አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪካ ከተፃፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የደቡብ ሱዳን ሴት መሪዎች በቅርቡ በተደረገው የሰለም ሥምምነት መሰረት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከከፍተኛ ሥልጣን ሹመቶች 35 ከመቶዎቹ ለሴቶች እንዲመድቡ ጥሪ አድርገዋል።
የአንጎላው ፕሬዚዳንት ዣኦ ሎሬንኮ ከአንድ ዓመት ባላይ በሆነው የሥልጣን ጊዚያቸው ሙስናን ለማቆም ባደረጉት ጥረት ካለፉት የሀገሪቱ አስተዳደሮች የተሻለ ስኬት አስገኝተዋል ሲሉ መንግሥቱን አጥብቀው የሚነቅፉት ሳይቀሩ ተናግረዋል።
የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪያክ ማቻር “ ይምጡና ጁባን ይጎብኙ” ብለው ፕሬዚደንቱ ሳልቫ ኪር ያቀረቡላቸውን ግብዣ ሳይቀበሉት ቀሩ።
ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ሃገር ዳላስ ከተማ የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ወንድ ልጅና ባለቤታቸው በተንደላቀቀው መኖሪያ ቤታቸው አንዲት ጊኒያዊት ወጣት ለአሥራ ስድስት ዓመታት በባርነት ይዘው አኑረዋል ተብለው በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍ/ቤት ክስ ተመሰረተባቸው።
ትናንት ሃሙስ ከሰዓት በኋላ ቪክቶሪያ ሃይቅ ላይ በተገለበጠው የመንገደኛ ማመላለሻ ጀልባ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል ከአንድ መቶ የሚበልጡ መሞታቸውን የታንዛኒያ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የደቡብ ሱዳን ወታደሮች በዩኒቲ ክፍለ ሃገር በዚሁ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ በአካሄዱት ጥቃት ህፃናትና አረጋውያንን በቁማቸው አቃጥለዋል፣ ሴቶችን ደፍረዋል፣ ሲቪሎችን በጥይትና በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎቻቸው እየዳጡ ገድለዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሺናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት ወነጀለ።
የደቡብ ሱዳኑ የሰላም ሥምምነት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ውጊያው አገርሽቷል የሚሉ ሪፖርቶች እየተሰሙ ነው።
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአረቢያ ልሣነ-ምድር መንግሥታት ጋር ያሉበት የተሟሟቀ ግንኙነት ምናልባት ኢትዮጵያን ወደ የመኑ ጦርነት ይጎትታት ይሆን? የሚል ሥጋት የቀሰቀሰባቸው ጥቂት አይደሉም።
ከቦርኪና ፋሶ ጋር በሚያዋስነው የኒጀር ደቡባዊ አካባቢ አንድ ጣሊያናዊ ቄስ መጠለፋቸው ተገለፀ።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሴቶች ላይ በስፋት ለሚደርሰው ወሲባዊ ጥቃትና ድፍረት የሀገሪቱ መንግሥት የመፍትኄ ዕርምጃ አልወሰደም ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች ወነጀሉ።
በኢትዮጵያና በኤርትራ የሰላም ስምምነት ከተደረገ በኋላ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ድንበር ፈርሶ የእርስ በእርስ ግብይት ተጀምሯል።
ኬንያ የህፃናትን ሞት ቁጥር ለመቀነስ የእናት ጡት ወተት ማጠራቀሚያ ባንክ ልትጀምር ነው። የናት ጡት ወተት ለሚያስፈልጋቸው ህፃናት ከማንኛዋም እመጫት እናት በፈቃደኝነት የተለገሰን ወተት በማሰባሰብና በማስቀመጥ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሃገርም ለመሆን ዝግጅቷን ጨርሳለች።
እስላማዊ ልማት ባንክ ሶማሊያ ውስጥ የጀመረውን የብዙ ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በሙስና በብልሹ አስተዳደር ውንጀላዎች ሳቢያ ማገዱ ተጠቆመ።
በቅርቡ ሜዲቴራኒያን ባህር ሊቢያ ጠረፍ ላይ ከአንድ መቶ በላይ ፍልሰተኞች የተጫኑባት የጎማ ጀልባ ተገልብጣ መሞታቸው ተገለጠ።
ኬንያ በሕገወጥ ሀገሯ የሚኖሩ የውጪ ዜጎች ላይ እያረገች ያለውን አሰሳ እንደምትቀጥል አስታወቀች።
በቅርቡ ያረፉት የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን አስከሬን በመንግሥታዊ የቀብር ሥነ ስርዓት ወደሚያርፍበት ወደትውልድ ሃገራቸው ወደ ጋና ተወስዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሐምሌ / 2010 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ላደረጉት የአምስት ቀናት ጉብኝት የአሜሪካ ድምፅ የተሟላ ሽፋን ሰጥቷል።
አሥር የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከሁለት ዓመታት በፊት አንድ ሆቴል ውስጥ ወረራ ባካሄዱበት ወቅት የወሲብ ጥቃትና ግድያ ፈፅመዋል በሚል ክስ ተፈርዶባቸዋል።
የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ከይታ በያዝነወ ሳምንት ሁለተኛ የሥልጣን ጊዜያቸውን ለመጀመር ቃለ መሓላ በፈፀሙባት ወቅት በሀገሪቱ ሰሜንና ማዕካላዊ ክፍል ያለውን የፀጥታ መናጋት ለማርገብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
አውሮፓ የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁጥር ቀንሷል። በተለይም በሜዲትራንያን ባህር በኩል ለመጋባት ከሚሞክሩት ፍልሰተኞች የሚሞቱት ብዛት ግን ጨምሯል ይላል ዛሬ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች አገልግሎት ዘገባ።
ሶርያ የመጨረሻውን በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር ያለውን ቦታ ለማስመለስ ለያዘችው ዕቅድ ኢራን የድጋፍ ድምፅ እያሰማች ነው። በሰሜን ምስራቅ ሶርያ ያለው ዒድሊብ ክልል ከአሸባሪዎች ነፃ መሆን አለበት ማለትዋ ተገልጿል።
ቻይና ከኢንዱስትሪ ማዳበር እስከ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ድረስ በሚካሄድ የዕድገት ሥራ ላይ የሚልውል አዲስ 60 ቢልዮን ዶላር ለአፍሪካ እንደመታቀርብ አስታውቃለች። በያዝነው ዓመት ማብቅያ ገደማ ከወለድ ነፃ የሆኑ ብድሮች በምትሰጥበት ወቅት የአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ብድሮች እንደሚሰረዙም ገልፃለች።
በኤርትራ ዛሬ ዓመታዊው የኤግዚቢሽን በዓል በይፋ ተከፍቷል።
የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ቤጅንግ ላይ በሚካሄደው የቻይናና አፍሪካ ጉባዔ ላይ ሲሳተፉ የብዙ ሚሊዮንና የብዙ ቢሊዮን ዶላር ውሎች እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።
ተጨማሪ ይጫኑ