ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የጦርነት ወንጀል አድራጎቶች በመፈፀም የተወነጀለ የጦር አበጋዝ በሀገሪቱ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።
የደቡብ ሱድን መሪዎች እስከ ትላንት በነበረው ጊዜ ውስጥ እንጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ተደርጎበት የነበረው የሽግግር የውህደት መንግሥት ምስረታ ባለመከናወኑ ከሀገሪቱ ጋር የለኝን ግንኙነት እንደገና እገመግማለሁ ብላለች ዩናይትድ ስቴትስ።
የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንትና ዋናው የአማፅያን መሪ የውኅደት መንግሥት የመመስረቱን ጉዳይ ለ100 ቀናት ለማዘግየት ተስማምተዋል። እስከ መጪው ማክሰኞ ባለው ጊዜ ውስጥ ነበር መመስረት የነበረበት።
በአጋዴዝ ኒጀር የተገነባ አዲስ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ሰፈር ሙሉ በሙሉ ሥራ ጀምሮ የመጀመርያ በረራ አካሂዷል።
የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጀመሩትን የመደመር እሣቤና “ለአካባቢው ሀገሮች አስፈላጊ ነው” ያሉትን የሰላምና የመተባበር መንገድ ሶቺ ላይ አጉልተው ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በምሥራቅ አፍሪካ ክልሎች ከባድ ዝናብ መውረድ እንደሚቀጥል ተንብየዋል። ሀገሮቹ ከባድ ዝናብና የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲፈራረቅባቸው ቆይቷል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር አስተዳደር የርስ በርስ ጦርነቱን ለማስቆም የተደረሰውን ሥምምነት ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ማዕቀቦች ለመጣል ዝግጁ ነች ሲሉ በደቡብ ሱዳን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ቶማስ ሀሼክ አስታወቁ።
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል።
በዚምባብዌ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰሩ ነባር ሃኪሞች መንግሥት የኑሮ መሻሻልና የደመወዝ ክፍያ ጥያቄያቸውን ካላሟላ ከዛሬ አንስቶ አድማ ለመጀመር ዝተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ በ28 ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ሶማልያ ውስጥ ኤምባሲ ከፈተች። ዛሬ የተከፈተው አዲስ ኤምባሲ ሞቃዲሾ በሚገኘው ዓለምቀፍ አውይሮፕላን ማረፍያ ምድር ላይ ይገኛል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳይ ምክትል ዋና ፀኃፊ አርሰላ ሙለር ከትናንት ወድያ ሰኞና ማክሰኞ ኤርትራ ጉብኝት አካሂደዋል ሲል የኤርትራ የማስታወቅያ ሚኒስቴር መግለጫ ገልጿል።
ቱኒዚያ ውስጥ ትላንት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዷል። ከ24 በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈውበታል። ኦፊሴላዊ ያልሆነ የምርጫው ውጤት ባመለከተው መሰረት ከገዢው ክፍል ጋር ብዙም ትስስር የላቸውም የተባሉ ሁለት ተወዳዳሪዎች እየመሩ መሆናቸው ተዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ህክምና ላይ በነበሩበት በሲንጋፖር ሆስፒታል ያረፉት የቀደሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን ዛሬ ሃራሬ ገብቷል።
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስከሬን በመጪው ረቡዕ ሀራሬ በሚገኘው የሮበርት ጋብሪኤል ሙጋቤ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፍያ ላይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አረፉ። ስለሙጋቤ ህልፈት በኦፊሴል ትዊተራቸው ያስታወቁት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢመርሰን መናንጋግዋ ናቸው።
ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰሞኑን በተከሰተው መጤ-ጠል ጥቃት ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተናገሩ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት እየተፈፀሙ ያሉ ሁከቶችን በብርቱ ቃላት አውግዞ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
ኢትዮጵያና ሌሶቶ ባዶ ለባዶ፣ ቡሩንዲና ኤርትራ ሁለት ለአንድ ተለያይተዋል።
በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለማትረፍ በመሸሽ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ መሞታቸው ተነግሯል።
ሁለት መቶ ሺህ ቡሩንዲያውያን ስደተኞችን በመጪው ጥቅምት ወር ከታንዛኒያ ወደሃገራቸው መመለስ ለመጀመር የተደረሰው ስምምነት በስደተኞቹ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቤቱታ እናቀርባለንም ብለዋል፡፡ ቢያንስ አንድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ስደተኞቹ በግድ ቢመለሱ እከሳለሁ ብሏል።
ኬንያ ድፍድፍ ነዳጅ ዓለም መላክ መጀመሯን አስታወቀች።
መንግሥቱ የተዋቀረው ለረጅም ጊዜ የዘገየው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዶ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ካሸነፉ በኋላ መሆኑ ነው።
ኬንያ የ2019 ብሄራዊ ህዝብ ቆጠራ ቅዳሜና እሁድ ይደረጋል።
ተጨማሪ ይጫኑ