በኤርትራ ዛሬ ዓመታዊው የኤግዚቢሽን በዓል በይፋ ተከፍቷል።
የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ቤጅንግ ላይ በሚካሄደው የቻይናና አፍሪካ ጉባዔ ላይ ሲሳተፉ የብዙ ሚሊዮንና የብዙ ቢሊዮን ዶላር ውሎች እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።
ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፕላ ውስጥ ለህክምና ወደውጭ ሀገር ለመሄድ የሞከሩ ታዋቂ ተቃዋሚን ፖሊሶች ማሰራቸውን ተከትሎ ተቃውሞ መቀስቀሱ ተዘግቧል።
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ለይፋ ጉብኝት ኬንያ ገብተዋል።
የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊዎች መሪ ሪክ ማቻር ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የታቀደውን የሰላም ሥምምነት እንደሚፈርሙ፣ አደራዳሪው ዛሬ አስታወቁ።
ሶማልያ የሚገኘውና ሞቅዲሾ ስታዲየም ውስጥ ሰፍሮ የነበረው የተመድ ሚሽን አሚሶም ከስፖርት ሜዳው ለቆ መውጣቱ ተገለፀ።
ሀገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጋርዮሽ ንግድን ለማሳደግና የአሜሪካውያንን መዋዕለ ንዋይ መዳቢዎች ለመሳብ እንደምትፈልግ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።
የደቡብ ሱዳን ሽምቅ ተዋጊዎች መሪ ሪክ ማቻርና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የርስ በርስ ጦርነት ለማብቃት የታቀደውን የሰላም ሥምምነት አንፈርምም ማለታቸው ተሰማ።
የዚምባቡዌ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በቅርቡ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች እንዲሰርዝ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ ውድቅ አደረገው።
የኡጋንዳ መንግሥት የሀገሪቱ የፓርላማ አባል ሮበርት ኪያጉላኚን እንዲፈቱ ዛሬ በናይሮቢ የተቃውሞ ሠልፍ ተደረገ። በተቃውሞ ሠልፉ ላይ በርካታ ኬንያዊያን እንዲሁም በናይሮቢ የሚኖሩ የኡጋንዳ ዜጎች ተሳትፈውበታል።
ባለፈው ቅዳሜ ያረፉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ ዋና ፀኃፊ ሰሞኑን እየታሰቡ ናቸው።
የዚምባቡዌ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች በሚመለከት ከተቃዋሚዎች የቀረበውን ክስ ዛሬ ረቡዕ ማድመጥ ጀምሯል።
ሞዛምቢክ በሃገሩዋ የሚሰማሩ ጋዜጠኞችን ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በዓለም ወደር የሌለው የምዝገባ ክፍያ ማስከፈል ትጀምራለች።
ደቡብ አፍሪካዊያን በመላ ሃገሪቱ ተንሠራፍቷል የሚባለውን “ስቴት ከፕቸር” የሚባለውን የሙስና መረብ ሊያጋልጥ የሚችል የፍርድ ቤት ምርመራ የሚጀመርበትን ጊዜ እየተጠባበቁ መሆናቸው ተነግሯል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ ዋና ፀኃፊና የኖቤል የሰላም ሽልማት ባለቤት ኮፊ አናን ከአጭር ጊዜ ሕመም በኋላ ከትናንት በስተያ፣ ቅዳሜ አርፈዋል።
የዓለምቀፍ የሕግ ምሁራን ኮሚሽን(ICJ) የኬንያ መንግሥት በሕገወጥ ግንባታዎች ላይ እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ ተቸ።
በምርጫ የተወዳደሩት የማሊ ፕሬዚዳንት ኖውበከር ኬታ በማጣርያው ምርጫ በከፍተኝ ድምፅ አሸንፈዋል።
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ እንደገና ለመመረጥ ላለመወዳደር መወሰናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ በደስታ ተቀብላለች፡፡
ካርቱም ላይ የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ላይ ከደረሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዳንዶቹ በሥምምነቱ በተካተቱት በአንዳንዶቹ አንቀፆች ባንስማም የፈረምነው ለሰላም ዕድል ስንል ነው ይላሉ፡፡
የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ ዛምቢያ ድንበር ላይ ተይዘው ታሰሩ።
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። በመጪው ምርጫ የቀድሞ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪን ዕጩነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
አልቃይዳ በ1998 በዳሬሰላምና በናይሮቢ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች ላይ ያደረሰዉ ጥቃት ታወሰ
የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ከሰባት ዓመታት በፊት የብዙ ሰዎች ደም ካፋሰሰው የእርስ በርስ ጦርነት በተያያዙ ጥፋቶች ለተወነጀሉ ሰዎች ትናንት በሰጡት ምህረት ተጠቃሚዎች መካከል አንዷ የቀድሞ የሀገሪቱ ቀዳማዊት እመቤት ሲሞን ባግቦ መሆናቸው ታወቀ።
የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መብረር ጀምሯል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
ተጨማሪ ይጫኑ