ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ላይ ሰሞኑን አል-ሸባብ ያደረሰውን ጥቃት የተቃወሙ ሶማሊያዊያን ዛሬ ኢስትሌ ቀበሌ ውስጥ ሰልፍ ወጥተዋል።
ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ፣ ባለፈው ወር ይፋ ያደረገችውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት እንድትሰርዝ ከአፍሪካ ሕብረት የተላለፈላትን ጥሪ ውድቅ አደረገች።
የሱዳን መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እያካሄደ ነው ያለውን ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ እንዲያቆም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ከሚሽነር ሚሼል ባሸሌ ጠየቁ።
የኬንያ መንግሥትና ተቃዋሚዎቹ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ ትናንት አደጋ በጣሉ ሽብርተኞች ላይ እጅግ ብርቱ የተባለ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል።
በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ነዋሪዎች፣ በየዞኑ ዋና ከተማ ሺኒሌ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
የዓለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ባግቦን ነፃ በማለቱ፣ “ይግባኝ እንጠይቃለን” ሲሉ፣ ዐቃብያነ ህግ አስታወቁ።
የዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ በጦር ወንጀለኛነት የተከሰሱትን የቀድሞ የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት ሎሬንት ግባግቦን ነፃ አላቸው።
ዚምባብዌ ውስጥ በነዳጅ ዋጋ መናር የተቆጡ ዜጎች የአካሄዱት ተቃውሞ የዋና ከተማዋን እንቅስቃሴ ቀጥ አድርጎ መዋሉ ተገለፀ።
ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ በማልታ ደሴት አቅራቢያ በሁለት የጀርመን ጀልባዎች ላይ ማረፊያ አጥተው የቆዩ አርባ ዘጠኝ ፍልሰተኞችን እንደሚያስተናግዱ የደሴቲቱ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆዜፍ ማስካት ዛሬ አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ሶማልያ ላይ በአካሄደው የአየር ድብደባ ሥስድት የአል ሸባብ አማፅያንን እንደገደለ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ገልጿል።
የጋቦን መንግሥት ቃል አቀባይ ዛሬ ማለዳ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት ወታደሮች ካለ አንድ በስተቀር ሁሉም ታስረዋል ሲሉ አስታውቀዋል።
ካርቱም የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምበሲ እንዳስታወቀው፣ ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ፣ አራት ደቡብ ሱዳናውያን ተገደሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ወንጀል አዳኝ ፖሊስ ሞዛምቢክ ውስጥ ግዙፍ የገንዘብ ሥርቆት የፈፀሙትን ሰዎች ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ ተቃርቧል።
በትናንትና ዕለት ከዛላንበሳ "ፋፃ" በተባለ አከባቢ ከባድ የጦር መሳርያዎች ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ የተደረገው እንቅስቃሴ የአካባቢው ሕብረተሰብ ስለ ጉዳዩ ማብራርያ እንፈልጋለን በማለተቸው ሂደቱን መስተጓጎሉን ይታወሳል።
የኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች አስከሬኖች ናቸው ብሎ እንደሚያምን የታንዛኒያ ፖሊስ የጠረጠራቸውን 13 አስከሬኖች መንገድ ላይ ወዳድቀው ማግኘቱን አስታወቀ።
የየኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ ለረዢም ጊዜ ሲገፋ የቆየውን ብሄራዊ ምርጫ ትላንት እሁድ ማካሄድዋ የሚታውቅ ቢሆንም፣ የምርጫው ሂደት ግን የቅንብር ጉድላት፣ የድምፅ ማጭበርበርና የምርጫ መሣርያዎች በሚገባ ያለመሥራት ጉድለት መስተዋላቸው ተገልጧል።
ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ውስጥ ከነገ በስተያ - ዕሁድ ይካሄዳል ለተባለው ምርጫ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንና ፀጥታና ደኅንነቱም ሙሉ በሙሉ እንደሚጠበቅ ፕሬዚዳንቱ ጆዜፍ ካቢላ ዛሬ አስታወቁ።
የበዙት አፍሪካዊያን የሆኑ ፍልሰተኞችን ያሳፈረች መርከብ ዛሬ ስፔን ወደብ ላይ ተጠግታለች።
ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ውስጥ የፊታችን ዕሁድ ይካሄዳል ከተባለው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጭ እንዲሆኑ መወሰኑ ያስቆጣቸው የሃገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢዎች ነዋሪዎች ያደረጉትን ሰልፍ ለመበተን ፖሊስ ዛሬ በወሰደው ዕርምጃ በተቃዋሚዎች ላይ ቀጥተኛ ተኩስ መክፈቱና አስለቃሽ ጋዝ መርጨቱ ተዘግቧል።
በሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሺር ላይ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለመደገፍ አንድ የሃገሪቱ ጋዜጠኞች ቡድን ሥራ ማቆሙን አስታውቋል።
ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች 37 ሰዎች መግደላቸውን የሚጠቁም መረጃ እንደደረሰው አምነስቲ አስታወቀ።
ቤልጄም በአፍሪካ ስለነበራት የቅኝ ገዢነት ታሪክ አያያዝን አስመልክቶ ስትታገል መቆየቷ ተገልጿል። በቅኝ ግዛቱ ወቅት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የኮንጎና የሩዋንዳ ተወላጆች በግጭትና በረሃብ ማለቃቸው ታሪክ ይናገራል።
በኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፖብሊክ በመጪው ሰኞ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው ምርጭ እንደሚተላለፍ ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሰዎች ገልፀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ጋንዳረሽ በተባለው የሶማልያ ጠረፍ አካባቢ ቅዳሜና ዕሁድ በአካሄደው ሥድስት ዙር የአየር ድብደባ 62 የፅንፈኛው አል ሸባባ አማጽያን መግደሉን ገልጿል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ተጨማሪ ይጫኑ