻሻል ያለመው የአንድ ዓመት ፕሮጀክት እያለቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ተጨማሪ ዕርዳታ የሃገሪቱን ምጣኔ ሃብት ያሳድጋል፤ ከእአአ 2018 ጀምሮ ፈጣን ለውጥ እየታየ ባለበት በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ሥፍራ ያጠናክራል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
በደቡብ ሱዳን የዬኢ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ ግጭቶችን ሽሽት ባለፉት ሁለት ሣምንታት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ብዙ ሺህ ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ወቅት ያለምግብና ውሃ እየተሰቃዩ ናቸው።
ተጨማሪ ይጫኑ