ካርቱም ውስጥ ትላንት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተካሄደ ግጭት ቢያንስ ሥምንት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ የሱዳን ገዢ ወታደራዊ ካውንስል ከሲቪል የተቃውሞ መሪዎች ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ንግግር አቋርጧል።
”…ጥላሁን ገሰሰ ‘ልብ ላይ ነው ወይስ ጉበት .. ፍቅር ሲይዝ የሚያድርበት?’ ብሎ ድሮ ሥሜት የሚመነጨው ከልብ ውስጥ ነው የሚል ግምት ነበር። አሁን በእርግጥ ይታወቃል። ሥሜትና ሃሳብ የማመንጨት ሥራ የአንጎል ነው።” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ የሥነ ልቦና፣ የነርቭና የአዕምሮ ህክምና ልዩ ባለሞያና ተመራማሪ።
የሶማሊያ የፖሊስ ክፍል በገለጸው መሰረት አንድ አጥፍቶ ጠፊ ሞቃዲሾ በሚገኘው ዋርዳ ናባዳ ወረዳ በሚገኘ መሥርያ ቤት ላይ ዛሬ ባደረሰው ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለዋል።
በአዲስ መልክ የተደራጀው የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት ከተፈረመ መንፈቅ ቢያልፈውም እስካሁን አንድም የፖለቲካ እስረኛ እንዳልተለቀቀ ተመድ ያወጣው አዲስ ሪፖርት አመለከተ።
በስድስት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በካብድ ዝናባማ አውሎ ንፋስ በተመታችው ሞዛምቢክ፣ የሰሜናዊ ክፍለ ግዛት ዛሬም በዝናቡ የጎርፉ አደጋ ይባባሳል ተብሎ ተፈርቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትሪፖሊ ውስጥ በመንግሥት እሥር ቤት የነበሩ ሊብያውያን ስደተኞችን ከቦታው አስወጥቷል። አንዳንዶቹ በእስር ቤቱ ሥላለው መጥፎ ሁኔታ ተቃውሞ በማሰማታቸው ጥቃት ደርሶብናል ካሉ በኋላ ነው የመንግሥታቱ ድርጅት እርምጃውን የወሰደው።
በደቡብ ሱዳን ወደሚገኘው ፋንጋክ ከፍለ ግዛት ያመራ የነበረ የምግብ ረድዔት የጫነ ጀልባ ባለፈው ዕሁድ ተገልብጦ መስመጡን አንድ የጀልባ ሰራተኞች ማኅበር ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ተናግረዋል።
የሱዳን የሽግግር ወታደራዊ መማክርት መንገዶቹ አሁኑኑ እንዲከፈቱና መሰናክሎቹ እንዲነሱ የጠየቀ ቢሆንም የሱዳን የተቃውሞ መሪዎች ካርቱም ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በህንድ ውቅያኖስ ላይ እየታየ ያለው አዲስ የትሮፒካል ሳይክሎን ወይም ከባድ አውሎ ነፋስ የተቀላቀለበት ማዕበል በያዝነው ሳምንት ኮሞሮስን፣ ሞዛምቢክንና ታንዜንያን ሊያተራምስ እንደሚችል ተተነበየ።
የማሊው ጠቅላይ ሚኒስትር ሱሜሉ ቡቤዬ ሜጋ እና መላ መንግሥታቸው ትላንት ሥራውን ለቋል።
በአፍሪካ የአራት ቀናት ጉብኝት ያደረጉት የዋይት ሃውስ ከፍተኛ አማካሪ ኢቫንካ ትረምፕ በትናንት የአይቮሪ ኮስት ውሏቸው በሴት ሥራ ፈጣሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተው ተናግረዋል።
የሊብያው አፈንጋጭ ጄነራል ኻሊፋ ሃፍታር ኃይሎች ዋና ከተማዪቱን ትሪፖሊን ለመቆጣጠር ውጊያ ከጀመሩ ወዲህ እጅግ ብርቱው የተባለ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊብያ ልዑክ ጋሳን ሳላሜ አስታወቁ።
ባለፈው ሣምንት በጦር ጄነራሎቻቸው ከሥልጣን ለተወገዱት የሱዳን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሺር ጥገኝነት ልትሰጥ እንደምትችል ዩጋንዳ ዛሬ አስታወቀች።
የሞዛምቢክ የቀድሞው የገንዘብ ሚኒስትር ማኑኤል ቻንግ ፍርድ ፊት እንዲቆሙ ለዩናይትድ ስቴትስ ወይም ለሞዛምቢክ ተላልፈው እንዲሰጡ አንድ የደቡብ አፍሪካ ዳኛ ወሰኑ።
ፎቶ ሪፖርታዥ - በደቡብ ሱዳን ላይ ከመከረው የቫቲካን መንፈሣዊ ጉባዔ የተወሰዱ ምስሎች። ይመልከቷቸው።
የደቡብ ሱዳንን ለአምስት ዓመታት የዘለቀ የርስ በርስ ብጥብጥ ለማስቆም ያስችላል የተባለውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ጥቂት ሳምንታት ሲቀሩት የሃገሪቱ የሃይማኖትና ሲቪክ መሪዎች የሚሣተፉበት የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ሊካሄድ ታቅዷል።
በሱዳን ለወራት የዘለቀው ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ ባሳለፍነው ሳምንት ማብቂያ ላይ በሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች በወታደራዊ ጦር ሠፈሮች ደጃፍ የመቀመጥ አድማ በመምታታቸው ወደ ከፋ ደረጃ አድጓል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉ ማግስት የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን እና የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም ባልደረባ የነበሩት ሻ/ቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ወደ ርዋንዳ -ኪጋሊ ተላኩ፡፡‹‹በሰው ልጅ ጭንቅላት ሊዳሰስ፣ሊታወቅ (ሊገመት) ›› የማይችል ሲሉ የሚገልጹትን ግፍ በዐይናቸው ለማየት ቻሉ፡፡
ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሳምንት መጫረሻ ላይ በተካሄደው ግጭት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የሀገሪቱ የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትር ዛሬ ለምክር ቤት ተናግረዋል።
ሊብያ ውስጥ አንድ ተዋጊ አውሮፕላን ዛሬ ትሪፖሊ በሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ድብደባ ማካሄዱን እማኞችና የጸጥት ኃይሎች ተናግረዋል።
ኤርትራ ውስጥ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ምን እንደሆኑ ወይም የሚገኙበትን ሁኔታ መንግሥቷ እንዲያሳውቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ጠየቁ።
ሳይክሎን ኢዳይ በመባል በሚጠራው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በተመታችው ሞዛምቢክ በገባው የኮሌራ በሽታ፣ እስከ ትናንት ሐሙስ ባለው አኃዝ፣ የሟቾች ቁጥር ከ5 ወደ 139 ማደጉ ተገለፀ።
የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ዛሬ ወደ ሞዛምቢክ ማምራታቸው ተሰማ። የዳይሬክተሩ ጉዞ ዓላማ፣ በቅርቡ ሳይክሎን ወይም ከባድ አውሎ ነፋስ በደቡባዊ ምሥራቅ የአፍሪካ ክፍል በሞዛምቢክ፣ ዚምባብዌና ማላዊ ውስጥ ያደረሰውን ውድመትና አደጋ ለመመልከት መሆኑም ታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ደቡባዊ አፍሪካዊቱን ሃገር ሞዛምቢክን በመታት ዝናብ አዘል ማዕበል ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ተናገሩ።
ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በየዕለቱ ለሚያደርገው መደበኛ በረራ ዛሬ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ከ38 ደቂቃ ላይ ከቦሌ ዓለምአቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ተነስቶ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ከተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሕይወት የተረፈ ማንም እንደሌለ ተረጋግጧል።
ተጨማሪ ይጫኑ