የዚምባቡዌ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ወር የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶች በሚመለከት ከተቃዋሚዎች የቀረበውን ክስ ዛሬ ረቡዕ ማድመጥ ጀምሯል።
ሞዛምቢክ በሃገሩዋ የሚሰማሩ ጋዜጠኞችን ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በዓለም ወደር የሌለው የምዝገባ ክፍያ ማስከፈል ትጀምራለች።
ደቡብ አፍሪካዊያን በመላ ሃገሪቱ ተንሠራፍቷል የሚባለውን “ስቴት ከፕቸር” የሚባለውን የሙስና መረብ ሊያጋልጥ የሚችል የፍርድ ቤት ምርመራ የሚጀመርበትን ጊዜ እየተጠባበቁ መሆናቸው ተነግሯል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞ ዋና ፀኃፊና የኖቤል የሰላም ሽልማት ባለቤት ኮፊ አናን ከአጭር ጊዜ ሕመም በኋላ ከትናንት በስተያ፣ ቅዳሜ አርፈዋል።
የዓለምቀፍ የሕግ ምሁራን ኮሚሽን(ICJ) የኬንያ መንግሥት በሕገወጥ ግንባታዎች ላይ እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ ተቸ።
በምርጫ የተወዳደሩት የማሊ ፕሬዚዳንት ኖውበከር ኬታ በማጣርያው ምርጫ በከፍተኝ ድምፅ አሸንፈዋል።
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ እንደገና ለመመረጥ ላለመወዳደር መወሰናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ በደስታ ተቀብላለች፡፡
ካርቱም ላይ የሥልጣን ክፍፍል ሥምምነት ላይ ከደረሱት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዳንዶቹ በሥምምነቱ በተካተቱት በአንዳንዶቹ አንቀፆች ባንስማም የፈረምነው ለሰላም ዕድል ስንል ነው ይላሉ፡፡
የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቴንዳይ ቢቲ ዛምቢያ ድንበር ላይ ተይዘው ታሰሩ።
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ድጋሚ ለመመረጥ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ። በመጪው ምርጫ የቀድሞ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪን ዕጩነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
አልቃይዳ በ1998 በዳሬሰላምና በናይሮቢ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች ላይ ያደረሰዉ ጥቃት ታወሰ
የአይቮሪኮስት ፕሬዚዳንት አላሳን ዋታራ ከሰባት ዓመታት በፊት የብዙ ሰዎች ደም ካፋሰሰው የእርስ በርስ ጦርነት በተያያዙ ጥፋቶች ለተወነጀሉ ሰዎች ትናንት በሰጡት ምህረት ተጠቃሚዎች መካከል አንዷ የቀድሞ የሀገሪቱ ቀዳማዊት እመቤት ሲሞን ባግቦ መሆናቸው ታወቀ።
የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መብረር ጀምሯል።
አፍሪካ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየመን ልዩ ተወካይ የሀገሪቱን ተፋላሚ ወገኖች የሰላም ድርድር ለማድረግ በሚያስችል ማቀፍ በሚመለከት ጄኔቫ ላይ እንዲነጋገሩ ሊጋብዟቸው አቅደዋል።
የዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች በድኅረ ምርጫው በመዲናይቱ ሀረሬ የሦስት ሰዎች ህይወት ያጠፋውን የወታደሮች ዕርምጃን አውግዘዋል። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዘገየ የተባለውን የምርጫ ውጤት በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
ዚምባብዌ ውስጥ ዛሬ ምርጫ ተካሂዷል። ለ38 ዓመታት ያህል በሮበርት ሙጋቤ ስትገዛ ከቆየች በኋላ የደቀቀው የሀገሪቱ ኢኮኖሚና ገፅታ ይሻሻላል የሚል እምነት እንዳለ ተገልጿል።
ኮንጎ በቅርቡ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ወረርሽኝ ቆሟል ስትል አወጀች። ይህ ሊሆን የቻለው በጤና ጥበቃ ባለሥልጣናቷና የዓለም የጤና ድርጅት ፈጣን ርብርብ መሆኑን ገልጣለች።
የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ሥምምነት ዘላቂነት እንዲኖረው፣ ድንበር ሲካለል የሚመለከታቸው ህዝቦች በጉዳይ እንዲሳተፉ ማድረግና ማነጋገር ያስፈልጋል ብለዋል የለንደን ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊ አቶ አብድረሓማን ሰይድ።
ኬንያ ግዙፉን የድሆች ሰፈር መንገድ ለመሥራት አፈራርሳ ሰውን መኖሪያ አልባነት አድርጋለች ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዛት።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሥልጣን ዘምኑን በተጨማሪ ሦስት ዓመት ለማራዘም የወሰደውን እርምጃ በማውገዝ የሀገሪቱ መሪዎች የሰላም ሥምምነት ላይ ለመድረስ ከልብ እንዲደራደሩ የጠይቀውን የዋይት ሃውስ መግለጫ ጁባ ነቀፈች።
ሶማሊያ የታችኛው ጁባ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ዛሬ ሰኞ ማለዳ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት አድርሰው ቢያንስ አሥራ ሁለት ሰዎች ተገደሉ።
“እንደ እኔ አስተያየት አሁን ዋናው መመለስ ያለበት ጥያቄ በምን መልክ በኤርትራና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውሕደት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ነው። ቁልፉ ኢትዮጵያ እጅ ነው ያለው።” ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ። “አሁን ለተጀመረው ቁልፉን የያዘችው ኢትዮጵያ ናት" በሚለው አልስማም። አሁን የሚደረገው የእርቅ ምመንገድ የተጀመረው በሁለት ብሔረ መንግስታት ልንለው እንችላለን ነው። ስለዚህ ሰጥቶ መቀበልን ከግንዛቤ የሚያስገባ ነው የሚሆነው።”ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ። “ይህ ሁኔታ ዳር እንዲደርስ ሁሉም በየበኩሉ ቀና ለሆነው ለውጥ ራሱን ማዘጋጀት አለበት። 'ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ያደርጉልናል' ብለን ቁጭ ብንል ለስኬት የመብቃት ዕድሉ አናሳ ነው የሚሆን።” ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ።
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ ጥገኝነት የጠየቁ ቁጥራቸው ወደ አምስት መቶ ለሚጠጋ ሶማሊያውያን የተሰጣቸውን ጊዚያዊ ህጋዊ ከለላ እንዲራዘምላቸው ወሰነ።
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ በመጪው እኤአ ታህሳስ 23 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድ ገለጹ። የወደፊት የፖለቲካ ዕቅዳቸውን አልተናገሩም።
ተጨማሪ ይጫኑ